መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ግብርና ጽሕፈት ቤት በአካባቢው አጥፊው የግሪሳ ወፍ መከሰቱን መግለጹ ይታወቃል። በጉዳዩ ላይ መናኸሪያ ሬዲዮ የክልሉን ግብርና ቢሮ አነጋግሯል። በአካባቢው የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ አደጋ እንዳያስከትል በአጭር ጊዜ መቆጣጠር መቻሉን የገለጹት በአማራ ክልል ግብርና ቢሮ የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ዶ/ር ማንደፍሮ አስላከ ናቸው፡፡ የግሪሳ ወፍ በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት በመሆኑ ሸዋሮቢትን ጨምሮ በ5 ዞኖችና በ60 ቀበሌዎች ጭምር መታየቱን ተናግረዋል። ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በጋራ በመሆን በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት መደረጉን ገልጸው፤ አሁን ላይ ጉዳት በማያስከትልበት ደረጃ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል። የኤልኒኖ ሥጋት ባለበት በዚህ ወቅት ድርቅ፣ ያልተስተካከለ የዝናብ ስርጭትና የሰብል አጥፊ ተባዮች እንደሚከሰቱ የሚጠበቅ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የተለያዩ ወራሪ ተባዮችን ጨምሮ የግብርናውን ሥርዓት ከሚያዛቡ ነገሮች አስቀድሞ ለመከላከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ ያለው የሰብል ሁኔታ በግሪሳ ወፍ ለመበላት ያልደረሰ በመሆኑ የከፋ ጉዳት አለመድረሱን ተናግረው፤ እስካሁን የግብዓትና የኬሚካል እጥረት አለመኖሩን እንዲሁም የተጀመረው የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል። መናኸሪያ ሬዲዮ በጉዳዩ ላይ የግብርና ሚኒስቴርን ቢጠይቅም በቅርቡ መግለጫ እንደሚሰጥበት በመግለጽ ምላሽ ሰጥቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ባለፉት 6 ወራት ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ከመጡት ውስጥ 25ሺሕ 581ዱ ብቻ ተገቢውን መስፈርት ያሟሉ መሆናቸውን የሲቭል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ገለጸ
ከክልል ከተሞች መሸኛ ይዘው ከመጡት ውስጥ 25ሺህ 581ዱ ብቻ በመዲናዋ የሚጠየቀውን መስፈርት ያሟሉ መሆናቸውን የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታወቀ።
ኤጀንሲው... read more
“ደህንነቱ የተጠበቀ የጤና ክብካቤ ለሁሉም ጨቅላ ህፃናት እና ህፃናት” በሚል መሪ ቃል የዓለም የታካሚዎች ደህንነት ቀን በላንድማርክ ሆስፒታል ተከበረ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም የታካሚዎች ደህንነት ቀን በላንድማርክ ጠቅላላ ሆስፒታል እየተከበረ ነው።
"ደህንነቱን የጠበቀ የጤና ክብካቤ ለሁሉም ጨቅላ... read more
በአደገኛ ጦር ተወግታ የ100 አመት እድሜ ያስቆጠረች ዓሣ ነባሪ
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአላስካ አዳኞች በተያዘችው ዓሣ ነባሪ ላይ በ19ኛው ክፍለ ዘመን የተሰራ የጦር ጫፍ መገኘቱ ሳይንቲስቶችን አስገርሟል።
ይህ... read more
በመኪናዎ የሞተር ዘይት መያዣ (Oil Canister) ላይ የሚጻፉትን ምስጢራዊ ቁጥሮች እና ፊደላት ያውቋቸዋል?
ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የመኪና ባለቤቶች እና አሽከርካሪዎች ለተሽከርካሪዎቻቸው የሞተር ዘይት ሲገዙ ወይም ሲቀይሩ በዘይቱ መያዣ ላይ የተጻፉትን ቁጥሮች... read more
በአለም አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ቢኖርም በአዲስ አበባ ግን በቅርቡ የዋጋ ጭማሪ እንደማይደረግ ተገለጸ
ሰኔ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ምንም እንኳን በአለም አቀፍ ደረጃ በሚገኙ ግዙፍ የነዳጅ አቅራቢ ሃገራት ላይ ውጥረት በመፈጠሩ በአቅርቦት እና... read more
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ለስም እንዲኖር፤ በተግባር ግን እንዳይሰራ እየተደረገ ነው ተባለ
ባለፉት ጊዜያት ምክር ቤቱ በሀገራዊ የፖለቲካ፤ ማህበራዊ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያወጣቸው የአቋም ሪፖርቶች እንደነበሩ ይታወቃል፡፡
ሆኖም ዛሬ ላይ ምክር ቤቱ... read more
በአፍንጫዎ ላይ የሚታየው መስመር ስለ ጤናዎ የሚናገረው ድብቅ ምስጢር
ግንቦት 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ብዙ ሰዎች በአፍንጫቸው የታችኛው ክፍል ላይ አግድም የሆነ መስመር ወይም እጥፋት ሲኖር ይስተዋላል። ይህ ምልክት... read more
በከተማ ለስላሳ ነፋስ 10 ኪሎዋት ኃይል የሚያመነጨው የፈረንሳይ ‘የነፋስ ዛፍ’
ጥቅምት 27 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ፈረንሳይ በከተማ አካባቢ ለስላሳ ነፋስን ወደ ንፁህ ኃይል በመለወጥ ረገድ አዲስ ምዕራፍ የከፈተችውን ፈጠራ ይፋ አደረገች።
የነፋስ... read more
በኢትዮጵያ ያልተገራ የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በሕግ አግባብ ብቻ ማስተካከል አዳጋች መሆኑ ተገለጸ
ታኅሳስ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለአጠቃቀም ምቹ እና ቀላል በሆኑት የማኅበራዊ ሚዲያ አማራጮች ላይ የሚጋሩ የሕዝብን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥሉ... read more
እንደ ሀገር ይህ ነው ተብሎ የተለየ ስያሜ የሚሰጠው የኢኮኖሚ ርዕዮት ዓለም እንደሌለ ተገለጸ
ኅዳር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሁን ላይ እንደ ሀገር የምንከለተው የኢኮኖሚ ስርዓት አፈጻጸሙና መልኩ ካፒታሊስት ይምሰል እንጂ ቅይጥ ኢኮኖሚ፣ ካፒታሊስት... read more
ምላሽ ይስጡ