ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ዶክተር ብርሃኑ አበራ የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች የራሳቸው የሆነ ሂደት እንዳላቸው ገልጸው፤ እንደ ማሳያም ከቅድመ-ምልክት ጀምሮ በተደጋጋሚ እና በቁጥር በርከት ብለው የመሬት መፈራረስ የሚያስከትሉትን በማንሳት አብራርተዋል።
ተቋሙ የስነ-መሬት እንቅስቃሴዎችን በቋሚነት በመከታተልና በመመዝገብ ላይ እንደሚገኝም ዳይሬክተሩ አክለዋል። ተቋሙ የክትትልና የጥናት ስራዎቹን ውጤታማ ለማድረግ ከተለያዩ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝና ለአብነትም ከኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ፣ ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር አስማምሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የመመዝገብ አቅም ያላቸውና «ብሮድ ባንድ» በመባል የሚታወቁ ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ እነዚህ መሣሪያዎች በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚከሰቱና በሬክተር ስኬል ከ4.5 በላይ የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን በስፋት የመመዝገብ አቅም ያላቸው ናቸው ብለዋል። አብዛኞቹ መሣሪያዎች ውድ በመሆናቸው በዓለም አቀፍ ድጋፍና በጋራ ትብብር የተገኙ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
ሆኖም ግን የኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት ሰፊ በመሆኑና የመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት ያለበት ሁኔታ በመኖሩ፣ በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎችና ተቋማት ቁጥር አሁንም በቂ አለመሆኑን ዶክተር ብርሃኑ ተናግረዋል።
በርካታ ተቋማትና በቂ የስነ-መሬት ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ያለው የሰው ኃይል እጥረት ለዘርፉ ትልቅ ፈተና ሆኖ መቀጠሉ ተመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በሱዳን ዳርፉር ክልል በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ከ1,000 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሱዳን ምዕራባዊ ዳርፉር ክልል ውስጥ በመራ ተራሮች አካባቢ ታራሲን በተባለች መንደር ላይ በደረሰ ከባድ የመሬት... read more
የህዝብ ቁጥር ማሻቀብና የጤና ዘርፉ ተግዳሮት
https://youtu.be/fWAa-xCiJDk
read more
በትግራይ ክልል በተካሄደው የ8ተኛ ክልል አቀፍ ፈተና ይሳተፋሉ ተብሎ ከተጠበቀው 50 በመቶ የሚሆኑት አለመሳተፋቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በትግራይ ክልል በጦርነት ምክንያት ተማሪዎች በመደበኛ የትምህርት ሰዓት እየተማሩ አለመሆኑ እና የፈተና ሰዓትም ጠብቀዉ እየተፈተኑ... read more
አውሮፕላኖች ያለ መስኮት?
የአየር ጉዞን የሚቀይር አዲስ ጽንሰ-ሀሳብ
መስከረም 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የአውሮፓ የዲዛይን ድርጅቶች አየር መንገዱን ሙሉ ለሙሉ ሊቀይር የሚችል አዲስ... read more
የኢትዮጵያ ፖሊስ ጥናት ኢንስቲትዩት ባለፉት 2 አመታት ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር የተገናኘ ጥናት አላካሄድኩም አለ
ጥር 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ተቋማት በተለያዩ ጉዳዮች የሚያወጧቸዉን ሪፖርቶች ፖሊሲዎችን ለመፈተሽና ለፖሊሲ ግብዓትነት እየተጠቀምኩባቸዉ ነዉ ሲል የኢትዮጵያ ፖሊሰ ጥናት... read more
የኃይል ሥርቆት በፈጸሙ 111 ደንበኞች ላይ ክስ ተመሠረተ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሸገር ሪጅን በ8 ወራት ውስጥ አንድ መቶ አስራ አንድ ደንበኞች የኃይል ሥርቆት መፈጸማቸውን ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ እና... read more
ፓርቲው ከተሰረዘ በኋላ የሚያደረጋቸው የፖለቲካ እንቅስቃሴዎች ኢ-ህገ መንግስታዊ እንደሚሆን ተገለጸ
አንድ ፓርቲ ከምርጫ ቦርድ ህጋዊ እውቅናውን ካጣ በኋላ የሚያደርገው ማንኛውም እንቅስቃሴ ኢ-ህገ መንግስታዊ ይሆናል ሲሉ የህግና የፌዴራሊዚም ባለሙያዎች ለመናኸሪያ ሬዲዮ... read more
እግሯን በእንቅስቃሴ ላይ ሳለች በተቀበረ ቦምብ ያጣችው ዝሆን ሰው ሠራሽ እግር ተገጠመላት
መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በታይላንድ የምትገኘው ሞሻ የተባለችው እስያዊት ዝሆን፣ ገና በህፃንነቷ እንቅስቃሴ ላይ በነበረችበት ጊዜ በተቀበረ ቦምብ... read more
ማንበብና መጻፍን በ18 ዓመቱ የተማሩት ጄሰን አርዴይ የካምብሪጅ ዩኒቨርሲቲ ታናሽ ጥቁር ፕሮፌሰር ሆኑ
መስከረም 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአንዲት እናት ድጋፍና በራሳቸው ጽናት፣ የልጅነት የዕድገት መዘግየትን ተቋቁመው ትምህርታቸውን የተከታተሉት ጄሰን አርዴይ፣ በዓለማችን እጅግ... read more
ኢራንን የሚደግፉ ወዮላቸው – ትራምፕ
👉
https://youtu.be/e5Nvw7On-xU
በትዕግስቱ በቀለ
read more
ምላሽ ይስጡ