መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) «የምድር ጌጥ ኢትዮጵያ» በሚል ርዕስ ሲካሄድ የቆየው ታሪካዊና ባህላዊ አውደ ርዕይ የመጎበኛ ጊዜ፣ ከህዝብ የቀረበውን ከፍተኛ ፍላጎትና ጥያቄ መነሻ በማድረግ ለተጨማሪ ሶስት ሳምንታት መራዘሙ የዝግጅቱ አዘጋጅ «የሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት» አስታዉቋል፡፡ አውደ ርዕዩ ከዚህ ቀደም ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 10 ቀን ሲካሄድ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የነበሩ የሃይማኖታዊና የባህላዊ በዓላት መደራረብ እንዲሁም ከቦታ ምቾት ጋር ተያይዘው የነበሩ ችግሮች የጎብኚዎችን ቁጥር እንደገደበዉ ድርጅቱ ገልጻል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ አውደ ርዕይ፤ ህፃናትና ቤተሰቦች የሀገራቸውን፣ የሃይማኖታቸውን፤ የቅዱሳት ቤተክርስቲያናትን ታሪክና ቅርሶች በቅርበት የሚያውቁበትን እድል የፈጠረ ነው ተብሏል። ዝግጅቱም በማየት፣ በመዳሰስ፣ በመስማት፣ በማሸተትና በመቅመስ አምስቱንም የስሜት ሕዋሳት በሚያሳትፍ ልዩ አቀራረብ የተዘጋጀ ሲሆን፤ የላሊበላ፣ የአክሱም፣ የደብረ ዳሞና የሌሎችም ታሪካዊ ቦታዎች ምስልና ቅርሶች ቀርበውበታል። በተጨማሪም በቦታው ላይ በርካታ ታሪካዊና ባህላዊ ይዘቶች በመኖራቸው፤ አውደ ርዕዩን ወደፊት «ቋሚ ሙዚየም» ለማድረግ የሚያስችል ሥራ በጥረት ላይ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። በዚሁ መሠረት አውደ ርዕዩ ከመስከረም 30 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር አጋማሽ ድረስ ባሉት ተከታታይ ሶስት ሳምንታት፤ በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል። አስተባባሪዎቹ አክለውም፤ እስካሁን አውደ ርዕዩን ያላዩ ህፃናትና ቤተሰቦች ከጦር ኃይሎች ወደ ቀራኒዮ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው «ሆላንድ ፓርክ» በመገኘት ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለአማራ ክልል ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን የምግብ ድጋፍ ማድረጉን አስታወቀ
ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል በተከሰተው ድርቅ የከፋ ችግር ላይ ለሚገኙ ዜጎች ከ5 ሚሊዮን ብር... read more
በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንቶሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦች ተከሰሱ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በታክስ ስወራ፣ የተጨማሪ ታክስ አለመክፈል፣ በኮንቶሮባንድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘውን ገንዘብ ሕጋዊ አስመስሎ በማቅረብ ወንጀል... read more
ባንኮች እስከ ምሽት 3፡30 ሰዓት ድረስ ክፍት እንዲሆኑ የሚያስገድደዉ ደንብ ከባንኮች አሰራር ጋር የማይጣጣም ነዉ ሲል የባንኮች ማህበር አስታወቀ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወጣው ባንኮች እስከ ምሽት 3:30 ሰዓት ድረስ አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ ከባንኮች አሠራር ጋር የማይጣጣም መሆኑን... read more
የፍሳሽ አወጋገድን በተመለከተ የወጣው መመሪያ አቅመ ደካሞችን ያማከለ አይደለም ተባለ
👉የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በበኩሉ የዜጎችን ህገ-መንግስታዊ መብት ያስጠበቀ መመሪያ ነው ብሏል።
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)ቅሬታቸውን... read more
በእስራኤል ጥቃት የሞቱት የኢራን ባለስልጣናት እና ሳይንቲስቶች ሙሉ ስም እና የስራ ኃላፊነታቸው
👉ሜጀር ጄኔራል ሆሰይን ሰላሚ (Major General Hossein Salami): የኢስላሚክ አብዮታዊ ጥበቃ ኃይሎች (IRGC) ዋና አዛዥ የነበሩ ሲሆን፣ በእስራኤል የአየር ጥቃት... read more
በአማራ ክልል ሁለት ሰዎች ላይ የኤም ፖክስ (Mpox) ቫይረስ መገኘቱ ተገለጸ
በአማራ ክልል ኤም ፖክስ (MPox) ተላላፊ ቫይረስ በሽታ በመተማ እና ባሕርዳር ከተሞች በሁለት ሰዎች ናሙና ተወስዶ መረጋገጡን የአማራ ክልል የኅብረተሰብ... read more
የዩ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ. መቋረጥ በኢትዮጵያ ላይ የደቀነው አደጋ
https://youtu.be/2kwjgk-Qmdc
read more
ከትራፊክ አደጋ እስከ አሰቃቂ የህይወት ምዕራፍ …የህክምና እጦት
እናት ለቤቷ ምሶሶ እንደሆነች ይታወቃል ልጆችም ከሌላው ቤተሰብ በተሻለ መልኩ ከእናታቸው ጋር የቀረበ ግንኙነት እንደለቸው ነው የሚነገረው፤ በሃገራችን ኢትዮጵያ ብሎም... read more
በክልሉ በምሽትና በርቀት ተምረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 23 ሺህ 281 ተማሪዎች ውስጥ አንድም ተማሪ የማለፊያ ውጤት አለማምጣቱን የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ገለጸ፡፡
ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በምሽትና በርቀት በግልና በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን ተከታትለው... read more
በአፋር ክልል የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ለጊዜው መቆሙን ተከትሎ ከስፍራው የተፈናቀሉ ዜጎች እና ፋብሪካዎችን ስራ ለማስጀመር ጥናት እየተጠና መሆኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ሰራተኞች ማህበራት ኮንፌዴሬሽን በበኩሉ በክልሉ ከከሰም የስኳር ፋብሪካ የተፈናቀሉ ሰራተኞችን በተለያዩ ፋብሪካዎች ለማሰማራት የታቀደ ቢሆንም፤ ፋብሪካዎቹ ካላቸው የሰራተኛ ቁጥር... read more
ምላሽ ይስጡ