ግንቦት 20 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ይህ ጣልያናዊ አማካኝ ስሙ ከመድፈኞቹ ጋር ሲያያዝ ለመጀመሪያ ጊዜ አይደለም፤ አምና ጥር ወር ላይ እንኳን ተጫዋቹን ለማስፈረም ከጫፍ ደርሰው እንደነበር የሚታወስ ነው።
አርሰናል የ22 ዓመታት የፕሪምየር ሊግ ዋንጫ ጥማቸውን በቆረጡ በጥቂት ቀናት ውስጥ፣ የኒውካስሉን ኮከብ ሳንድሮ ቶናሊን ለማስፈረም ጥረት እያደረጉ ነው የሚሉ ዘገባዎች በስፋት እየተሰራጩ ይገኛሉ። ምንም እንኳን የቶናሊ ወኪሎች ተጫዋቹ ከሴንት ጄምስ ፓርክ እንዲወጣ ከፍተኛ ግፊት እያደረጉ እንደሆነ ቢነገርም፣ ተዓማኒው የክሮኒክል ጋዜጠኛ ሊ ራይደር ግን ጉዳዩ ከወሬ የዘለለ እንዳልሆነ ገልጿል።
እንደ ራይደር ዘገባ ከሆነ በአርሰናል ቤት ያሉ የውስጥ ምንጮች ስለ ቶናሊ የሚወራውን ወሬ አስተባብለዋል። በሁለቱ ክለቦች መካከል እስካሁን የተደረገ ይፋዊ ንግግር የሌለ ሲሆን፣ አርሰናልም በዚህ ክረምት ቅድሚያ የሚሰጠው ለአማካይ ክፍል ተጫዋች እንዳልሆነ ተጠቁሟል። የሚኬል አርቴታ ቡድን በዲክላን ራይስ፣ ማርቲን ኦዴጋርድ፣ ሚኬል ሜሪኖ እና ማርቲን ዙቢሜንዲ አማካኝነት ጠንካራ የአማካይ ክፍል ያለው ሲሆን፣ የክለቡ ትኩረት በጉዳት ምክንያት ክፍተት በታየባቸው የተከላካይ እና የፊት መስመር ክፍሎች ላይ ነው።
ኒውካስል ዩናይትድ ለጣሊያናዊው ኮከብ ከ75 ሚሊዮን እስከ 100 ሚሊዮን ፓውንድ የሚደርስ ዋጋ የለጠፈ ሲሆን፣ ተጫዋቹ እስከ 2029 ድረስ የሚያቆይ ውል አለው። ክለቡ የአውሮፓ መድረክ ተሳትፎ እድልን አላገኘም፤ ያንን ተከትሎ ቶናሊ ሊለቅ ይችላል የሚል ግምት ቢኖርም፣ ኒውካስል ግን ተጫዋቹን በራሱ ፍላጎት እና በፈለገው ዋጋ እንጂ በቀላሉ አሳልፎ ለመስጠት ዝግጁ እንዳልሆነ ተጠቁሟል። አርሰናል በአሁኑ ወቅት ትኩረቱን በቡዳፔስት በሚካሄደው የሻምፒዮንስ ሊግ ፋይናል ላይ ያደረገ በመሆኑ የዝውውር ጉዳዩ ለጊዜው የቆየ ይመስላል።
ሳንድሮ ቶናሊ ከውርርድ እገዳው ከተመለሰ በኋላ ለኒውካስል ዩናይትድ በነበረው ቆይታ በሊጉ ካሉ ምርጥ አማካዮች አንዱ መሆኑን አስመስክሯል። ተጫዋቹ ለኒውካስል ባደረጋቸው ጨዋታዎች በኳስ ቁጥጥር፣ በጨዋታ ንባብ እና በፈጣሪነት ብቃቱ የሚደነቅ ሲሆን፣ እስካሁንም ለክለቡ በሁሉም ውድድሮች 2 ግቦችን ከመረብ ማሳረፍ የቻለ ሲሆን 3 ለጎል የሚሆኑ ኳሶችንም አመቻችቶ አቀብሏል። ቶናሊ በጨዋታ በአማካይ 85 በመቶ የኳስ ቅብብል ስኬት ያለው ሲሆን፣ ይህም ለአርሰናል መሰል ክለቦች ተመራጭ እንዲሆን አድርጎታል።
ኒውካስል ባለፈው የዝውውር መስኮት አሌክሳንደር ኢሳክን ለሊቨርፑል አሳልፎ የሰጠ ቢሆንም፣ አሁን ግን የክለቡ አስተዳደራዊ መዋቅር የተሻለ በመሆኑ ተጫዋቹን በቀላሉ የመልቀቅ ፍላጎት የለውም። ነገር ግን የትርፋማነት እና የፋይናንስ ደንብ ስጋት ያለበት ኒውካስል፣ እስከ 75 ሚሊዮን ዩሮ ከቀረበለት ተጫዋቹን ለመሸጥ አይኑን ያሻሻል ተብሎ አይጠበቅም።
ይህ ጣልያናዊ አስደናቂ አማካኝ በሦስቱ ታላላቅ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች ማለትም በአርሰናል እና በሁለቱ የማንቸስተር ከተማ ክለቦች በጥብቅ ይፈለጋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ