ሰኔ 13 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቶዮታው ሊቀመንበር አኪዮ ቶዮዳ (Akio Toyoda) በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው ውስጥ አነጋጋሪነታቸውን ቀጥለዋል። ሁሉም ሰው ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EVs) ብቻ ፊቱን እያዞረ መምጣቱ ትልቅ ስጋት እንደፈጠረባቸው የገለጹት ሊቀመንበሩ፣ ባህላዊ የነዳጅ ሞተሮችን መደገፋቸውን በመቀጠላቸው “ብቸኝነት” እንደሚሰማቸው በግልጽ ተናግረዋል።
ከታዋቂው Carwow የመኪና መድረክ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ቶዮዳ ሲናገሩ፦ “ከሶስት ወይም ከአራት ዓመታት በፊት፣ ‘የሞተር ሽታ፣ ድምፅ እና ራሱ ሞተሩ ይማርከኛል’ ብዬ በግልጽ የተናገርኩት እኔ ብቻ ነበርኩ” ብለዋል።
በርካታ የመኪና አምራቾች ሙሉ በሙሉ ትኩረታቸውን ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች እያዞሩ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ቶዮታ ግን የተለየ መንገድ በመከተል ላይ ይገኛል። ኩባንያው እንደ ሌሎቹ ወደ አንድ አማራጭ ብቻ ከመሮጥ ይልቅ በሃይብሪድ፣ በሃይድሮጅን ቴክኖሎጂ፣ በባህላዊ የነዳጅ ሞተሮች (Combustion Engines) እንዲሁም በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ላይ በአንድነት ኢንቨስት እያደረገ ይገኛል።
ሊቀመንበሩ አክለውም፣ ባህላዊ ሞተሮች አሁንም በገበያው ውስጥ የራሳቸው ትልቅ ቦታ እንዳላቸውና በሞተር ልማትና ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ የተሰማሩ የብዙ ሺህ ሰራተኞችን የስራ ዕድል እንደሚታደጉ አስገንዝበዋል።
ይህ አነጋጋሪ አስተያየት የተሰጠው ቶዮታ የሙከራ ደረጃ ላይ ያሉ የሃይድሮጅን መኪኖቹን፣ በተለይም የ GR Yaris ሞዴልን በይፋ ባሳየበት በጃፓኑ የሱፐር ታይኪዩ (Super Taikyu) የጽናት እሽቅድምድም ውድድር ላይ መሆኑ ታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናና ብልሹ አሰራርን ማስቀረት የሚያስችል ነው ተባለ
ከሰሞኑን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን እንዲጎበኙት ተደርጓል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በእቅድ... read more
ኤሎን ማስክ በትራምፕ ሪፐብሊካን “ትልቅ፣ ቆንጆ ሂሳብ” ላይ ትችታቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል
ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የስፔስኤክስ እና ቴስላ ዋና ስራ አስፈፃሚ ኤሎን ማስክ በትራምፕ ሪፐብሊካን አስተዳደር የቀረበውን "ትልቅ፣ ቆንጆ ሂሳብ"("big,... read more
ኢሰመኮ የዋና ኮሚሽነር ዕጩ ጥቆማ ማሰባሰብ መጀመሩን አስታወቀ
ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በፌዴራል ሕገ መንግሥቱ መሠረት ነጻ የፌዴራል መንግሥት አካል ሆኖ በአዋጅ... read more
የመንገድ ደህንነት ጥራትን የሚያስገድድ አዲስ ዘመናዊ አሰራር ይፋ ተደረገ
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የመንገድ ላይ አደጋዎችን ለመቀነስ ወሳኝ እርምጃ ነው የተባለ ሲሆን፣ ጥራት እና ደረጃ የወጣላቸው የፍጥነት መቆጣጠሪያዎች፣ የደህንነት... read more
በየመን ዋና ከተማ ላይ የተፈጸመው የእስራኤል የአየር ጥቃት የሁቲ ከፍተኛ አመራሮችን ገድሏል ተባለ
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የእስራኤል ጦር በየመን ዋና ከተማ በሆነችው ሳና ላይ ባደረሰው የአየር ጥቃት የኢራን ደጋፊ የሆነውን የሁቲ ቡድን... read more
በክልሎች የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለቀጣይ ምርጫ ያላቸው ዝግጅት አነስተኛ መሆኑን ፓርቲዎች ገለፁ
የተለያዩ የክልል ፓርቲዎች በግጭት፣ በበጀት እጥረት እና በውስጥ የአደረጃጀት ችግር ምክንያት የምርጫ ዝግጅታቸው ዝቅተኛ መሆኑን ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡
ጠንካራ አደረጃጀት መመስረት እና... read more
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጠናከር ማስቻሉ ተገለጸ
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የአገርን የደን ሽፋን መጠን በማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን... read more
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ከታህሳስ ወር ጀምሮ 200ሺሕ የሶሪያ ስደተኞች ከቱርክ ወደ አገራቸው መመለሳቸውን አስታወቁ
የቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በታህሳስ ወር የቀድሞ የሶሪያ ፕሬዝዳንት ባሻር አል አሳድ ከስልጣን ከተወገዱ በኋላ፣ 200ሺሕ የሶሪያ ስደተኞች ከቱርክ... read more
የሽንት ቤት ወረቀት ለማግኘት ማስታወቂያ መመልከት ግዴታ ሆነ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በቻይና አንዳንድ የሕዝብ መጸዳጃ ቤቶች፣ የሽንት ቤት ወረቀትን ለመስጠት ቅድመ ሁኔታ ያስቀመጠ አዲስ ሥርዓት መዘርጋታቸው... read more
በፈረንሳይ፣ ቁራዎች ጽዳት ሰራተኛ ሆኑ
መስከረም 08 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በምዕራብ ፈረንሳይ የሚገኘው ታዋቂው የ"ፑይ ዱ ፉ" የመዝናኛ መናፈሻ፣ ልዩ የሆነ የጽዳት መርሃ ግብር በመጀመሩ የመናፈሻው... read more
ምላሽ ይስጡ