ነሐሴ 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በደርግ ዘመነ መንግሥት ጋዜጠኛና የካሜራ ባለሙያ የነበሩት እና በአሁኑ ወቅት ኑሯቸውን በእንግሊዝ ሀገር ያደረጉት አቶ አለባቸው ደሳለኝ፣ በአንድ ወቅት ከቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ጋር ለሦስት ሰዓታት ቆይታ ማድረጋቸውን ከመናኸሪያ ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ልዩ ቃለ መጠይቅ ተናግረዋል፡፡ አቶ አለባቸው እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግሥት የአክሱም ሐውልት ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ በተደጋጋሚ ይጠይቅ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ ፕሬዝዳንቱ ይህ ጥያቄ ለአፄ ኃይለ ሥላሴ ቀርቦ እንደነበር በማስታወስ፣ የማጓጓዣ እና ሌሎችም ጉዳዮች ባለመሟላታቸው ሳይሳካ መቅረቱን አመላክተዋል፡፡ በእርሳቸው ዘመን ይህን ግዙፍ ሐውልት ወደ ሀገር ቤት ለማስገባት መርከብና አስፈላጊ ዝግጅቶች ላይ ውይይቶች ቢደረጉም አለመሳካቱን ከፕሬዝዳንቱ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደነገሯቸው ጠቁመዋል፡፡ በውጭ ሀገራት ያሉ የኢትዮጵያ ቅርሶች ወደ ሀገር እንዲመለሱ ፕሬዝዳንቱ ከፍተኛ ፍላጎት እንደነበራቸው የሚናገሩት አቶ አለባቸው፣ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ እንደነበርም መገንዘባቸውን ገልጸዋል፡፡ የአክሱም ሐውልት ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ ከሪቻርድ ፓንክረስትና ከሌሎችም ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ሥራውን መስራታቸውን ጠቁመዋል፡፡
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
ምላሽ ይስጡ