መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሚቴዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ያለፈውን የክረምት ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማ እና የበጋ ወቅት የአየር ጠባይ አዝማሚያ ይፋ የሚደረግበት መድረክ በዛሬው ዕለት አካሂዷል። ግምገማው የትንበያ ጥራትን፣ ተደራሽነትንና ተጠቃሚነትን ለማሻሻል የሚያግዙ አቅጣጫዎችን ለመለየት እድል የሚፈጥር በመሆኑ፣ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ሁኔታዎችን ቀድሞ ግንዛቤ እንዲኖር በማድረግ ተገቢ ዝግጅትና የምላሽ እርምጃ መወሰድ እንዳለበት የገለጹት የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር እና በዓለም ሚቴዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ አህጉር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፈጠነ ተሾመ ናቸው። በመድረኩ የ2018 ክረምት ወራት የዝናብ ስርጭት እና የነበሩ ተጽዕኖዎች፣ እንዲሁም የ2019 የበጋ የአየር ሁኔታ ትንበያ ይፋ ተድርጓል። በአብዛኛው የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን ከመደበኛ በላይ እንደሚሆን የኢንስቲትዩቱ የትንበያ መረጃ ጠቅሷል። ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ በሰሜን ምስራቅ፣ በመካከለኛው እና በምስራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ከ5 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች እንደሚሆን ተነስቷል። በአርብቶ አደር እና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች በበጋ ወቅት የሚከናወኑ የግብርና ስራዎችን ለማከናወን እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል። የውሃ አቅርቦትን ከማሻሻል አንጻርም ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተገልጿል። በሰሜን፣ በሰሜን ምስራቅ እና በምስራቅ የሀገሪቱ ስፍራዎች ላይ የሚጥለው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በሚሰበሰቡ እና በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችልም ተጠቁሟል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ኮንዶሚኒየም እና አፓርታማ ልዩነታቸው ምንድነው?
መስከረም 20 ቀን 2019 (መናኸሪያ ሬዲዮ) — በከተሞች እያደገ የመጣውን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለመመለስ ከሚገነቡት ዘመናዊ ሕንፃዎች መካከል ኮንዶሚኒየሞች እና... read more
ስፔን በወር አበባ ህመም ምክንያት የሚሰጥ የሚከፈልበት የክህሎት ፈቃድ መፍቀዷን አስታወቀች
መጋቢት 09 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ስፔን ከሥነ-ተዋልዶ ጤና ማሻሻያ ጋር በተያያዘ በከፍተኛ የወር አበባ ህመም ለሚሰቃዩ ሴቶች የሚከፈልበት የሕመም ፈቃድ... read more
ኦይል ሊቢያ እና ቶታል ኢነርጂስ፤ አሽከርካሪዎች ባሉበት ሆነው ወረፋ መያዝ የሚችሉበትን አሰራር መዘርጋታቸው ተገለጸ
ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ነዳጅ ለመቅዳት በርካታ አሽከርካሪዎች ረጃጅም ሰልፎችን መጠበቅ እየተለመደ መጥቷል በመላት ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ ይህን እንግልት... read more
የአፍሪካ ህብረት በዲሞክራቲክ ኮንጎ የመንግስት እና በኤኤፍሲ/ኤም23 እንቅስቃሴ መካከል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት አደነቀ
ሐምሌ 12 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር የሆኑት ማህሙድ አሊ ዩሱፍ፣ በዛሬው ዕለት በዶሃ፣ ኳታር በተካሄደው ስነ-ስርዓት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ... read more
የቁርጥ ቀኑ አርበኛ የሕይወት ፍፃሜ. . . ጀግናው በላይ ዘለቀ (አባኮስትር)
https://youtu.be/yas3ybFrj40
"አንች አገሬ ኢትዮጵያ! እውነት በድዬሽ ከሆነ ነፍሴን አይቀበላት። አልበደልኩሽ ከሆነም ወንድ አይብቀልብሽ!”
♻️ከ80 ዓመታት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት ጥር 5 ቀን... read more
በካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይ የሚመራው ሊብራል ፓርቲ የአገሪቱን አጠቃላይ ምርጫ ማሸነፉ ተገለፀ
ማርክ ካርኔይ እና ሊብራል ፓርቲ በካናዳ ምርጫ ድል እንደቀናቸው የተናገሩ ሲሆን፣ የዶናልድ ትራምፕ አቋም ለውጤቱ እንዳገዛቸው ተገልጿል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ... read more
sport
ቼልሲ የፕሪሚየር ሊግ የመክፈቻ መርሀ-ግብራቸው እንዲሸጋሸግ ለፕሪሚየር ሊጉ ያስገቡት ደብዳቤ ውድቅ ተደረገ
ሐምሌ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ... read more
ሳይንቲስቶች የመብረቅ አደጋን ተቋቁሞ የሚበቅል የዛፍ ዝርያ ማግኘታቸውን አስታወቁ
መብረቅ ከሚመታቸው ዛፎች መካከል አብዛኞቹ ይደርቃሉ፤ ነገር ግን ሳይንቲስቶች ከመብረቅ አደጋ የሚተርፉ ብቻ ሳይሆኑ በአደጋው ምክንያት የሚበቅሉ የዛፍ ዝርያዎች እንዳሉ... read more
በከተማዋ ደረሰኝ በማይቆርጡ ከ1 ሺህ በላይ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱ ተገለጸ
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ በንግድ ስርዓቱ ላይ የሚገኙ አካላት ህጋዊ ግብይት እንዲፈፅሙ ለማስቻል ደረሰኝ እንዲቆርጡ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
በዚህም መሰረት... read more
ትራምፕ ኦባማን በ2016ቱ የሩሲያ ምርመራ ክህደት ፈጽመዋል ሲሉ ወቀሱ
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ የ2016ቱን የሩሲያ የምርጫ ጣልቃ ገብነት ምርመራ አስመልክቶ የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማን... read more
ምላሽ ይስጡ