መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚው በአቶ አንዋር አብራር በኩል ባወጣው ይፋዊ የሚዲያ መግለጫ፣ ፍትሃዊ የኤሌክትሪክ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ባከናወነው ሰፊ ሥራ በጉራጌ ዞን በእኖር እና እዣ ወረዳዎች የሚገኙ 19 የገጠር መንደሮችን በበዓሉ ዋዜማ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረጉን አስታውቋል። ቀድሞም ቢሆን በደማቅ የመስቀል በዓል አከባበሩ የሚታወቀው አካባቢው፣ አሁን ደግሞ በእነዚህ መንደሮች ኤሌክትሪክ መግበቡ የበዓሉን አከባበር ይበልጥ ያሳምረዋል ተብሏል። ይህን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ለማከናወን ከ132 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገ ሲሆን፣ ለሥራው ስኬትም 25.92 ኪሎ ሜትር መካከለኛ እና 38 ኪሎ ሜትር ዝቅተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ተከናውኗል። በፕሮጀክቱ 2 ሺህ 295 የሚጠጉ ቆጣሪዎች የተገጠሙ ሲሆን፣ በአንድ ቆጣሪ አማካይ 5 የቤተሰብ አባላት ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ በተሰላው መሠረት 11 ሺህ 475 ዜጎችን የመብራት ባለቤት ማድረግ ተችሏል። በተጨማሪም ከወጣው አጠቃላይ ወጪ ውስጥ 40 ሚሊዮን የሚሆነው በሕብረተሰቡ ቀጥተኛ ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት የተሸፈነ መሆኑ የሕዝብና የተቋሙን አብሮነት ድንቅ ማሳያ እንደሆነ ተገልጿል። ይህ የልማት ሥራ የአካባቢውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ በማነቃቃትና በማሳደግ ረገድ ትልቅ ሚና ከመጫወቱም በላይ፣ የዘንድሮውን የመስቀል በዓል ለነዋሪዎቹ ልዩ እንደሚያደርገው ይጠበቃል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ከሶማሌ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተሰጠ መግለጫ!
መስከረም 07 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአሜሪካ ኤምባሲ ዶሎ ዞንን በተመለከተ ያወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያ በአካባቢው ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አያንጸባርቅም! የሶማሌ ክልል... read more
ኢትዮጵያ ከዉጭ ስታስገባ የነበረዉን የቃጫ ምርት እስከ 40 በመቶ መቀነሷ ተገለጸ
ኢትዮጵያ በእንሰት ምርት የምትታወቅ እና አምራች ሃገር ብትሆነም ከእንሰት ምርት የሚገኘዉን እና ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚዉለዉን ቃጫ በዉጭ ምንዛሬ ከዉጭ ስታስገባ... read more
በመዲናዋ የሚተከሉ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃዎች ለስርቆት እንዳይጋለጡ በማይቀልጡ ቁሶች እንዲተኩ እየተደረገ ነው ተባለ
ጥቅምት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በመዲናይቱ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ስታንዳርዱን የጠበቀ የቆሻሻ መጣያ (ደስት ቢን) እንዲተከል ምቹ ሁኔታ የፈጠረ... read more
የጤና አግልግሎት በመስጠት 25 ዓመታትን ያስቆጠረው አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል የህክምና ጥራትን በማስጠበቅ ረገድ ሚናው ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በ1992 ዓ.ም የተቋቋመው አዲስ ህይወት አጠቃላይ ሆስፒታል የተለያዩ የጤና አገልግሎቶችን በመስጠት 25 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን የህክምና አሰጣጥ ጥራቱን በማሻሻል አሁን... read more
ሰሜን ኮሪያ 5,000 ቶን የሚመዝን #አጥፊ የጦር መርከብ በሚቀጥለው ጥቅምት ልትገነባ ነው
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ሰሜን ኮሪያ ሶስተኛውን 5,000 ቶን የሚመዝነውን የቾይ ህየን (Choe Hyon) ክፍል የጦር መርከብ በገዢው ሰራተኞች ፓርቲ... read more
ተቅማጥና ትውከት በሽታ
በጋምቤላ ክልል ኑዌር ብሔረሰብ ዞን አራት ወረዳዎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ ተከሰተ
🔰በአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ የዘጠኝ ሰው ሕይወት ሲያልፍ 136... read more
በመዲናዋ መዝናኛ ቦታዎች የሚሰሩ ሰራተኞች ቅሬታ
https://youtu.be/en9ekzIubDw
read more
ከደረሰኝ ጋር የተገናኙ ጠቅላላ ወንጀሎች
👉ማንኛውም ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ ያለበት ታክስ ከፋይ ያለደረሰኝ ግብይት ያከናወነ እንደሆነ ከብር 25ሺ (ሃያ አምስት ሺ ብር) እስከ ብር 50... read more
የዲሞክራሲ ተቋማት ላይ እንዲሰሩ የሚመረጡ አመራሮች የኋላ ታሪካቸው ከዘርፉ ጋር ሊገናኝ እንደሚገባ ተገለጸ
አመራሮቹ ለሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መከበር የሚኖራቸው ሚና እንዲሁም የሚጣልባቸው ሃላፊነት የህዝብ አደራ በመሆኑ ከሃላፊነቱ በፊት በዘርፉ ላይ የኋላ ታሪክ... read more
የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኢንስቲትዩት የዚህ አመት ምዝገባ እስከ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ተገለጸ
መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ፀዳለ ተክሉ የዚህ ዓመት የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ምዝገባ... read more
ምላሽ ይስጡ