ሐምሌ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃለ-መጠይቅ፣ በዮርዳኖስ በሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎች ላይ የተቃጣውን ያልተጠበቀ የኢራን የባሊስቲክ ሚሳይል ጥቃት በመኮነን አሜሪካ እጅግ በሐይል የተሞላ ምላሽ እንደምትሰጥና ኢራንን «አደብ እንደሚያስተምሯት» አስታወቁ።
ፕሬዚዳንቱ በሰጡት ጠንካራ መግለጫ፣ የአሜሪካ አየር መከላከያ ኃይሎች የተኮሱትን ሚሳይሎች ለማከሸፍ የነበራቸው ጊዜ ጥቂት ደቂቃዎች ብቻ እንደነበረ ገልጸው፣ የጦር ኃይሎቹ በቅጽበት ባደረጉት ቅንጅት ሚሳይሎቹን ሙሉ በሙሉ አየር ላይ ማክሸፍ መቻላቸውን አደንቀዋል።
በተጨማሪም ትራምፕ ሌሊቱን ከአሜሪካ እና ከሳዑዲ ዓረቢያ ጋር በመቀናጀት በኢራቅ በሚገኙ የኢራን ድጋፍ በሚደረግላቸው የሺዓ ታጣቂዎች ላይ የተፈጸመው የአየር ጥቃት ከኢራቅ መንግሥት ጋር በሙሉ ስምምነት የተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ