መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲሱ ዓመት ዋዜማ ከ600 በላይ ታራሚዎች በይቅርታ መፈታታቸው ሲገለጽ፤ ይህም የሆነው በሀገራዊ ምክክሩ ጥያቄ መሰረት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ባደረገው የአመቻችነት ሚና እንደሆነ ታውቋል፡፡ ከ600 በላይ ታራሚዎቹ መፈታታቸው በአንድ በኩል የይቅርታና የምህረት ሕጋዊ ሥርዓትን መሰረት ያደረገ መሆኑን በመጥቀስ፤ መንግስትም የወሰደው እርምጃ ተገቢነት ያለው ነው ሲሉ የሕግ ባለሙያዎች ሀሳባቸውን ለመናኸሪያ ሬዲዮ ገልጸዋል፡፡ ምህረት እና ይቅርታ በሕጉ የተቀመጡና ሕጋዊ መሰረት ያላቸው ቢሆኑም አፈጻጸማቸው የተለያየ እንደሆነ የሚገልጹት የሕግ ባለሙያው አቶ ዮናስ ወልደየስ፣ እንደ ሀገር እነዚህ ሂደቶች እጅግ አስፈላጊ ናቸው ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል ያለ ፍርድ ሂደት ረጅም ጊዜ ታስረው የሚቆዩ ዜጎች መኖራቸውን በመጥቀስ፣ ይህ ሁኔታ መሻሻል እንዳለበት እና ለዚህም የፍትሕ ተቋማት ጠንካራ ሥራ ሊሠሩ እንደሚገባ ሀሳባቸውን አሳፍረዋል፡፡ ይህንኑ ሀሳብ የሚያጠናክሩት ሌላኛው የሕግ ባለሙያ አቶ አምደገብርኤል አድማሱ፤ መንግስት የወሰደው እርምጃ ታራሚዎቹ ወጥተው ሕዝብን ማገልገል እንዲችሉ እና ሀገሪቱ ካለችበት ሁኔታ አንጻር ሰላምን ለማስፈን በማሰብ ነው ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡ ምህረት እና ይቅርታ የራሳቸው የአፈጻጸም ሂደት ቢኖራቸውም ሕጋዊ መሰረት ያላቸው በመሆኑ፣ እንደነዚህ ዓይነቶች እርምጃዎች በመንግስት በኩል ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል፡፡ በሌላ በኩል የሚስተዋሉ የፍትሕ መዘግየት ሂደቶች ሊሻሻሉ እንደሚገባቸው አስምረውበታል፡፡ አንድ ተከሳሽ ፍርድ እስኪሰጥበት ድረስ ንጹሕ ሆኖ የመገመት፣ የቅድመ ፍርድ እስር ሕጋዊ መሠረት ያለው መሆን፣ እንዲሁም የእስር ጊዜውና የፍርድ ሂደቱ ፈጣንና በሕጉ መሠረት ሊመራ እንደሚገባው ባለሙያዎቹ አፅንኦት ሰጥተውበታል፡፡
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ