መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም የቱሪዝም ቀን ሲከበር ዘመኑ የደረሰበት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለቱሪዝሙ ዘርፍ የሚያመጣው ሚና የሚነገርበትም እንደሆነ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ትላንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ39ኛ ጊዜ “የዲጂታል አጀንዳ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለቱሪዝም አዲስ ቅኝት” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የተገለጸው የዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን ፡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የአገልግሎት ጥራትን ለማስጠበቅ ትኩረት የሚሰጥበትም ወቅት ነው ተብሏል። ቴክኖሎጂው በቱሪዝም ዘርፍ የጎብኚዎችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መረጃ ለመስጠት፣ የጉዞ ዕቅድና ቆይታ ለማቀላጠፍ፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በተቀናጀ መንገድ ለማስተዋወቅ እና የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ቱሪዝም ቀን በማስመልከት በትላንትናው እለት አዲስ የቱሪስት ዲጂታል የመረጃ ማዕከል ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱንም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል። በዓሉ ከመስከረም 14 እስከ 17 ቀን 2019 ዓ.ም በተለያዩ ፕሮግራሞች የሚከበር ሲሆን ከሚከበርባቸው ኹነቶች መካከልም ጎብኚዎችን ከአዲስ አበባ ወደ ቤኑና መንደር በባቡር ትራንስፖርት ማጓጓዝ፣የጎንደር ቤተ መንግስት እና የጅማ አባ ጅፋር ቤተ-መንግስት የእድሳት ስራዎች ተጠናቀው “ሕይወት በአብያተ መንግስት” በተሰኘ ፕሮጀክት ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረጉም ጠቁመዋል። የዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን በጎንደር ከተማ እንደሚከበርና ክብረ በአሉም የዓለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስ የሆነውን የመስቀል ደመራ በዓል በጋራ ማከበርን እንደሚያካትትም ጭምር ሚኒስትሯ ገልጸዋል። አሁን ላይ በዘርፉ የሚደረጉና የተደረጉ የዲጂታል ስርአት ለውጦችና ተሞክሮዎች ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ትግበራም መንገድ የሚከፍቱ በመሆናቸው ጅምሩ ከዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን መሪ ቃልም ጋር የተስማማ እንደሆነ አብራርተዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎትን መጠቀም በተለይ በጎብኚዎች ፍላጎት ላይ ተመስርቶ አገልግሎት ለመስጠት ይበልጥ አጋዥ ስለመሆኑም ተጠቁሟል ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የካናዳ ተማሪ የስልኩን ‘ቺፕ’ ወደ የመሬት መንቀጥቀጥ ሴንሰር ቀየረ
ሕዳር 04 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የካናዳ ተማሪ የሞባይል ስልክ ውስጥ የሚገኘውን ጥቃቅን የፍጥነት መለኪያ 'ቺፕ' በመጠቀም የመሬት መንቀጥቀጥን አስቀድሞ የሚጠቁም ሴንሰር... read more
የጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ የሙያ ማህበር ጋር በመተባበር 11ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን አካሄደ
የቶራሲክ ሶሳይቲ የሙያ ማህበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ራሄል አርጋው በሰጡት መግለጫ የጤና ሚኒስቴር የህብረተሰቡን ጤና ለማሻሻልና ልንከላከላቸው በምንችላቸው በሽታዎች የሚከሰቱ ህመምና... read more
አፍሪካዊው የፈጠራ ሰው ከ40 በላይ ቋንቋዎችን በቅጽበት የሚተረጉም የጆሮ ማዳመጫ ፈጠረ
👉የቋንቋ አለመቻል ችግርን ይቀርፋል ተብሏል
ሐምሌ 27 ቀን2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአንድ አፍሪካዊ የፈጠራ ባለሙያ የተሰራው አዲስ የጆሮ ማዳመጫ፣ ከ40 በላይ የሚሆኑ ቋንቋዎችን የበይነመረብ... read more
እንደ ሀገር ይህ ነው ተብሎ የተለየ ስያሜ የሚሰጠው የኢኮኖሚ ርዕዮት ዓለም እንደሌለ ተገለጸ
ኅዳር 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) አሁን ላይ እንደ ሀገር የምንከለተው የኢኮኖሚ ስርዓት አፈጻጸሙና መልኩ ካፒታሊስት ይምሰል እንጂ ቅይጥ ኢኮኖሚ፣ ካፒታሊስት... read more
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን በእጣ እና በጨረታ ለነዋሪዎች የተላለፉና ባለድለኞች እንዲገቡ ያልኩባቸዉን ሁሉንም የመኖሪያ ሳይቶች የመሰረተ ልማት አሟልቼ ጨርሻለሁ አለ
👉ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸዉ ቅሬታ አቅራቢዎች በበኩላችዉ ግቡ ተብሎ ቀነ ገደብ ቢቀመጥም ምንም የተሟላ መሰረተ ልማት የለም ሲሉ... read more
ህፃን አግተው ገንዘብ የጠየቁ ግለሰቦች በጽኑ እስራት ተቀጡ
ግንቦት 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የ6 ዓመት ህፃን በማገት እና ቤተሰቦቹን ለገንዘብ በመደራደር ወንጀል የተከሰሱ ሁለት ግለሰቦች በ12 እና በ9... read more
የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ሃይል ከሶማሊያ እንዲወጣ የመጠየቁ ጉዳይ እና አንደምታው…
የባህር በር እና የውሃ ጉዳይ ለሀገራት የምጣኔ ሃብት ጉልበት በመሆናቸው ሀገራት ሲራኮቱበት ይስተዋላል። ኢትዮጵያ የባህር በር ከሌላቸው ሀገራት መካከል ብትሆንም... read more
በእንጨት ብስክሌት የሰራው ኢትዮጵያዊ ወጣት እያነጋገረ ነው
👉1,255 ኪሎ ሜትር በዩኬ አቋርጦ እየተጓዘ ነው ተብሏል
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ከተማ የሚገኘው የኢምፔሪያል ኮሌጅ ተማሪ... read more
በበጀት ዓመቱ ከ1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የቡና ምርት ለመሰብሰብ እየተሰራ ነው ተባለ
ኅዳር 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በዚህ አመት እንደ ሀገር ከ1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሜትሪክ ቶን በላይ የቡና ምርት ለመሰብሰብ በትኩረት... read more
ሶስት ተቋማት በቱሪዝም ዘርፍ በትብብር ለመስራት ተፈራረሙ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት እና የቱሪዝም ሚኒስቴር በቱሪዝም ዘርፍ በትብብር መስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ዛሬ ተፈራርመዋል።
ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ... read more
ምላሽ ይስጡ