ነሐሴ 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኦገስት 28 ምሽቱን በኪየቭ ክልል በሚገኝ የመጻሕፍት መጋዘን ላይ ሩሲያ በሰነዘረችው የአየር ድብደባ ከ60,000 በላይ መጻሕፍት ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተገለጸ። የወደመው መጋዘን የReadеat እና የbook. ua የመጻሕፍት መደብሮች እንዲሁም የVivat፣ Osnovy፣ Uroboros፣ Khto Tse? እና Krapky አታሚዎች የነበሩ መጻሕፍት ተከማችተውበት የነበረ መሆኑ ታውቋል። የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪይ ሲቢሃ ድርጊቱን አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት፣ “ቀደም ሲል የሩሲያ ኢምፓየር የዩክሬን መጻሕፍትን ያግድ ነበር፤ ዛሬ ደግሞ የሩሲያ ድሮኖች መጻሕፍት የተከማቹባቸውን መጋዘኖች ያቃጥላሉ ፤የጦር መሳሪያዎቹ ቢቀየሩም ያው አባዜ እና ውድቀት ግን አልተቀየረም” ብለዋል። ሚኒስትሩ አክለውም የዩክሬን መጻሕፍት መታተማቸውን እና መነበባቸውን እንደሚቀጥሉ ገልጸው፣ የዩክሬን ባህል ይበልጥ እንደሚስፋፋና ሀገሪቱም ጸንታ እንደምትቆም አረጋግጠዋል። ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር ያለው ዋና ተግባር ሩሲያ ለማጥፋት የምትፈልገውን ሁሉ መጠበቅ እና የማጥፋት አቅሟን መቀነስ እንደሆነ የጠቆሙት ሲቢሃ፣ ዩክሬን ተጨማሪ የአየር መከላከያ ስርአቶች እንደሚያስፈልጓት እንዲሁም የሩሲያ የጦር ማሽን መሳሪያዎችን የማምረት እድሉ እና የሀብት ምንጩ ሊቀንስ እንደሚገባ አሳስበዋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ