ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ማንቸስተር ዩናይትድ የቶተንሃሙን አምበል ክሪስቲያን ሮሜሮን ለማስፈረም የዝውውር ጥያቄ እያዘጋጀ መሆኑ ተዘግቧል።
የ28 ዓመቱ አርጀንቲናዊ ተከላካይ ቶተንሃም በፕሪሚየር ሊጉ ለሁለተኛ ተከታታይ ዓመት 17ኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁን ተከትሎ፣ በዚህ ክረምት ክለቡን ይለቃል ተብሎ በስፋት ይጠበቃል። አርጀንቲናዊው ጋዜጠኛ ጋስተን ኤዱል እንደዘገበው፤ ማንቸስተር ዩናይትድ ቀጣዩ የተጫዋቹ ማረፊያ ለመሆን ተስፋ በማድረግ ይፋዊ የዝውውር ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ ይገኛል።
ጊቭሚስፖርት (GiveMeSport) በበኩሉ፣ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ቶተንሃም ሮሜሮን አሁንም የቡድኑ ወሳኝ አካል አድርጎ ስለሚመለከተው በቀላሉ አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆኑን ገልጿል። የ2022 የዓለም ዋንጫ አሸናፊው ሮሜሮ፣ ክለቡ ቶተንሃም በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም እንኳ ራሱን በፕሪሚየር ሊጉ ካሉ ምርጥ የመሀል ተከላካዮች አንዱ ማድረግ በመቻሉ፣ ቶተንሃሞች ለዝውውሩ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን እንደሚጠይቁ ይገመታል።
የትራይባል ፉትቦል (Tribal Football) ዘጋቢው አሌክስ ሮበርትስ በበኩሉ፤ ሮሜሮ በቶተንሃም ያለው የኮንትራት ውል ማፍረሻ 50 ሚሊዮን ዩሮ መሆኑንና ይህንን ገንዘብ ለማቅረብ ዩናይትድ ዝግጁ መሆኑን ገልጾ፤ ተጫዋቹን ከአገሩ ልጅና ከቅርብ ጓደኛው ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ጋር የማጣመር ዕቅድ እንዳላቸው ዘግቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ለጎንደር ከተማ የልማት ስራ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሊካሔድ መሆኑ ተገለጸ
ታሪካዊቷን የጎንደር ከተማ የልማት ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችል የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ሚያዚያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ሊካሔድ መሆኑ የጎንደር ከተማ አሥተዳደር... read more
በቀሪዎቹ የክረምት ወራት ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚኖር ተገለጸ
ነሐሴ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ ባለፉት ሁለት የክረምት ወራት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ መደበኛና ከመደበኛ በላይ የሆነ... read more
የኢትዮጵያን ፓስፖርት ለማውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ የሌሎች ሃገራት ዜጎች ተገቢውን ቅጣት እያገኙ እንዳልሆነ ተገለጸ
ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተለያዩ ሀሰተኛ መረጃዎች የኢትዮጵያን ፓስፖርት ለማውጣት ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር የዋሉ የጎረቤት ሀገራት ዜጎች በፍርድ ቤት... read more
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እየተከተለው ያለው ጠበቅ ያለ አሰራር ፓርቲዎችን ለቀጣዩ ምርጫ የሚያጠናክር ነው ተባለ
እግዱ የተጣለባቸው ፓርቲዎች ግን ውሳኔው ተገቢነት እና ህጋዊ መሰረት የሌለው ነው ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያዊያን እንደ አገር በቅርቡ ከሚጠብቋቸው ትልልቅ ብሔራዊ ጉዳዮች መካከል... read more
የአዋዛ ስምምነት እንዲተገበር በተለያዩ አማራጮች ጫናዎችን ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
ነሐሴ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቅርቡ በቱርክሚስታን ከተማ አዋዛ የተደረገው ባህር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ጉባኤ የፀደቀው የአዋዛ ስምምነት በጂኦግራፊ አቀማመጥ... read more
ከቶብሩክ የባህር ዳርቻ አቅራቢያ 18 ስደተኞች ሞቱ
👉50 ያክሉት ደግሞ ጠፍተዋል ሲል IOM ገልጿል
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት (IOM) እንደገለጸው፣ ከሊቢያዋ ቶብሩክ የባህር... read more
የቤት ልማት ተደራሽነትን ለማስፋት የፋይናንስ አማራጭ ጥናቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ ተገለጸ
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቤት ልማት ተደራሽነትን ለማስፋት የፋይናንስ አማራጭ ጥናቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ የፖሊሲ... read more
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ፍቃድ እድሳትን በወቅቱ ለመጨረስ የሰዓት ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ
ታኅሳስ 09 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ከሃምሌ 01 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓ.ም... read more
የ5ሜጋ ባይት ሃርድ ድራይቭ በ1956 በአይቢኤም ሲጓጓዝ የሚያሳየው ምስል ቅርምትን ፈጥሯል
ሐምሌ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዛሬ በኪሳችን ከምንይዛቸው ጥቃቅን የኮምፒዩተር ማከማቻ መሳሪያዎች ጋር ሲነጻጸር፣ ከ60 ዓመታት በፊት የነበረው ቴክኖሎጂ ምን... read more
የውጭ ባንኮች በሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ የሚፈቅድ አዋጅ ጸደቀ
ታኅሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም(መናኸሪያ ሬዲዮ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በአካሄደው 11ኛ መደበኛ ስብሰባው የውጭ ባንኮች በሀገር ውስጥ ገብተው እንዲሰሩ... read more
ምላሽ ይስጡ