ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) እ.ኤ.አ. በኦገስት 1963 ዓ.ም በኦስትሪያ ቲሮል ክልል በሚገኘው ሱልዝታልፈርነር የበረዶ ግግር ላይ በወቅቱ የ23 ዓመት ወጣት የነበሩ ጀርመናዊ ተራራ ወጪ ከጓደኞቻቸው ጋር ጉዞ በማድረግ ላይ ሳሉ ድንገት ወደ ጥልቅ የበረዶ ስንጥቅ ውስጥ ይወድቃሉ። በወቅቱ አብረዋቸው የነበሩት አባላት በገመድ ጎትተው ለማውጣት እንዲችሉ እና የሰውነታቸውን ክብደት ለመቀነስ ሲሉ የያዙትን ቦርሳ ወደ በረዶው ስንጥቅ ውስጥ ለመጣል ተገደዱ። ከ63 ዓመታት በኋላ እ.ኤአ በኦገስት 2026፣ በቆላማው አካባቢ የበረዶው መቅለጥን ተከትሎ በቦታው የሚያልፍ አንድ ተራራ ወጪ ቦርሳውን እና የግል ሰነዶቻቸውን በበረዶው ላይ ተጋልጠው ያገኛቸዋል። የኦስትሪያ ፖሊስ አባላት በቦርሳው ውስጥ ከነበሩት ሰነዶች ላይ ስማቸውን በጥንቃቄ በማንበብ አሁን የ86 ዓመት አረጋዊ የሆኑትን የቦርሳውን ባለቤት ማግኘት ችለዋል። አረጋዊው ተራራ ወጪ በጤና ምክንያት በአካል ተገኝተው መረከብ ባለመቻላቸው፣ ፖሊስ ቦርሳውን እና በውስጡ የነበሩትን የታሪክ ማስታወሻዎች ለልጃቸው አስረክቧል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ