መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም ወር ላይ የሚከበሩትን የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላትን ለመታደም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቱሪስቶች አንደሚመጡ የሚታወቅ በመሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችም በበቂ ሁኔታ መደረጋቸውን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ መስቀል እና ኢሬቻን ለማክበር ወደ መዲናዋ የሚመጡ የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች ተገቢውን መስተንግዶ እና መረጃ እንዲያገኙ የሆቴል ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ማህበሩ ከአባላቱ ጋር ቅድመ ውይይት ማከናወኑን የሆቴል ባለንብረቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን ገልጸዋል፡፡ ሆቴሎች አሁን ላይ ትልልቅ ኹነቶችን በስፋት እያስተናገዱ በመሆኑ ልምዳቸው እየጨመረ መሆኑን በመጥቀስ የሚመጡ ቱሪስቶች የቆይታ ጊዜያቸውንም እንዲያራዝሙ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠታቸው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ እንዲሁም ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ የሚጎበኝ ስፍራ የሌላት በመሆኑ መተላላፊያ በመሆኗ የሆቴሎች ተጠቃሚነት ዝቅተኛ እንደነበረ በመጥቀስ አሁን ላይ አዲስ አበባን ብቻ ለመጎብኘትም በርካታ ጎብኝዎች እንደሚመጡ እና የሆቴሎች ተጠቃሚነትም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላትን አስመልከቶ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር አብረው እየሰሩ መሆኑን በማንሳት የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላትን አስመልክቶ በጋራ የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸዉን አስረድተዋል፡፡ በሆቴሎች በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማስቻል እና አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ ማህበሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል፡፡ ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
የአሜሪካው አፓቺ የውጊያ ሄሊኮፕተር በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ አቅራቢያ ተከሰከሰች
ሰኔ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሆርሙዝ ባህረ ሰላጤ አቅራቢያ ከፍተኛ ወታደራዊ ስምሪት ላይ የነበረች የአሜሪካ ጦር ኃይል ኤኤች-64 አፓቺ (AH-64 Apache)... read more
በአፍና በከንፈር አካባቢ የሚያጋጥም ቁስል ከየት የመጣ ነው?
👉የህክምና ድህረ ገጾች ስለበሽታው ምን ይላሉ?
ሐምሌ 16 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአፍና በከንፈር አካባቢ የሚያጋጥመው ቁስለት ኸርፒስ (Herpes) በሄርፒስ ሲምፕሌክስ ቫይረስ... read more
በሃይማኖት ስም በማህበራዊ ሚዲያ ምን እየተሰራ ነው?
https://youtu.be/T9Bwg-uIffs
read more
የአዋዛ ስምምነት እንዲተገበር በተለያዩ አማራጮች ጫናዎችን ማድረግ እንደሚገባ ተገለጸ
ነሐሴ 13 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቅርቡ በቱርክሚስታን ከተማ አዋዛ የተደረገው ባህር የሌላቸው ታዳጊ ሀገራት ጉባኤ የፀደቀው የአዋዛ ስምምነት በጂኦግራፊ አቀማመጥ... read more
የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ያሳድጋል የተባለው የኢትዮጵያ – አውሮፓ ህብረት የንግድ ፎረም 2026 ተጀመረ
ሚያዚያ 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ያሳድጋል የተባለውና ከዛሬ ሚያዝያ 12 እስከ ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚቆየው የኢትዮጵያ... read more
ከስደት ለተመለሱ ዜጎች የስነልቦና ድጋፍ ለመስጠት ስምምነት ተፈረመ
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ) የተሻለ ኑሮና ገቢን ለማግኘት በማሰብ ወደ ተለያዩ የውጭ ሀገራት የሚያቀኑ የዜጎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑ... read more
የውጭ ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ መቀዛቀዝ በሴቶችና በእናቶች ላይ የሚሰሩ ስራዎቸን ፈትኗል ተባለ
ሐምሌ 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በተያዘው በጀት አመት በአለም አቀፍ ደረጃ ድጋፍ ሲያደርጉ የነበሩ የተለያዩ ግብረሰናይ ድርጅቶች ድጋፍ መቀዛቀዝ በሴቶችና... read more
በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች ዝግጁ ሊሆኑ ይገባል ተባለ
መስከረም 11 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ)በበጋ ወራት ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸውን በሚያገኙ የደቡብ እና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ያሉ አርሶ አደሮች... read more
የነዳጅ እጥረት እና የመለዋወጫ ዕቃ ችግር በተፈለገው መጠን አውቶብሶችን ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለማስገባት ተግዳሮት መፍጠሩ ተገለጸ
የተበላሹ አውቶብሶችን ጠግኖ ወደ አገልግሎት ለማስገባት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም በተፈለገው መጠን መስራት እንዳልተቻለ የአዲስ አበባ ከተማ አውቶብስ አገልግሎት ድርጅት ለመናኸሪያ... read more
ውሾች የፓርኪንሰን በሽታን ምልክቱ ከመታየቱ በፊት በከፍተኛ ትክክለኛነት ማሽተት እና መለየት ይችላሉ ተባለ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቅርብ ጊዜ ጥናት እንደሚያመለክተው ውሾች የፓርኪንሰን በሽታን ምልክቶች ከመታየታቸው በፊት ለዓመታት በማሽተት መለየት የሚችሉ ሲሆን፣... read more
ምላሽ ይስጡ