መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) የዓለም የቱሪዝም ቀን ሲከበር ዘመኑ የደረሰበት የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ለቱሪዝሙ ዘርፍ የሚያመጣው ሚና የሚነገርበትም እንደሆነ የቱሪዝም ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ትላንት በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል። በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ47ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ39ኛ ጊዜ “የዲጂታል አጀንዳ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎት ለቱሪዝም አዲስ ቅኝት” በሚል መሪ ቃል እንደሚከበር የተገለጸው የዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን ፡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና ዲጂታል ቴክኖሎጂዎች የአገልግሎት ጥራትን ለማስጠበቅ ትኩረት የሚሰጥበትም ወቅት ነው ተብሏል። ቴክኖሎጂው በቱሪዝም ዘርፍ የጎብኚዎችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ መረጃ ለመስጠት፣ የጉዞ ዕቅድና ቆይታ ለማቀላጠፍ፣ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በተቀናጀ መንገድ ለማስተዋወቅ እና የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ሚኒስትሯ ጠቅሰዋል፡፡ የዓለም አቀፍ ቱሪዝም ቀን በማስመልከት በትላንትናው እለት አዲስ የቱሪስት ዲጂታል የመረጃ ማዕከል ተመርቆ ወደ ስራ መግባቱንም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል። በዓሉ ከመስከረም 14 እስከ 17 ቀን 2019 ዓ.ም በተለያዩ ፕሮግራሞች የሚከበር ሲሆን ከሚከበርባቸው ኹነቶች መካከልም ጎብኚዎችን ከአዲስ አበባ ወደ ቤኑና መንደር በባቡር ትራንስፖርት ማጓጓዝ፣የጎንደር ቤተ መንግስት እና የጅማ አባ ጅፋር ቤተ-መንግስት የእድሳት ስራዎች ተጠናቀው “ሕይወት በአብያተ መንግስት” በተሰኘ ፕሮጀክት ለጎብኚዎች ክፍት እንደሚደረጉም ጠቁመዋል። የዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን በጎንደር ከተማ እንደሚከበርና ክብረ በአሉም የዓለም አቀፍ የማይዳሰስ ቅርስ የሆነውን የመስቀል ደመራ በዓል በጋራ ማከበርን እንደሚያካትትም ጭምር ሚኒስትሯ ገልጸዋል። አሁን ላይ በዘርፉ የሚደረጉና የተደረጉ የዲጂታል ስርአት ለውጦችና ተሞክሮዎች ለሰው ሰራሽ አስተውሎት ትግበራም መንገድ የሚከፍቱ በመሆናቸው ጅምሩ ከዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን መሪ ቃልም ጋር የተስማማ እንደሆነ አብራርተዋል። የሰው ሰራሽ አስተውሎትን መጠቀም በተለይ በጎብኚዎች ፍላጎት ላይ ተመስርቶ አገልግሎት ለመስጠት ይበልጥ አጋዥ ስለመሆኑም ተጠቁሟል ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የልማት ተነሺዎች የቤተ እምነት አገልግሎት ጥያቄ
https://youtu.be/mqX1sYFeSDI
read more
የጦር መሳሪያዎችን በአግባቡ ማስተዳደር የሚያስችል አሰራር እየተቀረጸ ነዉ ተባለ
ታኅሳስ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ህገ-ወጥ የጦር መሳሪያ ዝዉዉር በየጊዜዉ እየጨመሩ ካሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶች መካከል እንደሆነ ይገለጻል፡፡
የፌዴራል ፓሊስ ኮሚሽን የህዝብ... read more
ለሰዎች ጅራት ሰርተው እየገጠሙ ያሉት የጃፓን ሳይንቲስቶች
ነሐሴ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ጃፓን የሚገኙ ሳይንቲስቶች፣ የሰውን ልጅ ሚዛን ለመጠበቅ የሚረዳ፣ የእንስሳትን ጅራት የሚመስል 'ሮቦቲክ ጅራት' በመንደፍ ፈተና... read more
ስጋት የተጋረጠበት የመምህርነት ዘርፍ
https://youtu.be/_H2vPXjiO3M
read more
በአማራ ክልል የተመረተ ከ20 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ኦፓል ለውጭ ገበያ አቅርበናል👉የክልሉ የማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ
በአማራ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተመረተ ከ20 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ የኦፓል ማዕድን በማዕከላዊ ገበያ በኩል ለውጭ ገበያ መቅረቡን የክልሉ... read more
በመሬት የይዞታ ማረጋገጥ ስራ ላይ ለሚነሱ ችግሮች በወረቀት ያለው ሰነድ ህጋዊ ሆኖ እንደሚቀርብ ተገለጸ
ኅዳር 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ የመሬት ይዞታ ማረጋገጥና ምዝገባ ላይ በዲጅታልና በወረቀት ሆኖ በሚቀርብበት ወቅት የሚፈጠሩ ቅሬታዎችና ክፍተቶች ካሉ... read more
በኢትዮጵያ በአደባባይ ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ በመስከረም ወር ላይ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ተጠቃሽ ነው።
የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር እንደሚገናኝና በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር እንደቆየ የታሪክ ምሁራን ይናገራሉ። በዓሉ መስከረም ከገባና የመስቀል በዓል... read more
የኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ማኅበር ለሴቶች የተሻሉ የብድር አማራጮችን ይፋ አደረገ
ሰኔ 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዋጅ ቁጥር 985/09 መሠረት በ2017 ዓ.ም የተቋቋመው ኦሜጋ ብድርና ቁጠባ ኅብረት ሥራ ማኅበር፣ ለሴቶች... read more
ቻይና በሰከንድ 30 ቢንቢዎችን የሚገድል የሌዘር መሣሪያ ሠራች
ሐምሌ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ የቻይና ኩባንያ በሰከንድ እስከ 30 ትንኞችን ወይም ቢንቢዎችን መግደል የሚችል አዲስ የሌዘር መሣሪያ... read more
በመዲናዋ እየተባባሰ ለመጣው ፆታዊ ጥቃት ጥናት ሊደረግ መሆኑ ተገለጸ
ኅዳር 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአዲስ አበባ ከተማ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጠውን ፆታዊ ጥቃት ለማስቀረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር... read more
ምላሽ ይስጡ