ሰኔ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሊቨርፑል በዚህ ክረምት የተከላካይ መስመሩን ማጠናከር ዋነኛ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ አድርጎ ወደ ዝውውር ገበያው ለመግባት መዘጋጀቱ ተዘግቧል። በክለቡ የግራ ተከላካይ መስመር ላይ ሚሎስ ኬርኬዝ እና ኮስታስ ሲሚካስ በመኖራቸው ቦታው አስተማማኝ ቢሆንም፤ በመሀል ተከላካይ ክፍል ግን ያለው አማራጭ አናሳ ሆኗል። በተለይም የኢብራሂማ ኮናቴ ክለቡን ለቆ መውጣት፣ እንዲሁም የቪርጅል ቫን ዳይክ እና ጆ ጎሜዝ ውል ወደ መጨረሻው ዓመት መግባቱ ሊቨርፑልን ልምድ ላላቸው ተከላካዮች እጥረት ዳርጎታል። ምንም እንኳን ክለቡ ወጣቱን ጄርሚ ዣኬን ከሬኔ ማስፈረም ቢችልም፣ እንዲሁም ጆቫኒ ሌኦኒ ከከባድ የጉልበት ጉዳት ቢያገግምም፤ ሊቨርፑል ለረጅም እና ለአጭር ጊዜ የሚጠቅመውን አስተማማኝ ተከላካይ ለማግኘት የኮከቦችን ዝርዝር አዘጋጅቷል።
ሊቨርፑል በዝርዝሩ ቀዳሚ ያደረገው በአውሮፓ በስፋት ከሚፈለጉ ተከላካዮች አንዱ የሆነውን የስፖርቲንግ ሊዝበኑን ጎንካሎ ኢናሲዮን ነው። ክለቡ ኳስን ከኋላ መስርቶ ወደ ፊት ማሳለፍ የሚችል እና የግራ እግር ተጫዋች የሆነ ተከላካይ የሚፈልግ ሲሆን፤ ይህ የ24 ዓመቱ ተጫዋች ለቫን ዳይክ ምርጥ አጋዥ ይሆናል ተብሎ ይታመናል። ለስፖርቲንግ ከ250 በላይ ጨዋታዎችን ማድረግ የቻለውና ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን ቋሚ ተሰላፊ መሆን የቻለው ኢናሲዮ፣ በውሉ ላይ የ52 ሚሊዮን ፓውንድ ማፍረሻ ያለው በመሆኑ ለሊቨርፑል ተመጣጣኝ የገንዘብ አማራጭ ሊሆን ይችላል።
ምንም እንኳን ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቼልሲ ተጫዋቹን ቀደም ብለው ቢፈልጉትም፣ ሊቨርፑል ግን የኮናቴን ምትክ በአስቸኳይ ስለሚፈልግ ተጫዋቹን ለማግኘት የተሻለ ዕድል አለው ተብሏል። ከኢናሲዮ በተጨማሪ የናፖሊው ሳም ቢውኬማ፣ የቶተንሃሙ ወጣት ሉካ ቩስኮቪች እና የኖቲንግሃም ፎረስቱ ሙሪሎ በሊቨርፑል የዝውውር ዝርዝር ውስጥ መካተታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ ክለቡ የተከላካይ መስመሩን የወደፊት ዕድል ለመገንባት በሚቀጥሉት ሳምንታት ጠንካራ እንቅስቃሴ እንደሚያደርግ ይጠበቃል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በሸዋሮቢት ከተማና አካባቢው የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ በቁጥጥር ሥር ማዋል መቻሉ ተገለጸ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት በአካባቢው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን መግለጹ ይታወቃል።... read more
አርሰናል ከሪያል ማድሪድ የጨዋታ ዳሰሳ
አለም በጉጉት እየጠበቀው የሚገኘው የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታ ማክሰኞ ምሽት ይከናወናል።
ሻምፒዮኖቹ ሪያል ማድሪዶች ክብራቸውን ለማስጠበቅ በወሳኝ ምዕራፍ ፤ እና አጓጊ... read more
የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ዣቪ ሲመንስን ለማስፈረም ከተጫዋቹ ወኪሎች ጋር ንግግሮች መጀመራቸው ተገለጸ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከባርሴሎና ታዋቂ የአዳጊዎች ማዕከል ፍሬ ውጤት የሆነው ዣቪ ሲመንስ ወደ ፓሪስ ሴንት ጄርሜ ካቀና በኋላ... read more
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናና ብልሹ አሰራርን ማስቀረት የሚያስችል ነው ተባለ
ከሰሞኑን የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን እንዲጎበኙት ተደርጓል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በእቅድ... read more
🚀 የሰማይ የፍጥነት አውሬዎች፡ MiG-31፣ F-15EX እና Su-27 – ከፍተኛ ፍጥነታቸው ምን ያህል ነው?
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአለማችን ላይ ባሉ እጅግ ዘመናዊ እና ፈጣን የጦር አውሮፕላኖች የፍጥነት አቅም ላይ የሚያጠነጥን መረጃ ቀርቧል። እነዚህ... read more
የዩኤስ ኤድ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ለስደተኞች መቅረብ ከሚገባው ምግብ ውስጥ 40 በመቶ ብቻ እየቀረበ ነው ተባለ
ሕዳር 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ አገልግሎት የዩኤስ ኤድ ድጋፍ ሙሉ በሙሉ መቋረጡን ተከትሎ ለስደተኞቹ መቅረበ ከሚገባው ምግብ ውስጥ... read more
በቻይና 7.1 መጠን ባለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከ95 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 29 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቻይና ተራራማ አካባቢ ማክሰኞ ማለዳ በደረሰ ከባድ የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 95 ሰዎች መሞታቸውን እና 130... read more
ኢትዮጵያ መምከር ጀምራለች
ኢትዮጵያ የመንግሥት አስተዳደር በመመስረት፣ ሕግና ሥርዓት በማበጀት፣ በሃይማኖት መታነጽ፣ በጀግንነት ሀገርን መጠበቅ እንዲሁም ማኅበራዊ ቁርኝት በማጥበቅ ለሺህ ዘመናት የኖሩ ታላላቅ... read more
ማንቸስተር ዩናይትድ በአክዜል ቱዋንዜቤ ጉዳይ ክስ ቀርቦባቸዋል
ሕዳር 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ማንችስተር ዩናይትድ የቀድሞ ተጫዋቹን አክሰል ቱዋንዜቤን ጉዳት በሚገባ እንዲከታተል ሁኔታዎችን ባለማመቻቸት ወይም ባሳዩት ግዴለቅነት የተሞላበት ድርጊት... read more
በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የሆነው ብሄራዊ የተማሪዎች ሽልማት ሊካሄድ ነው
ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሀገራችን የመጀመሪያው እና ብቸኛ የሆነው ሀገር አቀፍ የተማሪዎች ሽልማት ሊካሄድ መሆኑ ተገልጿል።
ይህን ሽልማት የሚያካሂደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ... read more
ምላሽ ይስጡ