ጥቅምት 19 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ተለያዩ የዓለማችን ሀገራት ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በሚያደጉበት ወቅት የአየር ላይ ጥበቃና አጃቢነት የሚያደርግላቸው የጦር ጄት፣ ኢትዮጵያ በቅርቡ በይፋ ተረክባ ወደ አየር ኃይሏ የተቀላቀለው ሱ-35 (Su-35) ሞዴል እንደሆነ ተገለጸ። በዓለም አቀፍ ደረጃ በከፍተኛ የውጊያ ብቃቱና አየር ላይ ተንቀሳቃሽነቱ በሚታወቀው በዚህ «ሱፐር ፍላንከር» (Super Flanker) የጦር አውሮፕላን አማካኝነት፣ የሩሲያው ፕሬዚዳንት በዓለም አቀፍ አየር ክልል በሚያደርጓቸው ስትራቴጂያዊ ጉዞዎች ሙሉ በሙሉ ታጥቀው ጥበቃ ከሚያደርጉላቸው አጃቢ ጄቶች መካከል ዋናው ነው።
ኢትዮጵያ ከሩሲያ የተረከበቻቸው እነዚህ የሱ-35 (Su-35S) 4++ ትውልድ የጦር ጄቶች፣ የሀገሪቱን አየር ክልል ከአስከፊ ጥቃቶች የመጠበቅና በቀጠናው አስተማማኝ የአየር የበላይነትን የማጎናጸፍ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ይታወቃል። ይህ አውሮፕላን የሩሲያ ቁጥር አንድ መሪን ደኅንነት ለመጠበቅ እስከመመደቡ ድረስ አስተማማኝና ዘመናዊ መሆኑ፣ ኢትዮጵያ የታጠቀችውን የጦር መሳሪያ የቴክኖሎጂ የበላይነትና የዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራት የሚያሳይ መሆኑ ተመልክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ