መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያለፈውን የክረምት ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማ እና የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ይፋ የሚደረግበት መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂዷል። ግምገማው የትንበያ ጥራትን፣ ተደራሽነትንና ተጠቃሚነትን ለማሻሻል የሚያግዙ አቅጣጫዎችን ለመለየት እድል የሚፈጥር በመሆኑ፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ሁኔታዎችን ቀድሞ ግንዛቤ እንዲኖር በማድረግ ተገቢ ዝግጅትና የምላሽ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት የገለጹት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና በዓለም ሚቴዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፈጠነ ተሾመ ናቸው። በመድረኩ የ2018 ክረምት ወራት የዝናብ ስርጭት እና የነበሩ ተጽዕኖዎች፣ እንዲሁም የ2019 የበጋ የአየር ሁኔታ ትንበያ ይፋ ተድርጓል። በአብዛኛው የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከመደበኛ በላይ እንደሚሆን የኢንስቲትዩቱ የትንበያ መረጃ ጠቅሷል። ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን ተነስቷል። በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች በበጋ ወቅት የሚከናወኑ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል። የውሃ አቅርቦትን ከማሻሻል አንጻርም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል። በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ የሚጥለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚሰበሰቡ እና በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችልም ተጠቁሟል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች ወሳኝ ኩነቶቻቸውን በመደበኛው የምዝገባ ስርዓት በማስመዝገብ ህጋዊ እውቅናና ጥበቃ እያገኙ ነው ተባለ
ነሐሴ 15 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ስደተኞችና ጥገኝነት ጠያቂዎች የልደት፣ የጋብቻ፣ የፍቺ እና የሞት ወሳኝ ኩነቶቻቸውን በመደበኛው የምዝገባ ስርዓት በማስመዝገብ... read more
ለመንግስት ሰራተኞች ይጀመራል የተባለው የጤና መድህን አገልግሎት መዘግየት የፈጠረው ቅሬታ
https://youtu.be/OZqt6p_mlJA
መንግስት የጤና አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ሰፊ ስራ ሲሰራ ይስተዋላል። እነዚህ ተቋማት ጥራት ላይ እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በርካታ ቅሬታዎች... read more
በገና በዓል ከ50 በላይ አሸከርካሪዎች ጠጥተው ሲያሽከረክሩ መገኘታቸውና መቀጣታቸዉ ተገለጸ
ጥር 07 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ በ9ኙ ክፍለከተሞች በተመረጡ ቦታዎች በተካሄደ ቁጥጥር የአልኮል ትንፋሽ ምርመራ ከተደረገላቸው 1 ሺ... read more
የታሪካዊው የበሬ ፍልሚያ አመጽ ታገደ
ጥቅምት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሜክሲኮ ከተማ የሕግ አውጪዎች ባሳለፉት ታሪካዊ ውሳኔ፣ ለ500 ዓመታት ያህል የዘለቀውና በሬዎችን የሚጎዳውና የሚገድለው የባህላዊ የበሬ... read more
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቋሚ ኮሚቴዎች የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የልምድ ልውውጥ መርሐ-ግብር ነገ ያካሂዳሉ
ሚያዚያ 06 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴዎች የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት... read more
በማርበርግ በሽታ ከተያዙ 11 ሰዎች ውስጥ 6ቱ በበሽታው ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ
ሕዳር 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከህዳር 5/ 2018 ዓ.ም ጀምሮ የማርበርግ ህክምና ምርመራ ሲደረግ የቆየ ሲሆን በበሽታው ከተጠቁ 11 ሰዎች... read more
ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ የሰላም መልዕክታቸውን ለፕሬዝዳንት ፑቲን ሰጡ
ነሐሴ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ በግላቸው የጻፉትን ለሰላም ጥሪ የሚያደርግ ደብዳቤ... read more
ከቀውስ ቀጠናዎች እስከ ህልውና ፈተና፦ በኢትዮጵያ የስደተኞች የጤና፣ የመብት ከለላ እና የሰብዓዊ እርዳታ እጥረት አሳሳቢነት
በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በሚቀጥሉት ውጥረቶች፣ የሰላም እጦት እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በኢትዮጵያ መጠለያ ያገኙ ስደተኞች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገራቸው... read more
በቀጣይ አስር ቀናት ውስጥ የሚኖረው የአየር ንብረት በአትክልቶችና በሰብሎች እድገት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ አለዉ ተባለ
ታኅሳስ 03 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በሰሜን ምስራቅ፣ በምስራቅ፣ በመካከለኛዉና በደቡብ ደጋማ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የሌሊትና የማለዳዉ ቅዝቃዜ በአንጻራዊ ሁኔታ የሚጠናከር... read more
ቻይና በሰከንድ 30 ቢንቢዎችን የሚገድል የሌዘር መሣሪያ ሠራች
ሐምሌ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ የቻይና ኩባንያ በሰከንድ እስከ 30 ትንኞችን ወይም ቢንቢዎችን መግደል የሚችል አዲስ የሌዘር መሣሪያ... read more
ምላሽ ይስጡ