መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) መስከረም ወር ላይ የሚከበሩትን የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላትን ለመታደም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ቱሪስቶች አንደሚመጡ የሚታወቅ በመሆኑ ቅድመ ዝግጅቶችም በበቂ ሁኔታ መደረጋቸውን ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡ መስቀል እና ኢሬቻን ለማክበር ወደ መዲናዋ የሚመጡ የውጭ ሀገራት ቱሪስቶች ተገቢውን መስተንግዶ እና መረጃ እንዲያገኙ የሆቴል ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ማህበሩ ከአባላቱ ጋር ቅድመ ውይይት ማከናወኑን የሆቴል ባለንብረቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አስቴር ሰለሞን ገልጸዋል፡፡ ሆቴሎች አሁን ላይ ትልልቅ ኹነቶችን በስፋት እያስተናገዱ በመሆኑ ልምዳቸው እየጨመረ መሆኑን በመጥቀስ የሚመጡ ቱሪስቶች የቆይታ ጊዜያቸውንም እንዲያራዝሙ ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠታቸው አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡ እንዲሁም ከዚህ ቀደም አዲስ አበባ የሚጎበኝ ስፍራ የሌላት በመሆኑ መተላላፊያ በመሆኗ የሆቴሎች ተጠቃሚነት ዝቅተኛ እንደነበረ በመጥቀስ አሁን ላይ አዲስ አበባን ብቻ ለመጎብኘትም በርካታ ጎብኝዎች እንደሚመጡ እና የሆቴሎች ተጠቃሚነትም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላትን አስመልከቶ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር አብረው እየሰሩ መሆኑን በማንሳት የመስቀል እና ኢሬቻ በዓላትን አስመልክቶ በጋራ የተጀመሩ ስራዎች መኖራቸዉን አስረድተዋል፡፡ በሆቴሎች በኩል የሚሰጡ አገልግሎቶች ጥራታቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ ለማስቻል እና አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ ማህበሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ የማህበሩ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል፡፡ ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
አዲሱ የካሳ አከፋፈል አዋጅ ማስፈጸሚያ መመሪያና ደንብ ስላልወጣለት በፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ ተግዳሮት መፍጠሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለጸ።
ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የካሳ ክፍያ በክልሎች እንዲፈጸም የሚደነግገው አዲሱ አዋጅ እስካሁን ማስፈጸሚያ መመሪያና ደንብ እንዳልወጣለት ለመናኸሪያ ሬዲዮ የተናገሩት... read more
ብቁ ያልሆኑ ዜጎች ለውጭ ሀገር የስራ ስምሪት እየተላኩ በመሆኑ ለስቃይ እየተዳረጉ ነው ተባለ
በውጭ ሀገር የስራ ስምሪት ብቁ ያልሆኑ ዜጎች እየተላኩ በመሆኑ ለስቃይ መዳረጋቸውን የፌደራል የስነ-ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ጥናት ገለጸ።
ይህንን በተመለከተ የወጣው... read more
በመዲናዋ ሲካሄድ የነበረው የማህበረሰብ የጤና መድህን ምዝገባ ከተያዘው እቅድ ከ85 በመቶ በላይ መሳካቱ ተገለጸ
ታኅሳስ 01 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጤና መድህን ምዝገባ በመዲናዋ ከጥቅምት 1 ቀን 2017 ጀምሮ ለ2 ወራት ሲከናወን መቆየቱ ይታወሳል፡፡
በህዝብ ተወካዮች... read more
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን ለአየር ክፍሉ ወሳኝ ሚና መወጣት የሚችሉ 114 የኤርናቪጌሽን ባለሙያዎችን በዛሬው ዕለት አስመረቀ
ነሐሴ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ዘርፉ አሁንም በቂ የሰው ሀይል ስለሌለው ክፍተቶቹን ለመሙላት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል አቬየሽን... read more
አሜሪካ ከዩኔስኮ ለመውጣት በዝግጅት ላይ ነች ተባለ
ሐምሌ 15 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)አሜሪካ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አባልነቷን ለማቋረጥ እየተዘጋጀች መሆኑ ታውቋል።
ይህ ውሳኔ የፕሬዚዳንት ዶናልድ... read more
ከአንጋፋዋ የኪነጥበብ ሰው #አለምጽሃይ ወዳጆ ጋር የተደረገ ቆይታ
https://youtu.be/NybH5JhdaNs
read more
ስልኩ አልተሰበረም! ከ16,000 ጫማ ከፍታ የወደቀው አይፎን! ✈️
ሕዳር 15 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)አስደናቂው የአላስካ ኤርላይንስ በረራ 1282 ክስተት! ከአደጋው በኋላ መርማሪዎችን ያስገረመ ክስተት ተመዝግቧል።
አውሮፕላኑ ወደ 16,000 ጫማ (5... read more
የንስር ዓይን አስገራሚ ሚስጥር
👉ከ10ኛ ፎቅ ላይ ሆኖ መሬት ላይ ያለውን ጉንዳን መመልከት ይቻላል ተብሏል
ነሐሴ 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ንስር በአለም ላይ ካሉት ፍጥረታት... read more
“ምስማር የመዋጥ ያህል የሚያም የጉሮሮ ህመም!” – አዳዲስ የኮቪድ ዝርያዎች በአሜሪካ በፍጥነት እየተስፋፉ ነው ተባለ
መስከረም 22 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)በአሜሪካ ውስጥ XFV ("ስትራተስ") እና NB.1.8.1 ("ኒምበስ") የሚባሉ ሁለት አዳዲስ የኮቪድ-19 ዝርያዎች በፍጥነት እየተሰራጩ ነው ተባለ።... read more
አሌክሳንደር ኢሳክ ከ4 ወራት ቆይታ በኋላ ወደ ሜዳ መመለሱን ክለቡ አስታውቋል
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ሊቨርፑል በ125 ሚሊዮን ፓውንድ የእንግሊዝ የዝውውር ክብረ ወሰንን በመስበር ያስፈረመው፣ ትውልደ ኤርትራዊው ስዊድናዊ አጥቂ አሌክሳንደር... read more
ምላሽ ይስጡ