ሰኔ 18 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ፥ የቀድሞዋን የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ተፅዕኖን እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን በበላይነት የማጠናከር እና የማስተካከል ትልቅ ኃላፊነት እንደሰጧቸው ተሰማ። ይህ የተሰጣቸው አዲስ ተልዕኮ በቀጠናው እየታዩ ያሉ የጸጥታ እና የዲፕሎማሲ መሻከር አዝማሚያዎችን በታዋቂ እና አንጋፋ ዲፕሎማቶች አማካኝነት ለመፍታት ከተያዘው የድርጅቱ ስትራቴጂ ጋር የተያያዘ መሆኑ ታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የውስጥ ምንጮች እንደገለጹት፣ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ በቀጠናው ባላቸው የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲ ልምድ፣ በተለይም ቀደም ሲል በጅቡቲ፣ በሴኔጋል እና በፈረንሳይ አምባሳደር እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (IGAD) እና በአፍሪካ ህብረት የዩኤን ልዩ መልዕክተኛ ሆነው በከፍተኛ የኃላፊነት ደረጃ የሰሩ በመሆናቸው ለዚህ ታላቅ ቀጠናዊ ሚና ተመራጭ አድርጓቸዋል።
ዋና ፀሐፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ ይህንን ውሳኔ ያሳለፉት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለውን የፖለቲካ ውጥረት ለማርገብ፣ በሀገራት መካከል ያለውን ትብብር መልሶ ለመገንባት እና የድርጅቱን ቀጠናዊ ተሰሚነት ከፍ ለማድረግ ታስቦ መሆኑ ተጠቁሟል። ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴም በቅርቡ የስልጣን ዘመናቸውን ካጠናቀቁ በኋላ በተለያዩ አህጉራዊ የግጭት አፈታት እና የሰላም ግንባታ ውይይቶች ላይ በንቃት እየተሳተፉ መቆየታቸው ይታወሳል።
ይህ ሹመት ዩኤን ለአፍሪካ ቀንድ ቀውስ ዘላቂ መፍትሄ ለመፈለግ በወሰደው ስልታዊ እርምጃ ውስጥ ትልቅ ግምት የተሰጠው ሲሆን፥ አዳዲስ ዝርዝር መረጃዎችን እና የሹመቱን ሙሉ ይዘት እንደደረሰን የምናቀርብ ይሆናል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
በከተማዋ 19 መስመሮች እስከ ምሽት 4 ሰዓት በቋሚነት የአውቶቢስ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ የአውቶቢስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሚሰጡ መስመሮች 19ኙ በቋሚነት እስከ ምሽት 4፡00 ሰዓት አገልግሎት... read more
ሀገራዊምክክር ኮሚሽን ለውይይት የሚቀርቡ አጀንዳዎችን ዛሬ ለሕዝብ ይፋ ሊያደርግ ነው
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ላለፉት አራት ዓመታት አጀንዳዎችን በማሰባሰብና በተለያዩ ምዕራፎች በርካታ ተግባራትን ሲያከናውን የቆየው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣... read more
የሚፈጸሙ ፆታዊ ጥቃቶችን ለፍትህ ተቋማት የሚያሳዉቁ የማህበረሰብ ክፍሎች አነስተኛ መሆናቸው አሳሳቢ ነው ሲል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
ጥር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶች እየተበራከቱ መምጣታቸዉን የሚያመላክቱ መረጃ እና ሪፖርቶች እንዳሉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ... read more
አፍሪካዊው የፈጠራ ሰው ከ40 በላይ ቋንቋዎችን በቅጽበት የሚተረጉም የጆሮ ማዳመጫ ፈጠረ
👉የቋንቋ አለመቻል ችግርን ይቀርፋል ተብሏል
ሐምሌ 27 ቀን2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአንድ አፍሪካዊ የፈጠራ ባለሙያ የተሰራው አዲስ የጆሮ ማዳመጫ፣ ከ40 በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎችን የበይነመረብ... read more
♻️ዝክረ ቡልቻ ደመቅሳ
🔰በመናኸሪያ ሌማት ፕሮግራማችን ቅዳሜ ከ10፡00 - 11፡00 ይጠብቁን!
አዘጋጅ እና አቅራቢ ሱራፌል ዘላለም__
ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ... read more
በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኝ መተከሉ ተገለጸ
ሐምሌ 08 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አማካኝነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 7ኛ ዙር የክረምት ወራትም በመከናወን... read more
ኢንሳ ድሮንን በመጠቀም ለትራንስፖርት ምቹ ባለሆኑ ቦታዎች ላይ ክትባቶችን እና ለግብርና የሚወሉ ኬሚካሎችን እያጓጓዘ መሆኑን ገለጸ
ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ኢንሳ ለትራንስፖርት ምቹ ባለሆኑና በፍጥነት መድረስ የሚገባቸውን እንደ ክትባትና ለግብርና ስራ ጥቅም... read more
ያለፓስፖርት የማይንቀሳቀሱት የአየርላንድ ላሞች
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አየርላንድ የእንስሳት እርባታን እና የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ ከፍ ያለ ትኩረት በመስጠት ትታወቃለች። ከዚህም አንዱ የላሞች ልዩ... read more
የኢራን ባለስልጣናት 997 የስታርሊንክ (Starlink) ሳተላይት መሣሪያዎችን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን እና 163 ሰዎችን ማሰራቸውን አወጁ!
ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢራን ከፍተኛ የመንግስት አካላት በተደረገው መጠነ ሰፊ ክትትል ከግንቦት እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም (እንደ አውሮፓውያኑ... read more
ምላሽ ይስጡ