ሰኔ 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ወጣቶች በፍጥነት እየተለወጠ ያለውን የዲጂታል ዓለም በተሳካ ሁኔታ እንዲቀላቀሉና እንዲያሸንፉ ለማስቻል “አዶናይ ቲክቶክ አካዳሚ” ሥራ ሊጀምር መሆኑን ወጣቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ አዶናይ አለሙ አስታወቀ።
አካዳሚው በዋናነት በርካታ ወጣቶችን ወደ ዲጂታሉ ዓለም በማስገባት፣ በቴክኖሎጂውና በንግዱ (ቢዝነሱ) መካከል አስተማማኝ ድልድይ የሚሆኑ ብቁ ባለሙያዎችን ለማፍራት ያለመ ነው ተብሏል።

ሰልጣኞች የዲጂታል ሥርዓቱን (ሲስተሙን) ቀመር በትክክል ተረድተው ሥራ ላይ እንዲያውሉ የሚረዳቸው ሲሆን፣ ከቴክኒክ ዕውቀት ባሻገር የራሳቸውን እምቅ አቅም እንዲያውቁ፣ አመለካከታቸውን እንዲቀይሩ፣ እንዲሁም ሰዎችን የመረዳትና የማስረዳት ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ተመቻችቷል።
በተያያዥም፣ “ሻርክ ታሌንት ማናጅመንት” የተሰኘው ቡድን ከዚሁ ሥራ ጋር በመቀናጀት፣ የወጣቶቹን ራእይ (ዕይታ) ወደ ተግባር በመቀየርና ጠንካራ የግልም ሆነ የተቋም ብራንዲንግ በመገንባት ረገድ በስፋት እንደሚሠራ ታውቋል።
ይህ ዕቅድ ወጣቶች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ብቻ ሳይሆኑ፣ ስኬታማ የዲጂታል ሥራ ፈጣሪዎች እንዲሆኑ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ