ነሐሴ 20 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የለንደኑ ክለብ ቼልሲ እና ኖቲንግሃም ፎረስት በ23 ዓመቱ እንግሊዛዊ አጥቂ ሊያም ዴላፕ ዝውውር ዙሪያ ሙሉ ስምምነት ላይ ለመድረስ ተቃርበዋል።
ባለፈው ክረምት ከኢፕስዊች ታውን በ30 ሚሊዮን ፓውንድ ስታምፎርድ ብሪጅን የተቀላቀለው ዴላፕ፣ በቼልሲ ቤት ባሳለፈው የመጀመሪያ የውድድር ዘመን በጉዳት እና በአሰልጣኞች መቀያየር ምክንያት በቂ የመጫወት እድል ሳያገኝ ቀርቷል።
ቼልሲዎች መጀመሪያ ላይ ለተጫዋቹ እስከ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ይፈልጉ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን ዝውውሩን በ45 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ለማጠናቀቅ ፈቃደኛ ሆነዋል። ታይዎ አዎኒዪን በ9 ሚሊዮን ፓውንድ ለኮቨንትሪ ሲቲ የሸጡት ኖቲንግሃም ፎረስቶች፣ በኦሊቨር ግላስነር ስር የፊት መስመራቸውን ለማጠናከር ዴላፕን ዋነኛ ኢላማቸው አድርገውታል።
ኤቨርተኖችም በተጫዋቹ ላይ ፍላጎት ቢኖራቸውም፣ ዴላፕ በፕሪሚየር ሊጉ የመቆየት ፍላጎት ያለው በመሆኑ እና ፎረስትም ድርድሩን በመግፋቱ የሕክምና ምርመራውን አጠናቆ ይፋዊ ውል ይፈራረማል ተብሎ ይጠበቃል።
ጉዳት እንዲሁም የአሰልጣኞች መቀያየር ተጫዋቹ በብሪጅ የነበረውን ቆይታ ከባድ አድርገውታል። በቼልሲ ማልያ በፕሪሚየር ሊጉ 1 ጎል ብቻ ነው ማስቆጠር የቻለው። ባጠቃላይ በቼልሲ ቆይታው ባደረጋቸው 47 ጨዋታዎች 3 ጎሎችን ብቻ ነው ማስቆጠር የቻለው።
በ24 ዓመቱ ላይ የሚገኘው እንግሊዛዊው አጥቂ የኖቲንጋም ፎረስት የሪከርድ ግዢ ሆኖ ወደ ሲቲ ግራውንድ የሚያመራ ሲሆን፣ ወጥነት ባለው መንገድ ኳስ እና መረብን ለማገናኘት የሚችልበት ወሳኝ የዕድሜ ክልል ላይ ስለሚገኝ ዕድሉን በሚገባ በሲቲ ግራውንድ ይጠቀማል ተብሎ ይገመታል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ማንነትን መሰረት አድርገው እየቀረቡ ያሉ ጥያቄዎችን በተመለከተ እየተደረጉ ያሉ ጥናቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸዉ ተጠቆመ
የማንነት እና የወሰን ጥያቄዎች ከተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች እየተነሱ መሆኑን ተከትሎ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የተለያዩ ጥናቶችን እያስደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡
መናኸሪያ ሬዲዮ ያነጋገራቸው... read more
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ አገራት እንደ ማዕድን ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶች ስለምን የግጭት የስዕበት ማእከል ሆኑ? በአስተዳደር እና የህግ ማዕቀፍ ችግር ወይስ የተፈጥሮ ሀብቱ በባህሪው ግጭትን ሳቢ ስለሆነ?
አፍሪካ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ቢኖራትም ሀብቱን ለልማት አውሎ የዜጎችን ሕይወት መቀየር፤ አህጉሪቱንም ከድህነት ማውጣት ግን አለመቻሉን የአህጉሪቱን ጉዳይን በቅርበት የሚከታተሉ... read more
ሳይንቲስቶች የዓለምን የቆሻሻ ችግር ለመፍታት “ሱፐር ዝንቦችን” በዘረመል እየቀየሩ ነው ተባለ
👉ዝንቦቹ የሰዎችን እዳሪ በመብላት ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የሚሞቱ ናቸው ተብሏል።
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዓለምን የቆሻሻ ችግር ለመፍታት ሳይንቲስቶች በዘረመል የተቀየሩ... read more
የዩ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ. መቋረጥ በኢትዮጵያ ላይ የደቀነው አደጋ
https://youtu.be/2kwjgk-Qmdc
read more
የሞባይል አፕሊኬሽኖች የሳይበር ወንጀለኞች ሰፊ ኢላማ እየሆኑ ነው ተባለ
የሞባይል መተግበሪያዎች (ሞባይል አፕሊኬሽኖች) የግል መረጃዎችን በስፋት በመያዛቸው የሳይበር ወንጀለኞች ዋነኛ ኢላማ እየሆኑ መምጣታቸውን የዘርፉ ባለሙያዎች አስጠነቀቁ።
በተለይም የአይኦኤስ (iOS) ስልኮች... read more
በቴሌግራም የተደራጀ የወሲብ ወንጀል መሪ በደቡብ ኮሪያ የዕድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት
ሕዳር 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በደቡብ ኮሪያ፣ በታዋቂው የቴሌግራም መተግበሪያ ላይ የጾታ ወንጀል ድርጊቶችን ሲያደራጅ የነበረው የወንጀል ቡድን መሪ የዕድሜ ልክ... read more
በጥርስ እና ጸጉር ንቅለ ተከላ ዙሪያ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከልክ በላይ የተጋነኑ በመሆኑ ቁጥጥር እና እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው ተባለ
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የንግድ ውድድሩን ተከትሎ የጤና ተቋማት አማላይ ማስታወቂያዎችን በማስነገር ህብረተሰቡን ወደ ተሳሳተ እይታ እየመሩት ነው ያለው... read more
ከ152 ሺህ በላይ የደንብ መተላለፎች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱ ተገለጸ
ጥር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከ27 ተቋማት ጋር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎችን ከባለድርሻ አካላት ጋር... read more
የሃይሌ ኃይሎች መጽሐፍ ተመረቀ
ሰኔ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የሕይወት ፍልስፍና ላይ ያተኮረ መጽሐፍ በሴት ልጁ፣ ፀሐፊ ሜላት ኃይሌ ተጽፎ ለንባብ... read more
ቻይና ለ50 ዓመታት ቻርጅ የማያስፈልገው የሳንቲም መጠን ያለው የኒውክሌር ባትሪ ፈጠረች
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቻይና የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችና የምርምር ተቋማት የኃይል አቅርቦትን ትርጉም የሚቀይር አስደናቂ ግኝት ይፋ አደረጉ። በቤታቮልት (Betavolt)... read more
ምላሽ ይስጡ