ነሐሴ 24 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በለንደን የሚገኘው የብሔራዊ የኒውሮሎጂ እና ኒውሮሰርጀሪ ሆስፒታል ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስቶች በዓለም የታሪክ የመጀመሪያ የሆነውን በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ የአንጎል ዕጢ የማስወገድ ቀዶ ሕክምና በስኬት ማከናወናቸውን ይፋ አድርገዋል። ይህ በዓይነቱ ልዩ የሆነው ቀዶ ሕክምና በሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ የላቀ የኢሜጂንግ እና የመምሪያ ቴክኖሎጂ በመታገዝ የሐንጎል ዕጢውን በትክክለኛነት ለማስወገድ ያስቻለ ሲሆን፣ በዕጢው ምክንያት የማየት አቅሙን አጥቶ የነበረውን ሕመምተኛ እይታ ሙሉ በሙሉ ለመመለስ አስችሏል። የሕክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ በ AI የታገዘ የቀዶ ሕክምና ስኬት በኒውሮሰርጀሪ ሴክተር አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ሲሆን፣ ለወደፊቱ ውስብስብ የአንጎል እና የነርቭ ቀዶ ሕክምናዎችን በበለጠ ጥራት እና ደህንነት ለማካሄድ ትልቅ መንገድ የሚከፍት ነው።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ