መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) «የምድር ጌጥ ኢትዮጵያ» በሚል ርዕስ ሲካሄድ የቆየው ታሪካዊና ባህላዊ አውደ ርዕይ የመጎበኛ ጊዜ፣ ከህዝብ የቀረበውን ከፍተኛ ፍላጎትና ጥያቄ መነሻ በማድረግ ለተጨማሪ ሶስት ሳምንታት መራዘሙ የዝግጅቱ አዘጋጅ «የሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት» አስታዉቋል፡፡ አውደ ርዕዩ ከዚህ ቀደም ከነሐሴ 28 እስከ መስከረም 10 ቀን ሲካሄድ የነበረ ቢሆንም፣ በወቅቱ የነበሩ የሃይማኖታዊና የባህላዊ በዓላት መደራረብ እንዲሁም ከቦታ ምቾት ጋር ተያይዘው የነበሩ ችግሮች የጎብኚዎችን ቁጥር እንደገደበዉ ድርጅቱ ገልጻል፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ተዘጋጅቶ የቀረበው ይህ አውደ ርዕይ፤ ህፃናትና ቤተሰቦች የሀገራቸውን፣ የሃይማኖታቸውን፤ የቅዱሳት ቤተክርስቲያናትን ታሪክና ቅርሶች በቅርበት የሚያውቁበትን እድል የፈጠረ ነው ተብሏል። ዝግጅቱም በማየት፣ በመዳሰስ፣ በመስማት፣ በማሸተትና በመቅመስ አምስቱንም የስሜት ሕዋሳት በሚያሳትፍ ልዩ አቀራረብ የተዘጋጀ ሲሆን፤ የላሊበላ፣ የአክሱም፣ የደብረ ዳሞና የሌሎችም ታሪካዊ ቦታዎች ምስልና ቅርሶች ቀርበውበታል። በተጨማሪም በቦታው ላይ በርካታ ታሪካዊና ባህላዊ ይዘቶች በመኖራቸው፤ አውደ ርዕዩን ወደፊት «ቋሚ ሙዚየም» ለማድረግ የሚያስችል ሥራ በጥረት ላይ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። በዚሁ መሠረት አውደ ርዕዩ ከመስከረም 30 ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር አጋማሽ ድረስ ባሉት ተከታታይ ሶስት ሳምንታት፤ በየሳምንቱ ቅዳሜና እሁድ ለጎብኚዎች ክፍት ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል። አስተባባሪዎቹ አክለውም፤ እስካሁን አውደ ርዕዩን ያላዩ ህፃናትና ቤተሰቦች ከጦር ኃይሎች ወደ ቀራኒዮ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው «ሆላንድ ፓርክ» በመገኘት ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንዲጠቀሙ ጥሪ አቅርበዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
እንግሊዝ እና አሜሪካ የኑክሌር ኃይል ፕሮጀክቶችን ለማፋጠን የሚያስችል ስምምነት ሊፈራረሙ ነው
መስከረም 05 ቀን (መናኸሪያ ሬዲዮ) ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩናይትድ ስቴትስ በአትላንቲክ ውቅያኖስ በሁለቱም በኩል የኑክሌር ኃይል ማመንጫዎችን ግንባታ የሚያፋጥን ታሪካዊ... read more
ኢምባሲዎች የየሀገራቸውን ባህል በማስተዋወቅ የፌስቲቫሉ አካል እንዲሆኑ እየሰሩ እንደሚገኙ የጳጉሜን ፌስቲቫል አዘጋጆች ገለጹ
ነሐሴ 30 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) ኢምባሲዎች የየሀገራቸውን ባህል በማስተዋወቅ የፌስቲቫሉ አካል እንዲሆኑ እየሰሩ እንደሚገኙ የጳጉሜን ፌስቲቫል አዘጋጆች ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታወቁ።... read more
በከተማዋ ላይ የታይሮይድ መድሃኒት ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመሆኑ አሳስቦናል ሲሉ ተጠቃሚዎች ገለጹ
ታኅሳስ 11 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) ለመናኸሪያ ሬዲዮ ቅሬታቸውን ያቀረቡት የእንቅርት መድሃኒት (ታይሮክሲን) ተጠቃሚ መድሃኒቱን የመንግስት መድሃኒት መሸጫ በሆነው ከነማ መደብር... read more
ኢትዮጵያን ጨምሮ በአፍሪካ አገራት እንደ ማዕድን ያሉ የተፈጥሮ ሀብቶች ስለምን የግጭት የስዕበት ማእከል ሆኑ? በአስተዳደር እና የህግ ማዕቀፍ ችግር ወይስ የተፈጥሮ ሀብቱ በባህሪው ግጭትን ሳቢ ስለሆነ?
አፍሪካ እምቅ የተፈጥሮ ሀብት ቢኖራትም ሀብቱን ለልማት አውሎ የዜጎችን ሕይወት መቀየር፤ አህጉሪቱንም ከድህነት ማውጣት ግን አለመቻሉን የአህጉሪቱን ጉዳይን በቅርበት የሚከታተሉ... read more
ከቀውስ ቀጠናዎች እስከ ህልውና ፈተና፦ በኢትዮጵያ የስደተኞች የጤና፣ የመብት ከለላ እና የሰብዓዊ እርዳታ እጥረት አሳሳቢነት
በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በሚቀጥሉት ውጥረቶች፣ የሰላም እጦት እና የተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት በኢትዮጵያ መጠለያ ያገኙ ስደተኞች በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገራቸው... read more
እስራኤል የጠላትን ድሮኖች በአየር ላይ የመጥለፍ እና ወደ ራሷ ኃይሎች የመምራት ቴክኖሎጂን አዳብራለች ተባለ
ሐምሌ 24 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የጦርነት ስልት እና ቴክኖሎጂ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። እስራኤል የጠላት ድሮኖችን በአየር ላይ እያሉ በመጥለፍ... read more
ግራፊን (Graphene)፤ የኃይል ማከማቻ ቴክኖሎጂን የሚቀይረውና የባትሪዎችን ዘመን የሚያድሰው አስደናቂ ቁስ
ግንቦት 26 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በቁሶች ሳይንስ እና በኤሌክትሮኒክስ ምህንድስና ዘርፍ ታላቅ አብዮት ይፈጥራል የተባለለት በ"ግራፊን" ላይ የተመሰረተ የኃይል ማከማቻ... read more
በዝናብ ወቅት የሚከሰት የዶሮ በሽታን ለመከላከል መንግስት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ
ነሐሴ 12 ቀን 2017 (መናኸሪያ ሬዲዮ)የዝናብ ወቅት ለዶሮ በሽታ አምጪ ተህዋስያን መራባትና መስፋፋት አመቺ በመሆኑ፣ መንግስት የባለሙያ ድጋፍና የግንዛቤ ማስጨበጫ... read more
ደቡብ ሱዳን በዓባይ ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት መወሰኗ በግብፅ በኩል የነበረውን የውኃ አጠቃቀም የበላይነትና ጫና በጋራ ለመጋራት የሚረዳ ነው ተባለ
መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነቡ የኃይል ማመንጫ ግድቦች በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ተጽዕኖ ቢኖራቸውም፣... read more
በጥርስ እና ጸጉር ንቅለ ተከላ ዙሪያ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከልክ በላይ የተጋነኑ በመሆኑ ቁጥጥር እና እርምጃ እየተወሰደባቸው ነው ተባለ
ታኅሳስ 04 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የንግድ ውድድሩን ተከትሎ የጤና ተቋማት አማላይ ማስታወቂያዎችን በማስነገር ህብረተሰቡን ወደ ተሳሳተ እይታ እየመሩት ነው ያለው... read more
ምላሽ ይስጡ