ሐምሌ 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በደቡብ አሜሪካዊቷ ሀገር ኢኳዶር፣ ባባሆዮ በተባለች ከተማ የሚገኘው ማርቲን ኢካዛ ሆስፒታል ሰኔ 9 ቀን 2015 ዓ.ም አንድ ያልተለመደና አሳዛኝ ክስተት አስተናግዷል። እድሜያቸው 76 የሆኑት አያት ቤላ ሞንቶያ በጽኑ ታመው ወደ ሆስፒታሉ ከገቡ በኋላ፣ በወቅቱ በነበሩት ሀኪሞች “ህይወታቸው አልፏል” የሚል ኦፊሴላዊ የሞት ምስክር ወረቀት ተሰጣቸው።
የሞታቸውን ዜና የሰሙት ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው የቀብር ስነ-ስርዓታቸውን ለመፈጸም አስከሬኑን በሬሳ ሳጥን ውስጥ አድርገው ወደ ቀብር ማዘጋጃ ቤት ወሰዱት። ለሰዓታት ያህል የሀዘን ስነ-ስርዓት ሲካሄድ ቆይቶ፣ ከቀብሩ በፊት የሬሳ ሳጥኑን ከፍተው ልብሳቸውን ለመቀየር ሲዘጋጁ ግን ያልተጠበቀ ድንጋጤ ተከሰተ።
የአያት ቤላ ሞንቶያ ልጅ የሆነው ጊልበርት ባልቤራን እንደተናገረው፣ ከሰዓታት ሀዘን በኋላ ከሳጥኑ ውስጥ ደካማ ማንኳኳትና የመተንፈስ ድምፅ መሰማት ጀመረ። ቤተሰቦቻቸው ሳጥኑን በፍጥነት ሲከፍቱ፣ አያት በህይወት ሆነው ግራ እጃቸውን በማንቀሳቀስና አፋቸውን በመክፈት አየር ለማግኘት ሲታገሉ ተመለከቱ።
ይህ ክስተት በወቅቱ በሆስፒታሉ ባለሙያዎች ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥን የፈጠረ ሲሆን፣ አያት ወዲያውኑ ወደ ጽኑ ህክምና ክፍል ተመልሰው ኦክስጅን እንዲያገኙ ተደረገ። የህክምና ባለሙያዎች እንደሚሉት አያት የካታሌፕሲ (Catalepsy) ተብሎ በሚጠራ የነርቭ መታወክ ሁኔታ ውስጥ ወድቀው የነበረ ሲሆን፣ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያለ ሰው የልብ ምቱና የመተንፈስ ፍጥነቱ እጅግ አነስተኛ ከመሆኑ የተነሳ እንደ ሞተ ሰው ተቆጥሮ በስህተት ሊደመደም ይችላል።
ክስተቱን ተከተሎ የኢኳዶር ጤና ሚኒስቴር አያት በስህተት ሞተዋል ተብለው የሞት ምስክር ወረቀት እንዴት ሊሰጣቸው እንደቻለ ለማጣራት ብሔራዊ ኮሚቴ አቋቁሞ ምርመራ ጀምሮ ነበር።
ሆኖም ግን፣ አያት ቤላ ሞንቶያ በጽኑ ህክምና ክፍል ውስጥ ለአንድ ሳምንት ያህል ከቆዩ በኋላ ሰኔ 16 ቀን 2015 ዓ.ም በተከሰተ የstroke ችግር ምክንያት ህይወታቸው ማለፉ በይፋ ተረጋግጧል።
የመጀመሪያው አጋጣሚ ግን በዓለም አቀፍ ደረጃ በህክምና ታሪክ ውስጥ እጅግ አስገራሚና በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ መነጋገሪያ ከሆኑ ክስተቶች አንዱ ሆኖ ተመዝግቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በመዲናዋ 10 የሚሆኑ ፏፏቴዎች ቢኖሩም ለቱሪስት ሳቢ ለማድረግ ጥናት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
በከተማዋ ባሉት ፏፏቴዎች የቱሪስቶችን ቀልብ የሚስቡ አድርጎ ለማስቀጠል የማልማት ስራ እየተሰራ እንደሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት... read more
በ274ቱ የኅብረት ሥራ ማኅበራት ሥጋ ቤቶች ለአዲስ ዓመት የአንድ ኪሎ ሥጋ ዋጋ 1,200 ብር እንዲሆን ከሥጋ ቤቶቹ ጋር ስምምነት መደረጉ ተገለጸ
ነሐሴ 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ኅብረት ሥራ ኮሚሽን በአዲስ ዓመት ከሥጋ አቅርቦትና ዋጋ ጋር በተያያዘ ሸማቹ ኅብረተሰብ እንዳይቸገር... read more
ኢሬቻን ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነጻ በሆነ መልኩ የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ብቻ ማክበር እንደሚገባ ተገለጸ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ዘንድሮም በዓሉ በሚከበርባቸው ሁሉም አከባቢዎች በደማቅ ሁኔታ ለማክበር ቅድመ በቂ... read more
አሜሪካና ቻይና ቲክቶክን ተከትሎ በምን ጉዳዮች ላይ ተስማሙ?
መስከረም 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካና የቻይና መንግስታት በቻይናው ኩባንያ ByteDance ስር ባለው ታዋቂው የቪዲዮ መጋሪያ መተግበሪያ ቲክቶክ ዙሪያ... read more
የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን የጎበኙ የውጭ አገር ቱሪስቶች ቁጥር በእጥፍ ጨምሯል ተባለ
የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክን ባለፉት ዘጠኝ ወራት የጎበኙ የውጭ አገር ቱሪስቶች ቁጥር ከቀደመው በእጥፍ መጨመሩን የፓርኩ ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ብሄራዊ ፓርኩንና... read more
በዘንድሮ በጀት ዓመት ህገ ወጥ የመሬት ወረራ 69 በመቶ መቀነሱ ተገለጸ
ሰኔ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማሰከበር ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸሙን በዛሬው ዕለት ገምግሟል። በዘንድሮው... read more
ኖቲንጋም ፎረስት ሊያም ዴላፕን ለማስፈረም መቃረቡ ተሰማ
ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የለንደኑ ክለብ ቼልሲ እና ኖቲንግሃም ፎረስት በ23 ዓመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ሊያም ዴላፕ ዝውውር ዙሪያ ሙሉ... read more
የጫት ምርት በህገ ወጥ መንገድ ለመውጣት ተጋላጭ መሆኑ ጥራቱ ላይ ችግር ፈጥሯል ተባለ
ወደ ተለያዩ ሀገራት አንዳንድ ምርቶች ሲላኩ በጥራት መጓደል እንዲሁም በህገወጥ ግብይት ምክንያት በሚፈለገው ልክ ገቢ እንዳይገኝ ተግዳሮት መሆኑ ይገለፃል፡፡
ኢትዮጵያ ወደ... read more
ያልተጠበቀው ሆነ፤የሃማስ መሪው እና ቤንያሚን ኔታንያሁ ተጨባበጡ
ቴል አቪቭ በጋዛ ሃማስ ላይ የምታደርገውን ጦርነት ለማቆም እና እስረኞችን ለመፍታት እንዲሁም፣ ታጣቂ ቡድኑ ታጋቾችን ለመልቀቅ፣ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ... read more
እስራኤል የአየር መከላከያ ጋሻዋን ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ላከች
ግንቦት 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) እስራኤል በቴክኖሎጂው ዓለም እጅግ ዘመናዊ እና ውጤታማ እንደሆነ የሚነገርለትን የ"አይረን ዶም" (Iron Dome) ሚሳይል መከላከያ... read more
ምላሽ ይስጡ