ነሐሴ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)
የአየር ማቀዝቀዣዎችን ሌሊቱን ሙሉ አበራርቶ መተኛት በሰውነት ላይ የተለያዩ የጤና መዛባቶችን ሊያስከትል እንደሚችል የሕክምና እና የጤና ባለሙያዎች ገልጸዋል።
የአየር ማቀዝቀዣ መሳሪያዎች በክፍል ውስጥ ያለውን እርጥበት በመምጠጥ አየሩ እንዲደርቅ ስለሚያደርጉ፣ በሰዎች ላይ የቆዳ ድርቀት እና የከንፈር መሰነጣጠቅ ያጋጥማል። በተጨማሪም የደረቀ አየርን ሌሊቱን ሙሉ መተንፈስ የጉሮሮ እና የመተንፈሻ አካላትን በማስቆጣት ለጉሮሮ ህመም፣ ለሳል እና ለጠዋት የጉሮሮ መድረቅ መንስኤ ይሆናል።
በተጨማሪም ሌሊቱን ሙሉ የሚወጣው ቀዝቃዛ አየር በሰውነት ላይ በቀጥታ ሲያርፍ የደም ዝውውር እንዲቀንስ እና የጡንቻዎች መኮማተር እንዲፈጠር ያደርጋል።
ይህም ሰዎች ጠዋት ከእ እንቅልፋቸው ሲነቁ የአንገት፣ የጀርባ እና የመገጣጠሚያዎች ግትርነት ወይም ህመም እንዲሰማቸው እንደሚያደርግ የሕክምና መረጃዎች ያመላክታሉ።
_
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ