ነሐሴ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)
የሐብሐብ ፍሬዎች በውስጣቸው ከፍተኛ መጠን ያለው ፕሮቲን፣ ለልብ ጤንነት ጠቃሚ የሆኑ ጤናማ ስቦች፣ ማግኔዚየም፣ ዚንክ እና ኮፐር የያዙ በመሆናቸው እጅግ ከፍተኛ አልሚ ምግብ የሚገኝባቸው የፍሬ አይነቶች እንደሆኑ የሥነ-ምግብ ተመራማሪዎች ገልጸዋል።
አብዛኛው ሰው የሐብሐብን ፍሬ ዘንግቶ የሚጥለው ቢሆንም፣ ፍሬዎቹን አቁላስቶ ወይም ደርቀው ሲበሉ ለሰውነት አስፈላጊ የሆኑ በርካታ ማዕድናትን ያቀርባሉ። በውስጡ የሚገኘው ማግኔዚየም የልብ ምትንና የደም ግፊትን ለማስተካከል የሚረዳ ሲሆን፣ ዚንክ ደግሞ የሰውነት በሽታ የመከላከል አቅምን ለማጠናከር እና የሕዋሳትን እድገት ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል።
በተጨማሪም የሐብሐብ ፍሬዎች በውስጣቸው የያዙት ከፍተኛ የፕሮቲን እና የኮፐር መጠን የጡንቻዎችን ጥንካሬ ለመጠበቅ፣ የምግብ መፈጨት ሥርዓትን ለማቃናት እና የቆዳ እንዲሁም የፀጉር ጤንነትን ለመጠበቅ እንደሚረዳ የጤና ባለሙያዎች ያመላክታሉ።
_
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ