መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ)በበጋ ወራት ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸውን በሚያገኙ የደቡብ እና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች የሚያገኙትን ዝናብ በአግባቡ ሊጠቀሙ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሜቴኦሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡ በኢንስቲትዩቱ ትንበያ መሠረት በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች፣ ከፊል አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች መረጃው እንዲደርስ እየተደረገ መሆኑን የተቋሙ የግብርና ሜቴኦሮሎጂ ባለሙያ አቶ ይመር አሰፋ ገልጸዋል፡፡ በአካባቢው የሚኖሩ አርሶ አደሮች በወቅቱ የመሬት ዝግጅት፣ የዘር ምርጫ እና የግብዓት አቅርቦት ሥራ ማከናወን እንዳለባቸው ጠቅሰዋል፡፡ የተለያየ የዝናብ መጠን እና ሥርጭት ሊያጋጥም ስለሚችል አርሶ አደሮች ከአካባቢያቸው የግብርና ባለሙያዎች ጋር በመመካከር ለዝናብ ሁኔታው ተስማሚ ጊዜ እና የዘር ዓይነት መምረጥ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በበጋው ወራት የኤልኒኖ ክስተት ለእነዚህ አካባቢዎች አዎንታዊ ሚና እንዳለው የተናገሩት ባለሙያው፤ በሰሜን አጋማሽ አካባቢዎች ደግሞ ሰብል የሚሰበሰብበት ወቅት እንደመሆኑ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የሚያስከትል በመሆኑ አሉታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡ ኢንስቲትዩቱ ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን በተለያዩ አማራጮች የበጋ የአየር ትንበያ መረጃ ተደራሽ እንዲሆን ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑን አቶ ይመር ገልጸዋል፡፡ በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች የበልግ ዝናብን የሚጠብቁ አርሶ አደሮች፣ የሚገኘውን የዝናብ ዕድል ወደ ምርት ለመቀየር የዘር፣ የመሬት፣ የግብዓትና የውኃ ዝግጅታቸውን በወቅቱ ማጠናቀቅ እንዳለባቸው ተመልክቷል፡፡ ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በእግር እየተጓዙ ስልክዎን ይሙሉ❗️
🛑የ15 ዓመቱ ፊሊፒናዊ ተማሪ የፈጠረው አስደናቂ ጫማ
ሰኔ 23 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)"እግር ይራመዱ፣ ስልክዎን ይሙሉ፣ ዓለምን ያሸንፉ!" የ15 ዓመቱ ፊሊፒናዊ... read more
ወጋገን ባንክ 33ኛ መደበኛ እና 16ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤን አካሄደ
መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባንኩ ከታክስ በፊት 4.3 ቢሊዮን ብር ትርፍ ሲያስመዘግብ፣ ጠቅላላ ሀብቱም 111.3 ቢሊዮን ብር መድረሱን አስታውቋል።... read more
በኢትዮጵያ በኤም ፖክስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተገለፀ
በጤና ሚኒስቴር በኩል የቅድመ ዝግጅት እና የቅኝት ስራዎች እየተሰሩ ቢሆንም በኢትዮጵያ በዝንጀሮ ፈንጣጣ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ሚኒስቴሩ ለመናኸሪያ... read more
በአንዳንድ ተቋማት ስር ያሉ አሰሪዎች ለሰራተኞቻቸው ጥብቅና በመቆማቸው ብቻ ከስራ ገበታቸው የመፈናቀል አደጋ እያጋጠማቸው መሆኑን የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን ገለጸ
የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን /ኢሰማኮ/ በአንዳንድ ተቋማት ስር የሚገኙ አሰሪዎች ለሰራተኞቻቸው ጥብቅና በመቆማቸው ብቻ ከስራ ገበታቸው የመፈናቀል አደጋ እያጋጠማቸው መሆኑን... read more
የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ ቋንቋ የመጥፋት አደጋ ስለተጋረጠበት የብሔረሰቡን ምሁራንና የመንግሥትን ትኩረት እንደሚሻ ተገለጸ
መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚገኙ 5 ነባር ብሔረሰቦች መካከል አንዱ የሆነው የቦሮ ሺናሻ ብሔረሰብ... read more
አዲሱ የካሳ አከፋፈል አዋጅ ማስፈጸሚያ መመሪያና ደንብ ስላልወጣለት በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ተግዳሮት መፍጠሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለጸ።
ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የካሳ ክፍያ በክልሎች እንዲፈጸም የሚደነግገው አዲሱ አዋጅ እስካሁን ማስፈጸሚያ መመሪያና ደንብ እንዳልወጣለት ለመናኸሪያ ሬዲዮ የተናገሩት... read more
በጦርነት ቀጠናዎች ለመለየት አስቸጋሪ የሆኑትን የፕላስቲክ ፈንጂዎች በቀላሉ የሚያጋልጠው አዲስ ድሮን ተሰራ
ሐምሌ 03 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአሜሪካው ቢንግሃምተን ዩኒቨርሲቲ የሚገኙ ተመራማሪዎች፣ በተለምዶ “ቢራቢሮ” እየተባሉ የሚጠሩትን እና በብረታ ብረት መመርመሪያዎች ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ... read more
ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በትራፊክ አደጋ ቅነሳ በሰራችሁ ስራ ከዓለም አቀፍ ተቋማት እውቅና ማግኘቷ ተገለጸ
ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በሰራችሁ ስራ ከዓለም አቀፍ ተቋማት እውቅና ማግኘቷን የመንገድ ደህንነትና መድን ፈንድ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
ምንም እንኳን አሁንም የትራፊክ አደጋ... read more
የብራዚሏ ላም በአንድ ቀን 123 ሊትር ወተት በማምረት ታሪክ ሰራች
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በብራዚል የምትገኝ አንዲት ላም በአንድ ቀን ውስጥ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ የወተት መጠን በማምረት የዓለም ክብረወሰን... read more
በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንዱስትሪ ስርጭትን የሚያሳይ ጥናት እየተጠናቀቀ ነው ተባለ
በሀገር አቀፍ ደረጃ የኢንዱስትሪ ስርጭትን የሚያሳይ ጥናት እየተጠናቀቀ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል፡፡
ጥናቱ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለማሳደግ እና በሁሉም... read more
ምላሽ ይስጡ