መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል “ቦረዳ ወረዳ” የድንጋይ ከሰል ማምረትና ማጠብ ሥራ ላይ የተሰማራው ዮ ሆልዲንግ፣ አሁን ላይ በሀገር ውስጥ ያለውን የድንጋይ ከሰል ፍላጎት ሙሉ በሙሉ ለመሸፈን እየሠራ መሆኑን የዮ ሆልዲንግ መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ መኮንን ዓለሙ ገልጸዋል። በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነውና በጋምቤላና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች ውስጥ በድንጋይ ከሰል ምርት የተሰማራው ዮ ሆልዲንግ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ለኃይል ይጠቀሙበት የነበረውን የከሰል ግብዓት ከውጭ በውጭ ምንዛሬ ያስመጡ እንደነበር ተናግረዋል። የዮ ሆልዲንግ የድንጋይ ከሰል ማምረቻና ማጠቢያ አሁን ላይ ወደ 70 በመቶ ለሚሆኑ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ምርቱን እንደሚያቀርብ አቶ መኮንን ገልጸዋል። ዮ ሆልዲንግ በጋምቤላና በደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ፋብሪካው በቀን ከ400 ቶን በላይ የሚያመርት ሲሆን፣ የማምረት አቅሙም በየዓመቱ እየጨመረ በመሄዱ የሀገር ውስጥ ፍላጎትን ለማሟላት እየተሠራ መሆኑን አክለዋል። ፋብሪካው በዓመት ውስጥ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ያላነሰ የድንጋይ ከሰል ምርት የሚያመርት ሲሆን፣ በቀጣይ 2 ተመሳሳይ ፋብሪካዎችን ለመገንባት እንደታቀደና ከኬንያ ጀምሮ ወደ ጎረቤት ሀገራት ለመላክ በዝግጅት ላይ መሆኑን አስታውቀዋል። ዮ ሆልዲንግ ቋሚና ጊዜያዊ ሠራተኞችን ጨምሮ ከ500 እስከ 700 ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል ተብሏል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በቲክቶክ ቪዲዮ የፕሬዝዳንቱን ክብር አዋረዱ የተባሉ ወጣቶች በቁጥጥር ስር ዋሉ
መስከረም 07 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ሁለት የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ፕሬዝዳንቱን የሚያወግዝ ዳንስ በመደነስ የቀረጹትን በማህበራዊ ሚዲያ... read more
የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ በArtificial Intelligence ለማዘመን ያለመው ግዙፉ “ሁዋዌ ፋይናንስ ሰሚት 2026” በአዲስ አበባ ተካሄደ
ሰኔ 16 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የዓለማችን የቴክኖሎጂ ተቋም የሆነው ሁዋዌ (Huawei Ethiopia Enterprise Business Group) የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ወደ ዲጂታል... read more
“የቆዳ ባንክ/ልገሳ በኢትዮጵያ መጀመር አለባት”የቃጠሎ ህክምናን ባለሙያዎች
ሰብዓዊ ፍጡር የሆነው የሰው ልጅ በተፈጥሮው በርካታ ድንቅ ስጦታዎች ተሰጥተውታል። ከእነዚህም መካከል ትልቁና የመጀመሪያው የሰውነት አካል የሆነው ቆዳው ነው።
የሰውነት ቆዳ... read more
በጊቤ ብሄራዊ ፓርክ የሚደረገውን ህገ-ወጥ ወረራ ለመከላከል ፖለቲካዊ ወሳኔዎችን የሚሹ ጉዳዮች መኖራቸው አፈጻጸሙን እንዲጓተት አድርጎታል ተባለ
ታኅሳስ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን በጊቤ ብሄራዊ ፓርክ ዙሪያ ሰፍረው፣ ፓርኩ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሰዎችን ለማንሳት... read more
የወንድ ብብት ላብ በሴቶች ሆርሞኖች እና ስሜት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አዲስ ጥናት አመለከተ
ሐምሌ 28 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በቅርቡ በሳይንሳዊ ዘርፍ የተደረገ አንድ ጥናት አስገራሚ ግኝት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ እንደሚያመለክተው፣ ከወንዶች ብብት ላብ ውስጥ... read more
የውጭ አገር ዜጎች በኢትዮጵያ የመኖሪያ ቤት ባለቤት የሚሆኑበት ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ
ሰኔ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ባለፈው ግንቦት ወር አጋማሽ ላይ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የነበረው አዋጅ ዛሬ ሲጸድቅ ከአዋጁ... read more
የአባይ ግድብ ምረቃ እና ዓለም አቀፍ ዘገባዎች
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ በመጪው የመስከረም ወር የአባይ ወንዝ ታላቁን ህዳሴ ግድብ (GERD) ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ስትሆን፣ ይህ ሜጋ... read more
ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት አባልነት ራሷን ዕጩ አድርጋ ማቅረቧ ተቀባይነቷን የሚያሳድግ ነው ተባለ
ታኅሳስ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ፤ ባሳለፍነው ሳምንት ተቀማጭነታቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮች... read more
የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ከ70 ግራም በታች የሆኑ የዳቦ ምርቶችን ሲያቀርቡና ሲሸጡ የተገኙ 53 ዳቦ ቤቶች ላይ እስከ ማሸግ የደረሰ እርምጃ መውሰዱን ገለጸ
ታኅሳስ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ኢንስፔክሽን እና ሬጉላቶሪ ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ አሰፋ ለጣቢያችን እንደገለጹት ባለፉት... read more
ለአንድ ሃገር ዘላቂ ሰላም መስፈን ከሚያስፈለጉ ነገሮች መካከል በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ያለው ግንኙነት የጠነከረ እና ሰላማዊ መሆን እንዳለበት ይገለጻል፡፡
ቢሆንም ግን በሃገራችን ያለው የፖለቲካ ውቅር እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ግንኙነት ደካማ ሆኖ የቆየ መሆኑ ይነሳል።
ቢሆንም ግን ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ... read more
ምላሽ ይስጡ