መስከረም 06 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ) ሲንጋፖር ዜጎቿን ከስልክ ላይ ሳያቋርጡ አልባሳትና ዜናዎችን የመመልከት (ዶምስክሮሊንግ) አባዜ ለመታደግና የመጽሐፍ ንባብን ለማበረታታት አዲስ የገንዘብ ማበረታቻ መርሃ ግብር ጀምራለች። የበለፀገችው ከተማ በዚህ ወር ይፋ ባደረገችው የጨዋታ መልክ ባለው ስልቷ የዜጎቿን ትኩረት የመሰብሰብ፣ አመዛዝኖ የማሰብ እና የማስበብ አቅም ለማሳደግ አልማለች። በዚህ አሰራር መሰረት ዜጎች በቀንቢያንስ ለ15 ደቂቃ መጽሐፍ በማንበብ ለገንዘብ የሚለወጡ ነጥቦችን ያከማቻሉ። በዚህ የነጥብ አሰባሰብ መርሃ ግብር ተሳታፊዎች አንድ የሲንጋፖር ዶላር ለማግኘት በመንግሥት ድረ-ገጽ ላይ 50 የንባብ ክፍለ-ጊዜዎችን መመዝገብ አለባቸው። ለአንድ ጊዜ ለ15 ደቂቃ ወይም ከዚያ በላይ ላነበበ ሰው 20 ምናባዊ ሳንቲሞች የሚሰጡ ሲሆን፣ አንድ ዶላር ለማግኘት 1,000 ሳንቲሞች ያስፈልጋሉ። በአንድ ቀን ውስጥ አንድ የንባብ ክፍለ-ጊዜ ብቻ ነው የሚፈቀደው። ዓላማው በቀላሉ በሚከናወኑ ተደጋጋሚ ድርጊቶች ጠቃሚ ልማዶችን መገንባት እንደሆነ የመንግሥት አካላት ገልጸዋል። ሰዎችን በታክሲ ውስጥ፣ ከመተኛታቸው በፊት ወይም በምሳ ሰዓት በቀን ለ15 ደቂቃ ብቻ እንዲያነቡ ማበረታታት የመርሃ ግብሩ ዋነኛ መነሻ ነው። ከዚህ በተጨማሪም የመንግሥት አካላት ማህበራዊ ሚዲያዎች በወጣቶች ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ በቀን የሚጠቀሙበትን ጊዜ መገደብን ጨምሮ የተለያዩ አማራጮችን እያሰቡበት ይገኛሉ። የሲንጋፖር መንግሥት የዜጎቹን ባህሪ ለማስተካከል የገንዘብ ማበረታቻ ሲጠቀም የመጀመሪያው አይደለም። ቀደም ሲል ለጤና ትኩረት በሰጡ መርሃ ግብሮች የእግር ጉዞ ላደረጉ ሰዎች የሱፐርማርኬት ኩፖኖችን እና የእለት ተእለት የእርምጃ ግቦችን ላጠናቀቁ ሰዎች ሽልማቶችን ሲሰጥ ነበረ። የንባብ አቅምን በተመለከተ ስጋት ቢኖርም፣ የሲንጋፖር የ15 ዓመት ተማሪዎች እ.ኤ.አ. በ2025 በተካሄደው ዓለም አቀፍ የተማሪዎች ምዘና (PISA) ቻይናን እና ታይዋንን በመበለጥ በዓለም በንባብ አቅም አንደኛ ደረጃን ይዘዋል።
___
ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
ምላሽ ይስጡ