ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የለንደኑ ክለብ ቼልሲ እና ኖቲንግሃም ፎረስት በ23 ዓመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ሊያም ዴላፕ ዝውውር ዙሪያ ሙሉ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበዋል።
ባለፈው ክረምት ከኢፕስዊች ታውን በ30 ሚሊዮን ፓውንድ ስታምፎርድ ብሪጅን የተቀላቀለው ዴላፕ፣ በቼልሲ ቤት ባሳለፈው የመጀመሪያ የውድድር ዘመን በጉዳት እና በአሰልጣኞች መቀያየር ምክንያት በቂ የመጫወት እድል ሳያገኝ ቀርቷል።
ቼልሲዎች መጀመሪያ ላይ ለተጫዋቹ እስከ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ዝውውሩን በ45 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ለማጠናቀቅ ፈቃደኛ ሆነዋል። ታይዎ አዎኒዪን በ9 ሚሊዮን ፓውንድ ለኮቨንትሪ ሲቲ የሸጡት ኖቲንግሃም ፎረስቶች፣ በኦሊቨር ግላስነር ስር የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ዴላፕን ዋነኛ ኢላማቸው አድርገውታል።
ኤቨርተኖችም በተጫዋቹ ላይ ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ ዴላፕ በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየት ፍላጎት ያለው በመሆኑ እና ፎረስትም ድርድሩን በመግፋቱ የሕክምና ምርመራውን አጠናቆ ይፋዊ ውል ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።
ጉዳት እንዲሁም የአሰልጣኞች መቀያየር ተጫዋቹ በብሪጅ የነበረውን ቆይታ ከባድ አድርገውታል። በቼልሲ ማልያ በፕሪሚየር ሊጉ 1 ጎል ብቻ ነው ማስቆጠር የቻለው። ባጠቃላይ በቼልሲ ቆይታው ባደረጋቸው 47 ጨዋታዎች 3 ጎሎችን ብቻ ነው ማስቆጠር የቻለው።
በ24 ዓመቱ ላይ የሚገኘው እንግሊዛዊው አጥቂ የኖቲንጋም ፎረስት የሪከርድ ግዢ ሆኖ ወደ ሲቲ ግራውንድ የሚያመራ ሲሆን፣ ወጥነት ባለው መንገድ ኳስ እና መረብን ለማገናኘት የሚችልበት ወሳኝ የዕድሜ ክልል ላይ ስለሚገኝ ዕድሉን በሚገባ በሲቲ ግራውንድ ይጠቀማል ተብሎ ይገመታል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገር የመመለስ ስራ ተጀምሯል ተባለ
ኅዳር 26 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሊባኖስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገር የመመለሱ ስራ መጀመሩን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት... read more
ዲሚትሪ ፓዬት ከእግር ኳስ ሜዳ ተሰናበተ
መጋቢት 16 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ፈረንሳዊው የአማካይ መስመር ተጫዋች ዲሚትሪ ፓዬት ለ21 ዓመታት የዘለቀውን ስኬታማ የእግር ኳስ ዘመን በይፋ ማክተሙን አስታውቋል።... read more
ኦቪድ ሪል እስቴት ኪንግስ ታወር ስር በሰየመው ሳይት የሚገኙ 249 ቤቶችን ገንብቶ አጠናቀቅ
ጥር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኦቪድ ሪል እስቴት አራት ኪሎ ጥይት ቤት ተብሎ በሚታወቀው አከባቢ ኪንግስ ታወር በሚል እየገነባ ከሚገኙ... read more
በአዲስ አበባ ከተማ እየተስተዋለ ያለዉ የነዳጅ እጥረት ከዛሬ ጀምሮ እንደሚፈታ ተገለጸ
ባለፉት ቀናት በመዲናዋ ነዳጅ ማደያዎች ላይ የነዳጅ እጥረት በማጋጠሙ ረጃጅም ሰልፎች በየማደያዎች ተስተዉሏል።
ይህንን መነሻ በማድረግ መናኸሪያ ሬድዮ የአዲስ አበባ ንግድ... read more
የትራፊክ መጨናነቅን የሚቀርፍ የቻይና ፈጠራ
👉ተለዋዋጭ የመንገድ መስመሮች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የከተማ ትራፊክ መጨናነቅ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ትላልቅ ከተሞች ዋነኛ ፈተና ከሆኑት... read more
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በቀን 11/02/2017 ዓ/ም በጻፈው ደብዳቤ 11 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዳገዳቸው ይታወቃል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ 5ቱ ፓርቲዎች /የወላይታ ብሔራዊ ንቅናቄ፤ አዲስ ትውልድ ፓርቲ፤ የጋምቤላ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ፤ የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት እና አገው ለፍትህ... read more
በ80 ዓመት አዛውንት እናት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በእስራት ተቀጣ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ በ80 ዓመት አዛውንት ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ተከሳሽ በ10 ዓመት ፅኑ... read more
የአሜሪካ የኑክሌር ሚስጥር በዲጂታል ካርዶች አማካኝነት ለዓለም ተጋለጠ!
ሚያዚያ 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ባለፈው የፈረንጆች አመት ቤሊንግካት (Bellingcat) የተባለው የምርመራ ተቋም ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት የአሜሪካ አየር ሃይል አባላት... read more
ስኳር የያዙ እና ስኳር አልባ የሆኑ ለስላሳ መጠጦች ለጤና አደገኛ ናቸው ተባለ
ነሐሴ 17 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ ጥናት እንደተረጋገጠው ስኳር የያዙም ሆኑ ስኳር አልባ የሆኑ ለስላሳ መጠጦች ለጤና ከፍተኛ አደጋ ያመጣሉ... read more
በከተማዋ ላይ የታይሮይድ መድሃኒት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመሆኑ አሳስቦናል ሲሉ ተጠቃሚዎች ገለጹ
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለመናኸሪያ ሬዲዮ ቅሬታቸውን ያቀረቡት የእንቅርት መድሃኒት (ታይሮክሲን) ተጠቃሚ መድሃኒቱን የመንግስት መድሃኒት መሸጫ በሆነው ከነማ መደብር... read more
ምላሽ ይስጡ