ሐምሌ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢንሹራንስ ኢንስቲትዩት ለትራፊክ ደህንነት (IIHS) ይፋ የተደረገ አዲስ ጥናት እንደሚያመለክተው፣ ዌይሞ (Waymo) የተሰኙት አሽከርካሪ አልባ ታክሲዎች ከሰው አሽከርካሪዎች ጋር ሲነጻጸሩ በከፍተኛ ደረጃ አስተማማኝና ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆናቸው ተረጋገጠ። ሮቦታክሲዎቹ ከ50 ሚሊዮን ማይል በላይ በሸፈነው ጉዞ ባስመዘገቡት የደህንነት መረጃ መሠረት፣ ለፖሊስ ሪፖርት የሚደረጉ የትራፊክ አደጋዎችን የመቀነስ ከፍተኛ ብቃት አሳይተዋል።
በጥናቱ ግኝት መሠረት አሽከርካሪ አልባ ታክሲዎቹ በሰው ከሚነዱ ተሽከርካሪዎች ጋር ሲነጻጸሩ በ68% አነስተኛ አደጋ አስመዝግበዋል። የሰው አሽከርካሪዎች በየአንድ ሚሊዮን ማይል 4.06 አደጋዎችን የሚያስመዘግቡ ሲሆን፣ የዌይሞ ታክሲዎች ግን ይህንን ቁጥር ወደ 1.28 ብቻ ዝቅ አድርገውታል። ከዚህ በተጨማሪም በዌይሞ ተሽከርካሪዎች የሚከሰቱት አደጋዎች አነስተኛ ጉዳት የሚያደርሱ ናቸው ተብሏል።
ይህ ጥናት በፊኒክስ፣ ሳን ፍራንሲስኮ እና ሎስ አንጀለስ ከተሞች የተካሄደ ሲሆን፣ በነዚህ ቦታዎች ዌይሞ ከፍተኛ ብቃት አሳይቷል። ሆኖም ግን በኦስቲን ከተማ የተወሰደው የናሙና መጠን በጣም አነስተኛ በመሆኑ ከተሽከርካሪዎቹ አፈጻጸም አንጻር ከሰው አሽከርካሪዎች በጥቂቱ ዝቅ ብሎ ተመዝግቧል።
ተመራማሪዎቹ ንጽጽሩ ፍትሃዊ እና ትክክለኛ እንዲሆን ለማድረግ የፍጥነት መንገድ (ሀይዌይ) መረጃዎችን እና ጥቃቅን የጭረት አደጋዎችን ከስሌቱ ውጭ አድርገዋል። ምክንያቱም ዌይሞ የሚያገለግለው በከተማ ውስጥ መንገዶች ላይ ብቻ ከመሆኑም በላይ ማንኛውንም ጥቃቅን ግጭት በቴክኖሎጂ መዝግቦ ሪፖርት ያደርጋል፤ በአንጻሩ የሰው አሽከርካሪዎች አብዛኛውን ጊዜ ትልልቅ አደጋዎችን ብቻ ሪፖርት ያደርጋሉ ተብሏል።
የ IIHS ተመራማሪዎች የተገኘው ውጤት በጣም አበረታች መሆኑን ቢገልጹም፣ ስለ ሮቦታክሲዎች ደህንነት ሙሉ በሙሉና ሰፊ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ አሁንም ተጨማሪ የመንገድ ላይ መረጃዎች ያስፈልጋሉ ሲሉ አሳስበዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ቻይና እና ኢትዮጵያን በህክምና ዘርፉ በጥልቀት ማገናኘት የሚቻልበት መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
ነሐሴ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በመርሀ ግብሩ ላይ ጥሪ የተደረገላቸው አካላት የተገኙ ሲሆን የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀስላሴ፤ የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ... read more
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋፋት ንቅናቄ ማስጀመሩን ይፋ አደረገ
ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ “አካታች የባንክ አገልግሎት ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል፤ ከሰኔ 2018 ዓ.ም እስከ መጋቢት... read more
የበጀት ውስንነትና የጸጥታ ችግር ለሰባተኛው አገራዊ ምርጫ በሚፈለገው ልክ እንዳንቀሳቀስ አድርጎናል ሲሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ገለጹ
መጋቢት 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሌላ በኩል አስቻይ ሁኔታ ባለባቸው አካባቢዎች ማህበረሰቡን ለማንቃት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ቪዥን ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ... read more
ኢትዮጵያ በግጭት አካባቢ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጥበቃ እንዲደረግ የሚያዘውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንጋጌ እንድትቀበል ግፊት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በግጭት አካባቢ ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጥበቃ እንዲደረግ የሚያዘውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ድንጋጌ እንድትቀበል ግፊት እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር... read more
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ አሽከርካሪዎች የሚያደርጉት የታሪፍ ማሻሻያ ሕገ-ወጥ መሆኑ ተገለፀ
ሚያዚያ 29 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሰሞኑ የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ፣ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ እስካሁን ምንም ዓይነት ውሳኔ... read more
የብሬንትፎርዱ ብሪያን ምቤሙ እና የስፖርቲንግ ሊዝበኑ ሩበን አሞሪም የወሩ ምርጥ ተብለው ተመረጡ
ጥቅምት 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በፕሪሚየር ሊግ የውድድር ወርኅ ጥቅምት ምርጥ ተጫዋቾች እና አሰልጣኞች መመረጣቸው ታውቋል። የብሬንትፎርዱ ክንፍ አጥቂ ብሪያን ምቤሙ... read more
አጼ ቴዎድሮስ ይጠቀሙት የነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ለጨረታ ቀረበ
መስከረም 04 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ)በ1868 ዓ.ም. በመቅደላ ዘመቻ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎንደር አካባቢ እንደተዘረፈ የሚነገርለት አጼ ቴዎድሮስ ይጠቀሙት የነበረ መጽሐፍ ቅዱስ... read more
የአሜሪካው አፓቺ የውጊያ ሄሊኮፕተር በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ አቅራቢያ ተከሰከሰች
ሰኔ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ አቅራቢያ ከፍተኛ ወታደራዊ ስምሪት ላይ የነበረች የአሜሪካ ጦር ኃይል ኤኤች-64 አፓቺ (AH-64 Apache)... read more
መርዛማ ብረቶችን በመመገብ ንፁህ ወርቅ የሚያመነጭ ባክቴሪያ ተገኘ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሳይንቲስቶች መርዛማ ብረቶችን ከተመገበ በኋላ ንፁህ ወርቅ የማምረት ችሎታ ያለው ባክቴሪያ መለየታቸውን አስታወቁ። ይህ ግኝት በወርቅ... read more
ምላሽ ይስጡ