መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ ዌስት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ (Addis West Substation) ላይ ባጋጠመ ድንገተኛ የትራንስፎርመር ብልሽት ምክንያት በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አንዋር አብራር ገልጸዋል። በዚህ ድንገተኛ ብልሽት ሳቢያ በእህል በረንዳ፣ አውቶብስ ተራ፣ አዲስ ከተማ ትምህርት ቤት፣ ገነሜ ትምህርት ቤት፣ አማኑኤል ቤተክርስትያን ፊትለፊት፣ አዲሱ ሚካኤል እና አካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጧል። በተጨማሪም በመሳለሚያ፣ አበበ ቢቂላ ስታዲየም፣ ኳስ ሜዳ፣ ግሩም ሆስፒታል፣ ታይዋን ገበያ ማዕከል እና አካባቢው እንዲሁም በአማኑኤል ሆስፒታል ፊት ለፊት፣ ሰባተኛ፣ ድሬ ሕንጻ ፊት ለፊት፣ ኮልፌ 18 ጤና ጣቢያ እና አካባቢው የኃይል መቋረጡ አጋጥሟል። በተመሳሳይ ሁኔታ በፈጥኖ ደራሽ፣ ኮልፌ ኮምፕሬሄንሲቭ ትምህርት ቤት፣ ኮልፌ 18 ማዞሪያ፣ ኢትዮ ጠቢብ ሆስፒታል እና አካባቢው፣ በኮልፌ መናፈሻ፣ ፊሊጶስ፣ ኮልፌ ጤና ጣቢያ (በከፊል)፣ ሎሚ ሜዳ፣ ኢንዱስትሪ መንደር፣ አዲስ ዌስት ሰብስቴሽን እና አካባቢው አገልግሎቱ ተቋርጦ ይገኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቀራንዮ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን፣ ቤተል ሆስፒታል፣ ቤተል ቢጫ ፎቅ፣ መስጅድ፣ ቤተል ፓስታ ቤት እና አካባቢው፣ በሆላንድ ኤምባሲ፣ የሺ ደበሌ፣ ጦር ኃይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን፣ ቻይና ኤምባሲ፣ አውጉስታ ጽዮን ማርያም ቤተክርስቲያን፣ አባ ጅፋር መስጅድ እና አካባቢው እንዲሁም በወይራ ሰፈር፣ ወይራ ኮንዶሚኒየም፣ ሞቢል፣ የቀድሞው ራሺያ ካምፕ፣ ተዘንአ ሆስፒታል፣ አውጉስታ፣ ወይብላ ማርያም፣ ጦር ኃይሎች ጎልፍ ክለብ እና አካባቢው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቋርጦ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የጥገና ባለሙያዎች ብልሽቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማስተካከል አገልግሎቱን ወደ ነበረበት ለመመለስ በትኩረት እየሠሩ ይገኛሉ። ተቋሙ ያጋጠመውን ድንገተኛ የኃይል መቋረጥ በማስመልከት ወቅታዊ መረጃዎችን በቀጣይ በይፋዊ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቹ የሚያሳውቅ ሲሆን፣ የጥገና ሥራው ተጠናቆ የኃይል አቅርቦቱ እስኪመለስ ድረስ ክቡራን ደንበኞቹ በትዕግሥት እንዲጠባበቁ በአክብሮት ጠይቋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የነዳጅ ዋጋ ጭማሪን ተከትሎ አሽከርካሪዎች የሚያደርጉት የታሪፍ ማሻሻያ ሕገ-ወጥ መሆኑ ተገለፀ
ሚያዚያ 29 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) ከሰሞኑ የተደረገውን የነዳጅ ዋጋ ጭማሪ ተከትሎ፣ የትራንስፖርት ታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ እስካሁን ምንም ዓይነት ውሳኔ... read more
ጉግል ማጭበርበርያ ድረ-ገጾችን ለመለየት አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መጠቀም ጀመረ
ጉግል በ Chrome ማሰሻው፣ በፍለጋ አገልግሎቱ እና በአንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ላይ የማጭበርበር ተግባራትን ለመከላከል አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መጠቀም መጀመሩን አስታወቀ።
የኩባንያው... read more
ኢትዮጵያ የፕላስቲክ ምርት ማምረት ካቆመች እስከ 50 ቢሊየን ብር በዓመት እንደምታጣ ተጠቆመ
ሰኔ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ለአካባቢ ብክለት የሚዳርጉ እና አንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ የሚውሉ ምርቶች በሥነ ምህዳር ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት... read more
የኮሪደር ልማቱ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መሆን እንዳለበት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮምሽን ገለጸ
የካቲት 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የክልል ከተሞች የሚገነባው የኮሪደር ልማት ለአካል ጉዳተኞች ምቹ መሆን እንደሚገባው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ... read more
የሰላም ካውንስሉ የክልሉን ቀውስ ለመፍታት የሄደበት ርቀት አመርቂ አለመሆኑ ተገለጸ
Conflict Management and African Politics በሚለው መጽሃፉ ላይ ቴረንስ ላዮንስ ሲጠቅስ ፡ የአመለካከት ልዩነት፣ መቃረን፣ አለመግባባት ወይም መረጋጋትና አንድነትን የሚያጠፋና ያጠፋ እንደሆነ... read more
ግብጽ ኢትዮጵያ ላይ መሠረተ ቢስ ክስ የምትመሰርተው በሰላማዊ መንገድ ዕድገቷን እንዳይፋጠን ለመገደብ መሆኑን ባለሙያዎች ገለጹ
መስከረም 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ግብፅ በየጊዜው አጀንዳ እየቀያየረች ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ የምታሳስተው፣ ኢትዮጵያ እና የተፋሰሱ አገራት በሕዳሴው ግድብ እና... read more
በባቡር ሀዲዶች ላይ የሚነሰነሱት ሻካራ ድንጋዮች ምስጢር
ሰኔ 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በየቀኑ በከተማችንም ሆነ በተለያዩ አካባቢዎች የባቡር ሀዲዶችን ስንመለከት፣ በሀዲዶቹ ስር እና ዙሪያ እጅግ በጣም ብዙ... read more
ኢትዮ ቴሌኮም ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንደሚያስፈልገው ገለጸ
ታኅሳስ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተያዘው በጀት ዓመት በተለያዩ ገጠራማ የሃገሪቱ ክፍሎች ለአገልግሎት ማስፋፊያ ስራ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንሚያስፈልግ... read more
በማይናማር የሚገኙ ዜጎችን ማስመለሱ ቢቀጥልም አሁንም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ዜጎች መበራከታቸው ተገልጿል
በማይናማር የሚገኙ ዜጎችን ማስመለሱ ቢቀጥልም አሁንም በህገ ወጥ መንገድ ወደ ስፍራው የሚያቀኑ ዜጎች መበራከታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ... read more
እንደ ሃገር የመሬት ሚኒስቴር ቢቋቋም የሚል ምክር ሃሳብ ቀረበ
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የከተማ መሰረተ ልማት እና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ እሸቱ ተመስገን(ዶ/ር) እንደ ሀገር የመሬት... read more
ምላሽ ይስጡ