ሰኔ 11 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአለማችን ግዙፍ እና ውድ የሆኑ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን የሚመራው ባለሀብቱ ኢሎን ማስክ፣ ካለው እጅግ ግዙፍ ሀብት አንጻር ከሌሎች ቢሊየነሮች በተለየ ሁኔታ እጅግ በጣም ቀላል እና ልከኛ (minimalist) ህይወትን እንደሚመራ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።
በአሁኑ ወቅት በቴክሳስ ግዛት በሚገኘው የSpaceX የሳተላይት መሥሪያ ጣቢያ አቅራቢያ፣ ዋጋው 50 ሺህ ዶላር አካባቢ በሚገመት እጅግ አነስተኛ ተገጣጣሚ ቤት (Prefabricated tiny home) ውስጥ ዋና መኖሪያውን አድርጎ እንደሚኖር ተገልጿል። ይህ በኩሽና፣ መኝታ ቤትና መታጠቢያ ቤት ብቻ የተወሰነችው አነስተኛ ቤት ለዕለት ተዕለት ኑሮ የሚያስፈልጉ መሰረታዊ ነገሮችን ብቻ ያካተተች ስትሆን፣ ይህም የማስክን ከቅንጦት ይልቅ ለተግባራዊነትና ለሥራ ምቾት የሚሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት ያሳያል ነው የተባለው።
ይህ የአኗኗር ዘይቤ ለብዙዎች አስገራሚ የሆነው ማስክ ከዚህ ቀደም የነበሩትን በርካታ የቅንጦት ቪላዎችንና ንብረቶችን በሙሉ ከሸጠ በኋላ መሆኑ ሲሆን፣ ምክንያቱን ሲያስረዳም ቁሳዊ ሀብቶችን በመቀነስ ሙሉ ትኩረቱን በሥራው ላይ ብቻ ማድረግ ስለፈለገ እንደሆነ ተናግሯል። ሮኬቶችን ወደ ጠፈር ከመተኮስ ጀምሮ አዳዲስ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂዎችን እስከማልማት ድረስ ሌት ተቀን የሚለፋው ኢሎን ማስክ፣ ይህንን መሰል አነስተኛ ቤት መምረጡ በአለማችን እጅግ ባለጸጋ ከሆኑ ሰዎች መካከል ትልቅ መነጋገሪያና በአርአያነት የሚጠቀስ የአኗኗር ዘይቤ ሆኗል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ