መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነቡ የኃይል ማመንጫ ግድቦች በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ተጽዕኖ ቢኖራቸውም፣ በትብብር ከተመሩ ለቀጠናው ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው ገልጸዋል። ውሳኔው የኢትዮጵያን ሀገራዊ የኃይል አቅርቦት ለማስፋፋት፣ የኤሌክትሪክ ተዳራሽነትን ለማረጋገጥ እና ትርፍ ኃይልን ለጎረቤት ሀገራት በመሸጥ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ይናገራሉ። ደቡብ ሱዳን በላይኛው ናይል ተፋሰስ ላይ ግድብ ለመገንባት የምታደርገው እንቅስቃሴ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን (CFA) መሠረት ያደረገ መሆኑን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡ ውሳኔው እስካሁን በግብፅ በኩል የነበረውን የውኃ አጠቃቀም የበላይነትና ጫና በጋራ ለመጋራት እንዲሁም ፍትሐዊ አጠቃቀምን ለማስፈን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ በዲፕሎማሲና በልማት ዘርፍ ድጋፍ የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ፣ ሌሎች የተፋሰሱ ሀገራትም ወደ ተመሳሳይ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲገቡ መንገድ የሚከፍት በመሆኑ ለቀጠናው ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት የወሰደችው ውሳኔ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስጠብቅና የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን የሚያረጋግጥ መሆኑን የዲፕሎማሲ ባለሙያው አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ገልጸዋል። ውሳኔው ከኢትዮጵያም ሆነ ከሌሎች የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት የጋራ ስምምነት ጋር የሚጣጣም መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ፤ ግድቡ መገንባቱ ሀገራት የተፈጥሮ ሀብታቸውን በሉዓላዊነት የመጠቀም መብታቸውን የሚያጠናክር እና የጋራ ተጠቃሚነት መርሕን የሚያጎለብት ነው ብለዋል። የግድቡ መገንባት የደቡብ ሱዳንን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ሌሎች የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትንም በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የውጭ ምንዛሬ ተመን መጨመር በዶሮና እንቁላል ዋጋ ላይ ተፅዕኖ ማሳደሩ ተገለጸ
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በ2017 በጀት አመት በዶሮና እንቁላል ምርት ላይ ለተስተዋለው ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ የውጭ ምንዛሬ መጨመር የራሱን... read more
የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን የጎበኙ የውጭ አገር ቱሪስቶች ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል ተባለ
የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን ባለፉት ዘጠኝ ወራት የጎበኙ የውጭ አገር ቱሪስቶች ቁጥር ከቀደመው በእጥፍ መጨመሩን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ብሄራዊ ፓርኩንና... read more
በጋምቤላ ክልል ህጻናት በቤት እንስሳት እየተለወጡ ነው ተባለ
በጋምቤላ ክልል ህጻናትን በቤት እንስሳት የመለዋወጡ ልማድ አሁንም ድረስ አለመቀረፉ እንዳሳሰበው የገለጸው የክልሉ የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ነው፡፡
ቢሮው አሁንም... read more
“ደህንነቱ የተጠበቀ የጤና ክብካቤ ለሁሉም ጨቅላ ህፃናት እና ህፃናት” በሚል መሪ ቃል የዓለም የታካሚዎች ደህንነት ቀን በላንድማርክ ሆስፒታል ተከበረ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም የታካሚዎች ደህንነት ቀን በላንድማርክ ጠቅላላ ሆስፒታል እየተከበረ ነው።
"ደህንነቱን የጠበቀ የጤና ክብካቤ ለሁሉም ጨቅላ... read more
በጅማ ከተማ የተፈጸመውን የቦምብ ጥቃት ተከትሎ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኦሮሚያ ክልል ጅማ ከተማ እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማት ለመጎብኘት የሄዱ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ባረፉበት ሆቴል... read more
በአዲስ አባባ ከተማ ከህንጻ ተደራሽነት ጋር በተያያዘ ግልጽ የአቤቱታ ማቅረቢያ መድረክ አዘጋጅቶ መፍትሔ እያሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ገለጸ
በመዲናዋ በህንጻ ተደራሽነት ዙሪያ ግልጽ የአቤቱታ ማቅረቢያ መድረክ ተዘጋጅቶ አካል ጉዳተኞች ለመንግስት አመራሮች ቅሬታቸውን አቅርበው ምላሽ ማግኘታቸውን ኮሚሽኑ ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡
ኮሚሽኑ... read more
ጥሬ ኑድል በልቶ ህይወቱ ያለፈው የ13 አመት ወጣት አሳዛኝ ሞት በግብፅ ሀገራዊ ክርክር አስነሳ
ነሐሴ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አንድ የ13 አመት ታዳጊ ሶስት እሽግ ጥሬ ፈጣን ኑድል ከተመገበ በኋላ ህይወቱ ማለፉን ተከትሎ በግብፅ... read more
ቦንጋ ከተማ በተከሰተው ድንገተኛ የትራፊክ አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ደረሰ
በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ሸታ ቀጠና (ካምፕ ሰፈር) ቁልቁለት በመውረድ ላይ እያለ በደረሰው ድንገተኛ ትራፊክ አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት... read more
የአየር ትንበያ ግምገማ እና የ2019 የበጋ አየር ትንበያ ይፋ ተደረገ
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያለፈውን የክረምት ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማ እና የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ... read more
መሐመድ እድሪስ የሰላም ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ
ኅዳር 20 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ መሐመድ እንድሪስ አቶ ብናልፍ... read more
ምላሽ ይስጡ