ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም ፖለቲካ ትኩረት አሁንም በቻይና መናገሻ ከተማ ላይ ያረፈ ሲሆን የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ የአሜሪካውን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን በታላቁ የሕዝብ አዳራሽ ካስተናገዱ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን በዚሁ ታሪካዊ ሥፍራ በደማቅ ወታደራዊ ክብር ተቀብለዋል።
የቻይና ወታደሮች፣ የጦር ኃይሎች የሙዚቃ ባንድ እና የሩሲያና ቻይናን ባንዲራዎች የሚያወገረግቡ ሕፃናት በቤጂንግ መሃል ለፕሬዚዳንት ፑቲን ከፍተኛ ክብር የታየበት አቀባበል አድርገውላቸዋል። በመቀጠልም ሁለቱ መሪዎች በጠበበ እና በሰፊው የልዑካን ቡድን መዋቅር የፊት ለፊት ውይይት ያደረጉ ሲሆን በውይይቱም ላይ የንግድ እና የኢነርጂ ትብብር፣ የዩክሬን ጦርነት፣ የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ እንዲሁም በቻይና እና ሩሲያ መካከል ስላለው ስልታዊ አጋርነት በሰፊው መክረዋል።
በዚህ ታሪካዊ ስብሰባ ላይ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሩሲያ ለቻይና ምንጊዜም አስተማማኝ የኢነርጂ አቅራቢ ሆና እንደምትቀጥል በድጋሚ ያረጋገጡ ሲሆን በሌላ በኩል ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ወደ ጫካ ሕግ እንዳይመለስ እና የኃያላን ፍላጎት በደካሞች ላይ እንዳይጫን ጠንካራ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል። አክለውም በመካከለኛው ምስራቅ በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
ይህ በሞስኮ እና በቤጂንግ መካከል ያለው ወዳጅነት በደመቀበት በዚሁ ዕለት፣ ቻይና ከዋሽንግተን ጋር ያላትን ግንኙነት ለማመጣጠን ትልቅ እርምጃ መውሰዷን አረጋግጣለች። ቤጂንግ ሁለት መቶ የቦይንግ አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማቀዷን ይፋ ያደረገች ሲሆን፣ ከአሜሪካ ጋር ያለውን የንግድ ስምምነት ለማራዘም ፍላጎት እንዳላት ገልጻለች። ይህ እርምጃ ቻይና በሞስኮ እና በዋሽንግተን መካከል ያላትን የዲፕሎማሲ እና የንግድ ሚዛን በጥንቃቄ እየጠበቀች መሆኑን ለዓለም ያሳየችበት ትልቅ ኩነት ሆኖ ተመዝግቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት መስማማታቸው ተገለጸ
ታኅሳስ 08 ቀን 2017 ዓ.ም(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት መፈራረማቸው ተገልጿል፡፡
በስምምነቱ በሰላም እና ፀጥታ፣ ኢኮኖሚ... read more
በአዲስ አበባ ከተማ ከግንቦት 6 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም የኩፍኝ የዘመቻ ክትባት ሊደረግ ነዉ
የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ በቀጣይ ከግንቦት 6 እስከ 15 ቀን 2017 ዓ.ም የሚካሄደውን የኩፍኝ ክትባት ዘመቻ በተመለከተ ከሚዲያ አካላት... read more
የቢሊየነሩ የፅሁፍ ስህተት ውዝግብ አስነሳ፤ የኢራን ቆንስላ ለኢሎን ማስክ “ተጨማሪ ትምህርት ያስፈልግሃል!” ሲል መለሰለት
ሰኔ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኤክስ (X) ባለቤትና ታዋቂው ቢሊየነር ኢሎን ማስክ በስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ ስያሜ ዙሪያ በገጹ ላይ ያሰፈረው... read more
ያለ ምንም ማስያዣ ለአርሶ አደሩ ብድር የማመቻቸቱ አሰራር የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመን እና ማሳደግ እንደሚረዳ ተገለጸ
ሐምሌ 29 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ አርሶ አደሮች በቂ የብድር አገልግሎት ባለማግኘታቸው እምብዛም ምርታማ ያለመሆን እና ዘርፉም ያለመዘመን... read more
ቆዳን እስከ አጥንት የማራገፍ ምትሀታዊ ችሎታ ያለው የነብር ምላስ
ሐምሌ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓለም የዱር እንስሳት ስነ-ምህዳር ውስጥ የላቀ ቦታ የሚሰጠውና በአድኖ ችሎታው የሚታወቀው ነብር፣ በቀላሉ የሚታይ ነገር... read more
የቤት ልማት ተደራሽነትን ለማስፋት የፋይናንስ አማራጭ ጥናቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ ተገለጸ
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቤት ልማት ተደራሽነትን ለማስፋት የፋይናንስ አማራጭ ጥናቱ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ይፋ እንደሚደረግ የፖሊሲ... read more
በበቆጂ አቅራቢያ በሚገኘው የጋለማ ደን የተነሳዉን እሳት ለማጥፋት መሳሪያ ቢጠየቅም ማግኘት አልተቻለም ተባለ
ለአንድ ሳምንት ያህል በአርሲ የሚገኘው የጋለማ ደን በእሳት ውስጥ እንደሚገኝ ያስታወቀው የአርሲ ተራራሮች ብሄራዊ ፓርክ ነው፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው የፓርኩ ሃላፊ... read more
ካናዳ የፍልስጤምን መንግስት በመስከረም ወር እውቅና ለመስጠት ከፈረንሳይና ከእንግሊዝ ጋር ተቀላቀለች
ሐምሌ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ካናዳ በመስከረም ወር የፍልስጤምን መንግስት በይፋ እውቅና እንደምትሰጥ ማስታወቋን ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኒ አስታወቁ። ካናዳ በዚህ... read more
የተቀቀለ ስጋን በስፋት ወደ ውጭ ሃገራት በመላክ የሚገኘውን የገቢ መጠን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አስታወቀ
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀዳሚ የሚያደርጋት የቁም እንስሳት ሃብት ቢኖራትም በገቢ ደረጃ ግን በሚፈለገው ልክ እንዳልተጠቀምንበት የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡
የተቀቀለ ስጋን ወደ ውጭ... read more
ትንታኔቴል አቪቭ ጎራዴዋን ታነሳ ይሆን?
https://youtu.be/AZQD1yXaa5g
read more
ምላሽ ይስጡ