ሰኔ 13 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቶዮታው ሊቀመንበር አኪዮ ቶዮዳ (Akio Toyoda) በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ውስጥ አነጋጋሪነታቸውን ቀጥለዋል። ሁሉም ሰው ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EVs) ብቻ ፊቱን እያዞረ መምጣቱ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረባቸው የገለጹት ሊቀመንበሩ፣ ባህላዊ የነዳጅ ሞተሮችን መደገፋቸውን በመቀጠላቸው “ብቸኝነት” እንደሚሰማቸው በግልጽ ተናግረዋል።
ከታዋቂው Carwow የመኪና መድረክ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ቶዮዳ ሲናገሩ፦ “ከሶስት ወይም ከአራት ዓመታት በፊት፣ ‘የሞተር ሽታ፣ ድምፅ እና ራሱ ሞተሩ ይማርከኛል’ ብዬ በግልጽ የተናገርኩት እኔ ብቻ ነበርኩ” ብለዋል።
በርካታ የመኪና አምራቾች ሙሉ በሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እያዞሩ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ቶዮታ ግን የተለየ መንገድ በመከተል ላይ ይገኛል። ኩባንያው እንደ ሌሎቹ ወደ አንድ አማራጭ ብቻ ከመሮጥ ይልቅ በሃይብሪድ፣ በሃይድሮጅን ቴክኖሎጂ፣ በባህላዊ የነዳጅ ሞተሮች (Combustion Engines) እንዲሁም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ በአንድነት ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል።
ሊቀመንበሩ አክለውም፣ ባህላዊ ሞተሮች አሁንም በገበያው ውስጥ የራሳቸው ትልቅ ቦታ እንዳላቸውና በሞተር ልማትና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ የብዙ ሺህ ሰራተኞችን የስራ ዕድል እንደሚታደጉ አስገንዝበዋል።
ይህ አነጋጋሪ አስተያየት የተሰጠው ቶዮታ የሙከራ ደረጃ ላይ ያሉ የሃይድሮጅን መኪኖቹን፣ በተለይም የ GR Yaris ሞዴልን በይፋ ባሳየበት በጃፓኑ የሱፐር ታይኪዩ (Super Taikyu) የጽናት እሽቅድምድም ውድድር ላይ መሆኑ ታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የኢራን ባለስልጣናት 997 የስታርሊንክ (Starlink) ሳተላይት መሣሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን እና 163 ሰዎችን ማሰራቸውን አወጁ!
ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢራን ከፍተኛ የመንግስት አካላት በተደረገው መጠነ ሰፊ ክትትል ከግንቦት እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም (እንደ አውሮፓውያኑ... read more
በጅቡቲ ድንበር ህይወታቸው የሚያልፍ አሽከርካሪዎችን አስክሬን ለማንሳት የሚጠየቀው ገንዘብ ከፍተኛ በመሆኑ ችግሩ አሳሳቢ ሆኗል ተባለ
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢትዮጵያ የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች እየደረሰባቸው ካለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ባለፈ ጠረፍ አካባቢ ያለው ከፍተኛ የሙቀት... read more
በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ
ግንቦት 4 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። በፎረሙ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፣... read more
ጁድ ቤሊንጋም ለሁለት ጨዋታ ቅጣት ተላልፎበታል
ማድሪድ ከሜዳቸው ውጪ በስታዲዮ ኤል ሳዳር ከኦሳሱና ጋር 1 አቻ በተለያዩበት ጨዋታ እንግሊዛዊው ድንቅ አማካኝ ጁድ ቤሊንጋም ጨዋታውን ሲመራ ለነበረው... read more
“ፎቶዬ አላማረኝም!” – ተፈላጊ ወንጀለኛ ለፖሊስ ‘ሰልፊ’ ልኮ ራሱን አሳልፎ ሰጠ
👉ወንጀለኛው በፖሊስ እየተፈለገ ፖሊስ የለጠፈውን ፎቶ ሲመለከት "ፎቶዬ አያምርም" ብሎ ሌላ የሰልፊ ፎቶ አንስቶ ለፖሊስ በመላኩ በቁጥጥር ስር ውሏል ነው... read more
የብራዚሏ ላም በአንድ ቀን 123 ሊትር ወተት በማምረት ታሪክ ሰራች
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በብራዚል የምትገኝ አንዲት ላም በአንድ ቀን ውስጥ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የወተት መጠን በማምረት የዓለም ክብረወሰን... read more
ጃፓን የደም አይነት የሌለው እና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰው ሰራሽ ደም ፈጠረች
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በናራ ሜዲካል ዩኒቨርሲቲ (Nara Medical University) በፕሮፌሰር ሂሮሚ ሳካይ (Prof. Hiromi Sakai) የሚመራ የጃፓን ተመራማሪዎች ቡድን... read more
አዲሱ ሰሌዳ ስራ ላይ ሲውል የተሽከርካሪ ስርቆት እንደማይኖር ተገለጸ
ሰኔ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አዲሱ ሰሌዳ ስራ ላይ ሲውል የተሽክርካሪ ስርቆት እንደማይኖር የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር አስታውቋል። ትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር ሚኒስትር... read more
ከግብፅና ከሱዳን ከሚነሱ ውዝግቦች በተጨማሪ የሀገር ውስጥ የውሃ ሀብት አስተዳደር የግጭት መንስኤ እንዳይሆን ሊሠራ እንደሚገባ ተገለጸ
ሐምሌ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ከሰሞኑ ባዘጋጀው በተፋሰስ ምክር ቤት ረቂቅ ደንብ ዙሪያ በተካሄደው የባለድርሻ አካላት የምክክር... read more
የፈረንጆች አዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ ርችት እንደሚተኮስ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት አስታወቀ
ታኅሳስ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የደህንነትና ልዩ ኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ዛሬ ታህሳስ 22 ቀን 2017... read more
ምላሽ ይስጡ