መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት በአካባቢው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን መግለጹ ይታወቃል። በጉዳዩ ላይ መናኸሪያ ሬዲዮ የክልሉን ግብርና ቢሮ አነጋግሯል። በአካባቢው የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ አደጋ እንዳያስከትል በአጭር ጊዜ መቆጣጠር መቻሉን የገለጹት በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ ናቸው፡፡ የግሪሳ ወፍ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት በመሆኑ ሸዋሮቢትን ጨምሮ በ5 ዞኖችና በ60 ቀበሌዎች ጭምር መታየቱን ተናግረዋል። ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት መደረጉን ገልጸው፤ አሁን ላይ ጉዳት በማያስከትልበት ደረጃ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል። የኤልኒኖ ሥጋት ባለበት በዚህ ወቅት ድርቅ፣ ያልተስተካከለ የዝናብ ስርጭትና የሰብል አጥፊ ተባዮች እንደሚከሰቱ የሚጠበቅ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የተለያዩ ወራሪ ተባዮችን ጨምሮ የግብርናውን ሥርዓት ከሚያዛቡ ነገሮች አስቀድሞ ለመከላከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ ያለው የሰብል ሁኔታ በግሪሳ ወፍ ለመበላት ያልደረሰ በመሆኑ የከፋ ጉዳት አለመድረሱን ተናግረው፤ እስካሁን የግብዓትና የኬሚካል እጥረት አለመኖሩን እንዲሁም የተጀመረው የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። መናኸሪያ ሬዲዮ በጉዳዩ ላይ የግብርና ሚኒስቴርን ቢጠይቅም በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥበት በመግለጽ ምላሽ ሰጥቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በምክር ቤቱ የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴ አመራሮች ተሰየሙ
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመን በ27ኛ መደበኛ ስብሰባው በምክር ቤቱ የተጓደሉ የቋሚ ኮሚቴ አመራሮችን ሰይሟል፡፡
አፈ ጉባኤ... read more
የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የቴክኒካል ጥገና ስልጠና እየሰጠ መሆኑ ገለጸ
👉የፌደራል ቴክኒክ እና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ከቻይና አጋር አካላት ጋር በጋራ በመሆን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የቴክኒካል ጥገና ስልጠና እየሰጠ መሆኑን ገለጸ
ነሐሴ... read more
ሳይንቲስቶች በፈንገስ የተደገፈ የሚያበራ እንጨት መፍጠራቸውን አስታወቁ
👉ጎዳናዎችና መናፈሻዎች ያለኤሌክትሪክ ይበራሉ ነው የተባለው።
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሳይንቲስቶች በጨለማ ውስጥ በራሱ የሚያበራ፣ በፈንገስ የተመሰረተ አዲስ የእንጨት ዓይነት... read more
ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት ጋር እያካሄደችው ያለው ግንኙነት የባህር በር ለማግኘት የተሻለ ዲፕሎማሲያዊ አካሄድ ነው ተባለ
ጥር 06 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ፌዴራል መንግስት ጋር እያካሄደችው ያለው ግንኙነት የባህር በር ለማግኘት የተሻለ ዲፕሎማሲያዊ ሂደት መሆኑን አምባሳደሮችና... read more
ለነዳጅ እጥረት እንደምክንያት እየቀረበ ያለው ጉዳይ
https://youtu.be/y9xV3WV4Koo
read more
ወቅቱ የወባ ትንኝ መፈልፈያ ቢሆንም እንደ ሃገር ያለው የወባ ስርጭት መጠን መሻሻል የታየበት ነው ተባለ
ጥቅምት 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከመስከረም እስከ ታህሳስ ያለው ወቅት የወባ ትንኝ የሚፈለፈልበት መሆኑን ተከትሎ በተቀናጀ ሁኔታ በየሳምንቱ በየክልሎች ያለውን ፤የመገምገም... read more
የጎንደር ከተማን የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር ለመፍታት የበጀት እጥረት አጋጥሟል ተባለ
ጥቅምት 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ችግሩን ለመፍታትም ባለፈው አመት በመገጭ ወንዝ ላይ የግንባታ ስራ የተጀመረ ቢሆንም እስካሁን ግን የመጣ መፍትሄ... read more
የፈጠራ ባህልን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው ተባለ
መንግስት የፈጠራ ባህልን ለማሳደግ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
የኢትዮ ሮቦ- ሮቦቲክስ ማኔጂንግ ዳይሬክተር በበኩላቸው አሁንም... read more
ምላሽ ይስጡ