ነሐሴ 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዘርፉን የአምስት ዓመታት የልማትና የለውጥ ጉዞ የገመገመበትን እና የቀጣይ የልማት አቅጣጫዎችን የሚያስቀጥልበትን ሀገር አቀፍ ጉባኤ ለአራት ቀናት ሲያካሂድ መቆየቱ ይታወቃል። በዚህ ሀገር አቀፍ መድረክ ባለፉት አምስት ዓመታት በዘርፉ የተከናወኑ ዋና ዋና የልማት ሥራዎች በጥልቀት የተገመገሙ ሲሆን፣ የፓናል ውይይቶች መካሄዳቸውም ተገልጿል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ዴኤታ ነቢሃ መሀመድ በመርሃ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ በሚኒስቴሩ በኩል በተለያዩ ዘርፎች ለአምስት ዓመታት በተሠሩ ሥራዎች ለውጥ መፍጠር ተችሏል ብለዋል። በእነዚህ ዓመታት የአጭር ጊዜ የክህሎት ሥልጠና በስፋት መስጠት መቻሉን እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች የገበያ ትስስር መፍጠር መቻሉን ጠቅሰዋል። በማጠናቀቂያ መርሃ ግብሩም ከመላ ሀገሪቱ ለተውጣጡ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ተቋማት የሽልማት ሥነ ሥርዓት ተከናውኗል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ