ነሐሴ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሀገራቸው ከቬኔዙዌላ ጋር በዓለም ታሪክ ትልቁ የሆነውን የነዳጅ ስምምነት መፈረሟን ይፋ አድርገዋል። በፕሬዝዳንቱ መመሪያ መሠረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ እና የጦር ጉዳዮች ሚኒስትሩ ፒት ሄግሴዝ ከቬኔዙዌላው ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት ዴልሲ ሮድሪጌዝ እንዲሁም ከግል ኩባንያ ጋር በመተባበር ባደረጉት ስምምነት አሜሪካ ከ65 ቢሊዮን ባሬል በላይ የሚሆነውን የቬኔዙዌላ የነዳጅ ተቀማጭ ሀብት በአብዛኛነት እንድትቆጣጠር አስችለዋል። ይህ ታሪካዊ ስምምነት ለአሜሪካ ግብር ከፋዮች ምንም አይነት ወጪ ሳያወጣ የአሜሪካን የነዳጅ ተቀማጭ ሀብት ከሁለት እጥፍ በላይ እንደሚያሳድገው ተገልጻል። በተጨማሪም የአሜሪካን የነዳጅ አቅርቦት በከፍተኛ ደረጃ በመጨመር ለረጅም ጊዜ የሚዘልቅ የነዳጅ ዋጋ ቅናሽ እንደሚያስገኝ ይጠበቃል። በሌላ በኩል ስምምነቱ ቬኔዙዌላን ወደ ታላቅ እድገት እና ብልጽግና በሚወስደው ጎዳና ላይ የሚያግዛት ከመሆኑም በላይ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ፕሬዝዳንት ትራምፕ አስታውቀዋል። _ ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
የመንግስታቱ ድርጅት የሰላም አስከባሪ አዛዥ የM-23 አማፂ ቡድን ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እንዲወጣ ጥሪ አቀረቡ
የፀጥታው ምክር ቤት የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን ኢላማ ያደረገውን ጥቃት ለማስቆም 'በፍጥነት' እርምጃ መውሰድ ይገባል ሲሉ ዣን ፒየር ላክሮይ-ክስ ተናግረዋል።
የመንግስታቱ ድርጅት... read more
በኔፓል የሚገኙ የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ከ1,600 በላይ ተማሪዎችን ከከፋ የጎርፍ አደጋ ታደጉ
ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኔፓል ኑዋኮት አውራጃ በሚገኘው ትሪቡቫን ትሪሹሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ47 ዓመቱ ርዕሰ መምህር ራጄንድራ... read more
ስልጣን ሊረከቡ የሳምንታት እድሜ የቀራቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገሪቱ የገቡ ስደተኞችን እንደሚያባርሩ ገለጹ
ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከአሜሪካው ”NBC” ቴሌቪዥን ጋር ታናንት ቃለ መጠይቅ የነበራቸው ተመራጩ ፕሬዝዳንት በምርጫ ቅስቀሳቸው ቃል በገቡት መሰረት... read more
አሜሪካ የሱዳኑን ፈጥኖ ደራሽ ሃይል በአገሪቱ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል በሚል ከሰሰች
ጥር 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሜሪካ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል (RSF) የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈጽሟል ከሚለው ክስ ባለፈ የቡድኑ መሪ... read more
ቦሪስ ጆንሰን እና ከፍተኛ የአውሮፓ ባለስልጣናት የባቡር ጣቢያውን ለቀው ከተጓዙ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሩሲያ የሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን) የዩክሬን ባቡር ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተገለጸ
መስከረም 04 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዩክሬን እና በፖላንድ ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው የያሆዲን የባቡር ጣቢያ ላይ የሩሲያ ድሮን ጥቃት ማድረሱ ተገለፀ።... read more
ኪሊያን ምባፔ 10 ቀን ከሜዳ እንደሚርቅ ተገልጿል
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ፈረንሳዊው ኮኮብ ኪሊያን ምባፔ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የምድብ 6ኛ ጨዋታ ጣልያን ቤርጋሞ ላይ ሪያል ማድሪድ... read more
ሰበር መረጃ …. የየመን ሁቲ አማፂያን በዓለም አቀፉ የባህር ትራንስፖርት መስመር ላይ የምትገኘውን ስትራቴጂካዊ ደሴት ተቆጣጠሩ
መስከረም 1 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የየመን ሁቲ አማፂያን በቀይ ባሕርና በኤደን ባህረ ሰላጤ መካከል በሚገኘውና ለዓለም አቀፍ የንግድ መርከቦች ወሳኝ... read more
የናይጄሪያ ጦር 34 አሸባሪዎች እንደገደለና ፣ 6 ወታደሮች እንደተገደሉበት አስታወቀ
ጥር 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በናይጄሪያ ሰሜናዊ ምስራቅ በናይጄሪያ ጦር እና እስላማዊ መንግስት ምዕራብ አፍሪካ ግዛት መካከል በተቀሰቀሰው የትጥቅ ግጭት... read more
ታሪካዊ የህክምና ስኬት፡ ለ24 ሰዓታት በቆየ ቀዶ ጥገና ተያይዘው የነበሩት ኢትዮጵያውያኑ ህፃናት ህያብ እና ውህብቶ ተለያዩ
መስከረም 09 ቀን 2019 ዓ.ም. (መናኸሪያ ሬዲዮ) — በህክምናው ዓለም እጅግ ውስብስብ ከተባሉት ክስተቶች አንዱ የሆነው የቀዶ ጥገና ሂደት ስኬታማ... read more
በሰባት የአሜሪካ ክፍለ ሀገራት የሚገኙ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የመረጃ ማዕከላት የውሃ ፍጆታ ከካሊፎርኒያ ከተሞች መብለጡ ተገለጸ
ነሐሴ 23 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአሜሪካ በሚገኙ ሰባት ክፍለ ሀገራት ውስጥ የሚሰሩ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና የቴክኖሎጂ የመረጃ ማዕከላት (Data... read more
ምላሽ ይስጡ