መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 2.9 ሚሊየን ድጋፍ የሚሹ ተረጂዎች እንዳሉ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን መረጃ አመላክቷል። የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ በድንገተኛ አደጋዎች ጊዜ የውጭ እርዳታ ጥገኛ ከመሆን ይልቅ በሀገር ውስጥ አቅም ፈጣን ምላሽ ለመስጠት በአዋጅ የተቋቋመ የገንዘብ ማሰባሰቢያ ሥርዓት መሆኑ ይታወቃል። ፈንዱ ከቴሌኮም እና ባንክ አገልግሎቶች ክፍያ፣ ከሎተሪ አገልግሎት፣ ከአክስዮን ክፍፍል፣ ከኬሚካል ሽያጭ፣ ከፓስፖርት፣ ቪዛ፣ ንግድ ፈቃድ አገልግሎቶች እና ከሌሎችም አማራጮች የሚሰበሰብ ነው። በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን ስር በሚተዳደረው በዚህ “የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ” በ6 ወር ውስጥ 15.5 ቢሊየን ብር እንደተሰበሰበ ኮምሽኑ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ተገልጿል። ከተሰበሰበው የገንዘብ መጠን ውስጥ 4.9 ቢሊየን ብር ለአደጋ ጊዜ ምግብ ግዢ እንደዋለም ተገልጿል። በኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን መረጃ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ 2.9 ሚሊየን ድጋፍ የሚሹ ተረጂዎች ያሉ ሲሆን፣ በአደጋ ስጋት ምላሽ የሚሰበሰበው ፈንድ እነርሱን ለመደገፍ አገልግሎት ይውላል ተብሏል። ይሁን እንጂ አንዳንድ የአገር ውስጥ እና የውጭ ድርጅቶች የግል ጥቅማቸውን ማዕከል በማድረግ በኢትዮጵያ ያሉትን የተረጂዎች ቁጥር አጋነው እንደሚያቀርቡ ተመላክቷል። በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ተጠቃሚ ተብለው የተለዩ የህብረተሰብ ክፍሎች:- የእለት ደራሽ እርዳታ ፈላጊዎች፣ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች፣ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተፈናቀሉ፣ ጎዳና ተዳዳሪዎችና በየቦታው የሚኖሩ ዜጎች፣ የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚዎች እንዲሁም የኢኮኖሚ ችግር ያለባቸው የስደት ተመላሾች መሆናቸው ተገልጿል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በተከሰተ ግጭት የኢራኗ ቀሸም ደሴት በነዳጅ ተበከለች
ነሐሴ 06 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)በሆርሙዝ ሰርጥ አቅራቢያ በተካሄደ ወታደራዊ ግጭት ሳቢያ የተመቱ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ባስከተሉት ተደጋጋሚ የነዳጅ መፍሰስ... read more
አባት አርበኞች ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር ቁርጠኛ መሆናቸውን ገለጹ
ትውልዱም የሀገርን ዳር ድንበር በውል ማወቅና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መከበር ውግንናውን ማሳየት እንዳለበት አስታውቀዋል፡፡
አባት አርበኞች ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ጥቅም መከበር አሁንም... read more
ዩናይትድ ስቴትስ የፍልስጤምን እውቅና በተመለከተ የፈረንሳይን ዕቅድ ‘በፅኑ እንደምትቃወም’ ገለጸች
👉ሳውዲ አረቢያ ግን 'ታሪካዊ ውሳኔ' ስትል አመሰገነች::
ሐምሌ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አሜሪካ ፍልስጤምን እንደ መንግስት እውቅና ለመስጠት የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን... read more
የተፈናቃይ ዜጎችን ቁጥር ለመቀነስ ለዜጎች ደህንነትና ጥበቃ የሚሰጥ መዋቅር መዘርጋት እንደሚገባ ተጠቆመ
ኅዳር 30 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሰሞኑ ተቀማጭነቱን በጄኔቫ ያደረገው የሀገር ውስጥ መፈናቀል መከታተያ ማዕከል ባወጣው ሪፖርት በአፍሪካ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር... read more
በሱዳን የስደተኞች መጠለያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ከሚሰነዘርባቸው ጥቃት ለማምለጥ እንዳልቻሉ እየገለጹ ነው
ነገ ሁለተኛ ዓመቱን የሚይዘው የእርስ በእርስ ጦርነት ከ12 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያፈናቀለ ሲሆን የዓለማችንን አስከፊ የረሀብ አደጋም ደቅኖባቸዋል፡፡
አሁን ደግሞ በምዕራባዊ... read more
ቻይና በ110 ቀናት ውስጥ የአለማችን ሰፊውን የውሃ ውስጥ ዋሻ በመገንባት ክብረወሰን አስመዘገበች
ሐምሌ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ቻይና በ110 ቀናት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የአለማችንን እጅግ ሰፊ የውሃ ውስጥ ዋሻ በመገንባት አዲስ ክብረወሰን... read more
ዓለም አቀፍ የሕክምና ስኬት፡ በደቡብ ኮሪያ በ3D ሰው ሰራሽ የንፋስ ቧንቧ በተሳካ ሁኔታ ታተመ
መስከረም 29 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ደቡብ ኮሪያዊያን ተመራማሪዎች በዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ ታላቅ የሕክምና ምዕራፍ አስመዝግበዋል። የጉሮሮ ካንሰር ቀዶ ሕክምና ወቅት የንፋስ... read more
በመዲናዋ እየተካሄደ ያለው 13ኛው የአፍሪካ ኢንተርኔት አስተዳደር ጉባኤ ከኢንተርኔት አጠቃቀምና ቁጥጥር ጋር በተያያዘ ለሚወጡ ህጎች አጋዥ እንደሚሆን ተገለጸ
ኅዳር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለመጀመሪያ ጊዜ በሃገራችን እየተካሄደ ባለው ጉባኤ ከተለያዩ ሃገራት የተወጣጡና በዘርፉ ያሉ ባለድርሻ አካላት ከኢንተርኔት አስተዳደር፤... read more
ለጎረቤት ሀገራት ጠብ አጫሪ እንቅስቃሴዎች ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ ያስፈልጋል ተባለ
በኢትዮጵያና ኤርትራ ህዝቦች መካከል ያለዉን አዎንታዊ ግንኙነት በሚያሳይ መልኩ እና በኤርትራ በኩል ያለውን ነባራዊ ጠብ ቀስቃሽ እንቅስቃሴ ብስለት በሚስተዋልበት ዲፕሎማሲያዊ... read more
ምላሽ ይስጡ