መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኤሊኖን ለዘመናት በተለያየ ስያሜ እየተጠራ አሉታዊ ተጽዕኖ ሲያሳድር የቆየ አለም አቀፍ ክስተት እንደሆነ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የስትራቴጂክና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አይድሩስ ሀሰን ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ሜትሪዮሎጂ ኢንስቲትዮት በሰጠው የትንበያ መረጃ፣ በአገሪቱ በ8 ክልሎች፣ በ37 ዞኖች፣ በ178 ወረዳዎች የኤሊኖን ክስተት እንደሚያጋጥም መገለጹን አስታውሰዋል። ዘንድሮ በተከሰተው ኤሊኖን ሁለት ከፍተኛ ተጽዕኖዎች ማለትም ከፍተኛ የዝናብ እጥረት ወይም ድርቅ እና የጎርፍ አደጋ እንደሚጠበቅ ምክትል ኮምሽነሩ አመላክተዋል። ኮምሽኑ ከሌሎች የመንግስት ተቋማት ጋር በመሆን ለክስተቱ ብቻ ሳይሆን ከኤሊኖን ባሻገር ምላሽ ለመስጠት በቂ ዝግጅት ማድረጉን ተናግረዋል። ክስተቱን ተከትሎ ለሚያጋጥም አደጋ ምላሽ ለመስጠት የሰብዓዊ እርዳታን በራስ አቅም ለመሸፈን ቀደም ብሎ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት በተጀመረው “የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” ትልቅ አቅም መፍጠር እንደተቻለ አመላክተዋል። በዚህም መሰረት እንደ አገር ለኤሊኖን ብቻ ሳይሆን፣ ከኤሊኖን ባሻገር ለሚያጋጥም አደጋ ምላሽ ለመስጠት በቂ ዝግጅት እንደተደረገ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን የስትራቴጂክና ሎጂስቲክስ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አይድሩስ ሀሰን አስታውቀዋል። ኮምሽኑ ከመንግስት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ጋር በጋራ ባዘጋጀው መድረክ ለፌደራል እና የክልል የኮምዩኒኬሽን እና ሚዲያ አካላት በኤሊኖን ወቅታዊ ሁኔታ፣ በሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነት እና በተቀናጀ የሚዲያ እና መረጃ ልውውጥ ዙሪያ ምክክር እያደረገ ነው። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የሴቶች ያለዕድሜ ጋብቻ እና ግርዛት የወንጀል ህግ እንዲሻሻል ለፍትህ ሚኒስቴር የማሻሻያ ጥናት መቅረቡ ተገለጸ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል የሴት ልጅ ግርዛትን በተመለከተ የተጣለው የወንጀል ቅጣት... read more
ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተሰጠ መግለጫ!
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ ኤምባሲ ዶሎ ዞንን በተመለከተ ያወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ በአካባቢው ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አያንጸባርቅም! የሶማሌ ክልል... read more
በዓሉን ምክንያት በማድረግ ደንብ በተላለፉ 280 በሚሆኑ አካላት ላይ የቅጣት እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
ጥር 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በገና በዓል የተለያዩ ህገ ወጥ ድርጊቶች... read more
በአሜሪካ ላሞች ላይ የVR መነጽር በማድረግ ጭንቀታቸው እንዲቀንስ እየተደረገ ነው ተባለ
👉መነጸሩ አረንጓዴ ሜዳዎችን እንዲያዩና ብዙ ወተት እንዲያመርቱ ያግዛቸዋል ነው የተባለው
ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በሚገኙ አንዳንድ እርሻዎች ላሞች በረት... read more
የአድዋ ድልን በስነ-ስዕል በመግለጽ ረገድ ገና እንዳልተሰራበት የዘርፉ ባለሙያዎች ገለጹ
የካቲት 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ታሪክን በሙዚቃ፣ በስዕል፣ በተውኔት እና በሌሎች ኪነጥበባዊ ስራዎች የመግለጽ እድል ቢኖርም ኢትዮጵያ ታሪካዊ ሁነቶቿን በተገቢው መልኩ... read more
በጣሊያን የአውሮፕላን ሞተር ሰው ስቦ አስገባ
በጣሊያን አንድ ሰው በአውሮፕላን ሞተር ተስቦ በመግባቱ የተነሳ ሁሉም የቤርጋሞ አውሮፕላን ማረፊያ በረራዎች እንዲታገዱ ተደረገ
ሐምሌ 1 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሰሜናዊ ጣሊያን... read more
“የሞት ወፍ” እየተባለ የሚጠራው አደገኛ አዳኝ፤በአዳኝነቱ የሚወዳደረው የለም ተባለ
ነሐሴ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በልዩ አደን ዘዴው እና በሚያስፈራ ቁመናው የሚታወቀው ሹቢል ስቶርክ (Shoebill Stork) የተባለው ወፍ፣ በአራት ጫማ... read more
በግድያ ወንጀል እና ከባድ በሰው አካል ላይ ጉዳት ማድረስ ወንጀል የተከሰሰው ግለሰብ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጣ
ተከሳሽ በፍቃዱ ተሰማ በጋምቤላ ክልል በማጃንግ ብሔረሰብ ዞን በጎደሬ ወረዳ ካቦ ቀበሌ ውስጥ በቀን 22/4/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ... read more
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ቋሚ ኮሚቴዎች ለነገ ረቡዕ ያዘጋጇቸውን የሥራ መርሐግብሮች ይፋ አድርገዋል
ጥቅምት 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጽህፈት ቤት፣ የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች ለነገ ረቡዕ... read more
የእስራኤል እና የኢራንን ወቅታዊ የህዝብ ብዛትና የቆዳ ስፋት እንዲሁም #ወታደራዊ አቅም ሲዳሰስ
🔰የእስራኤል ዝርዝር መረጃ‼️
እስራኤል በ2025 የህዝብ ብዛቷ ወደ 9,517,181 የተጠጋ ሰዎች እንዳሏት መረጃዎች አመላክተዋል።
የቆዳ ስፋት ደግሞ 22,145 ካሬ ኪሎ ሜትር እንደሆነና... read more
ምላሽ ይስጡ