ነሐሴ 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ተቋም ዳይሬክተር ዶክተር ብርሃኑ አበራ የሚከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች የራሳቸው የሆነ ሂደት እንዳላቸው ገልጸው፤ እንደ ማሳያም ከቅድመ-ምልክት ጀምሮ በተደጋጋሚ እና በቁጥር በርከት ብለው የመሬት መፈራረስ የሚያስከትሉትን በማንሳት አብራርተዋል።
ተቋሙ የስነ-መሬት እንቅስቃሴዎችን በቋሚነት በመከታተልና በመመዝገብ ላይ እንደሚገኝም ዳይሬክተሩ አክለዋል። ተቋሙ የክትትልና የጥናት ስራዎቹን ውጤታማ ለማድረግ ከተለያዩ ሀገር በቀልና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በትብብር እየሰራ እንደሚገኝና ለአብነትም ከኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ፣ ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር አስማምሮ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የመመዝገብ አቅም ያላቸውና «ብሮድ ባንድ» በመባል የሚታወቁ ዘመናዊ መሣሪያዎችን በመጠቀም ላይ እንደሚገኙ የገለጹት ዳይሬክተሩ፤ እነዚህ መሣሪያዎች በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚከሰቱና በሬክተር ስኬል ከ4.5 በላይ የሆኑ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን በስፋት የመመዝገብ አቅም ያላቸው ናቸው ብለዋል። አብዛኞቹ መሣሪያዎች ውድ በመሆናቸው በዓለም አቀፍ ድጋፍና በጋራ ትብብር የተገኙ መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።
ሆኖም ግን የኢትዮጵያ የቆዳ ስፋት ሰፊ በመሆኑና የመሬት መንቀጥቀጥ ስጋት ያለበት ሁኔታ በመኖሩ፣ በዘርፉ የሚሰሩ ባለሙያዎችና ተቋማት ቁጥር አሁንም በቂ አለመሆኑን ዶክተር ብርሃኑ ተናግረዋል።
በርካታ ተቋማትና በቂ የስነ-መሬት ባለሙያዎች የሚያስፈልጉ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ያለው የሰው ኃይል እጥረት ለዘርፉ ትልቅ ፈተና ሆኖ መቀጠሉ ተመላክቷል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ከሰል የማክሰል ሂደቱ በሳይንሳዊ መልኩ ባለመደገፉ ተፈጥሯዊ የአደጋ ስጋቶች እየጨመሩ መሆኑ ተገለጸ
ኢትዮጵያ የከሰል ምርትን በስፋት ከሚጠቀሙ 5 ሀገራት አንዱዋ ስትሆን ምርቱን ለአለም አቀፍ ገበያ በከፍተኛ ደረጃ በማቅረብ የሚታወቁ 5 ሀገራት እንዳሉም... read more
ብቁ ያልሆኑ ዜጎች ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት እየተላኩ በመሆኑ ለስቃይ እየተዳረጉ ነው ተባለ
በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ብቁ ያልሆኑ ዜጎች እየተላኩ በመሆኑ ለስቃይ መዳረጋቸውን የፌደራል የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ጥናት ገለጸ።
ይህንን በተመለከተ የወጣው... read more
በበቆጂ አቅራቢያ በሚገኘው የጋለማ ደን የተነሳዉን እሳት ለማጥፋት መሳሪያ ቢጠየቅም ማግኘት አልተቻለም ተባለ
ለአንድ ሳምንት ያህል በአርሲ የሚገኘው የጋለማ ደን በእሳት ውስጥ እንደሚገኝ ያስታወቀው የአርሲ ተራራሮች ብሄራዊ ፓርክ ነው፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የፓርኩ ሃላፊ... read more
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የደረሱ ሰብሎችን እንዳይጎዳ በጊዜ ምርት ለመሰበሰብ ቅደመ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ክልሎች ገለጹ
ጥቅምት 10 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) አልፎ አልፎ የሚከሰተው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የደረሱ ሰብሎችን እንዳይጎዳ ሁሉን የህብረተሰብ ክፍሎች ያሳተፈ የምርት መሰበሰብ... read more
♻️ስርቆት የፈጸሙ ግለሰቦች ተይዘዋል
👉የቃሉ ወረዳ ፓሊስ ጽ/ቤት ከኮምቦልቻ ቁጥር 2 እስከ ኮምቦልቻ ቁጥር 1 በተዘረጋ 132 ኪሎ ቮልት ተሸካሚ የኤሌክትሪክ ታወር ላይ ስርቆት... read more
ኢትዮ ቴሌኮም በጅማ ከተማ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን ለማፋጠን የሚያስችል የስማርት ሲቲ ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመ
ኢትዮ ቴሌኮም ከጅማ ከተማ አስተዳደር ጋር በከተማዋ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያደርግ የስማርት ሲቲ “ስማርት ጅማ” ፕሮጀክትን ለመተግበር የሚያስችል... read more
የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶችን የማጠናከሪያ ትምህርት ከመስጠት ባለፈ በትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን መፈተሸ ይገባል ተባለ
ሐምሌ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ከሆነ በኋላ ምንም ተማሪ ለማያሳልፉ 700 ያህል... read more
የውጊያ ጄት በትምህርት ቤት ውስጥ ተከስክሶ ቢያንስ 19 ተማሪዎች ሲሞቱ ከ50 በላይ የሚሆኑት መቁሰላቸው ተገለጸ
👉የብሔራዊ ሃዘን ቀን ታውጇልም ተብሏል
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በባንግላዲሽ ዋና ከተማ ዳካ በሚገኝ አንድ የኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ የባንግላዲሽ አየር... read more
በአፋር ክልል ፈንታሌ አካባቢ ተገኘ ስለተባለው የሚቴን ጋዝ ጥናት የሚያደርግ የባለሙያ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩ ተገለጸ
ኢሮፕያን ሳተላይት ባወጣው መረጃ በፈንታሌ ወረዳ ከወራት በፊት ሲከሰት የነበረውን የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ባልተለመደ መልኩ ሚቴን የተሰኘ የተፈጥሮ ጋዝ መገኘቱን... read more
የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን በከተማዋ 27 የትራፊክ መብራት መጋጠሚያዎች ላይ በጸሀይ የሚሰራ የሀይል አቅርቦት መኖሩን አስታወቀ
ጥር 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን የከተማዋን የትራፊክ መብራቶች ባልተቆራረጠ መልኩ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማድረግ 27 የትራፊክ... read more
ምላሽ ይስጡ