ነሐሴ 24 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢራን ተፅዕኖ ፈጣሪ ሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ መሪ የሆኑት ሞጅታባ ኻመነኢ ለፋርስ ባሕረ ሰላጤ ሀገራት መሪዎች በላኩት የጽሁፍ መልእክት፣ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በቀጣናው ላይ ስጋት የደቀነውን «እውነተኛ ጠላት» በጋራ እንዲጋፈጡ ጥሪ አቅርበዋል። በደብዳቤው ላይ እንደተጠቀሰው፣ የኢራን ከፍተኛ መሪ የአያቶላህ አሊ ኻመነኢ ልጅ የሆኑት ሞጅታባ ኻመነኢ፣ የፋርስ ባሕረ ሰላጤ ሀገራት የውጭ ኃይሎች በቀጣናው ጉዳይ ውስጥ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም እና የጋራ ደህንነታቸውን ለማስጠበቅ በአንድነት ሊቆሙ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሞጅታባ ኻመነኢ በዚሁ መልእክታቸው በቀጣናው የሚገኙ ሀገራት እርስ በእርስ ከመቃረን ይልቅ፣ የጋራ ሰላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ ውይይትና ትብብርን ማስቀደም እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። የፖለቲካ ተንታኞች እና የዲፕሎማሲ ባለሙያዎች እንደሚያመላክቱት፣ ይህ የጽሁፍ መልእክት ኢራን በይፋዊ እና በኢ-ይፋዊ መንገድ ከጎረቤት አረብ ሀገራት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማጠናከር እና በቀጣናው ያለውን ወታደራዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ውጥረት ለማቃለል የምታደርገው ጥረት አካል ነው:: በተጨማሪም የውጭ ሀገራት በይፋ ወታደራዊ በረራዎች እና እንቅስቃሴዎች በፋርስ ባሕረ ሰላጤ ላይ የሚያሳድሩትን ተፅዕኖ ለመቀነስ ያለመ እርምጃ እንደሆነ ተገልጻል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ