ጥቅምት 23 ቀን 2019(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሜሪካ፣ ደቡብ ኮሪያ እና ጃፓን የሰሜን ኮሪያን የኒዩክለር መሣሪያዎች ሙሉ በሙሉ የማስወገድ እና ቀጠናዊ መረጋጋትን የማረጋገጥ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን በድጋሚ ይፋ አድርገዋል።
የሶስቱ ሀገራት ከፍተኛ የዲፕሎማሲ እና የደህንነት ባለስልጣናት ቅዳሜ ዕለት ባወጡት የጋራ መግለጫ፣ የሰሜን ኮሪያን “ሙሉ በሙሉ ከኒዩክለር ነፃ የማድረግ” (complete denuclearization) ግባቸው ጸንቶ እንደሚቀጥል አፅንኦት ሰጥተዋል።
ይህ ውሳኔ የተሰማው ፒዮንግያንግ ከዋሺንግተን ጋር ሊደረግ የሚችለውን ዲፕሎማሲያዊ ውይይት ተንተርሶ የሚቀርብለትን ትጥቅ የመፍታት ጥሪዎች አበክሮ ውድቅ ማድረጓን በቀጠለበት ወቅት መሆኑ ተመላክቷል።
በቀጠናው እየጨመረ የመጣውን የኒዩክለር እና የባለስቲክ ሚሳኤል ስጋት ለመግታት የተቋቋመው የሶስትዮሽ ጥምረት፤ ሰሜን ኮሪያ የሀገራትን ሰላም እና ፀጥታ አደጋ ላይ የሚጥሉ ድርጊቶቿን እንዲያስቆም የተቀናጀ ዲፕሎማሲያዊ ግፊት እና የጸጥታ ጥበቃ እርምጃዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ