ሰኔ 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዋጅ ቁጥር 985/09 መሠረት በ2017 ዓ.ም የተቋቋመው ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ማኅበር፣ ለሴቶች ከፍተኛ የብድር አማራጮችን ማዘጋጀቱን አስታውቋል። ማኅበሩ የኤሌክትሪክ መኪና ግዢ ለመፈጸም ፈልገው ብድር ለወሰዱ አባላቱ የመኪና ርክክብ ፈጽሟል። ምንም እንኳን በገበያ ላይ በታየው የመኪና ዋጋ መጨመር ምክንያት ርክክቡ በተባለው ጊዜ ባይከናወንም፥ ከደንበኞች ጋር በተደረገ መግባባት መኪኖቹን ማስረከብ መቻሉን የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ ጫካ ተናግረዋል።
ማኅበሩ የኅብረተሰቡን ፍላጎት ለማሟላት ሦስት አዳዲስ የብድር አማራጮችን ማቅረቡን የገለጹት ሥራ አስኪያጁ፤ የአዲስ መኪና ዋጋ መጨመርን ከግምት በማስገባት የመኪና ብድር፣ ቤት ለመሥራት፣ ለማደስ ወይም ለመግዛት ለሚፈልጉ የቤት ብድር፣ እንዲሁም በንግድ ሥራ ላይ ለተሰማሩና ሥራቸውን ለማስፋፋት ተጨማሪ በጀት ለሚያስፈልጋቸው የንግድ ብድር ማዘጋጀቱን አስረድተዋል።
በተጨማሪም ማኅበሩ ለሚዲያ እና ለኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ልዩ የብድር አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የተገለጸ ሲሆን፥ በርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ከአባላት ጋር የአሠራር ምክክር ተካሂዷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ