መስከረም 13 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) ሴቶች በግጭት ወቅት ጉዳት እንዳይደርስባቸው የመጠበቅና በሰላምና ደህንነት ዙሪያ ያላቸውን ሚና የማጉላት ሥራ ሊሠራ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሴቶች ማኅበራት ቅንጅት (NEWA) “ብሔራዊ የሴቶች፣ ሰላምና ደህንነት ፎረም” በሚል ባዘጋጀው መድረክ ላይ ገልጿል። የቅንጅቱ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሳባ ገብረመድህን የሴቶች ሰላምና ደህንነት አጀንዳ በሴቶች የሰላም ድርድር ተሳትፎ ብቻ ሳይወሰን ከግጭት በመከላከል፣ በጥበቃ እና በአካቶ መተግበር አለበት ብለዋል። በተለይ ግጭት በሚከሰትባቸው አካባቢዎች ሴቶች ከፍተኛ ጉዳት እንደሚደርስባቸው ተናግረው፤ ከግጭቱ በኋላ ለማገገም የሚያስችሏቸው መሠረተ ልማቶችና አገልግሎቶች መጠናከር እንዳለባቸውም አብራርተዋል። በውሳኔ ሰጪ ሂደቶች የሴቶች ዝቅተኛ ተሳትፎ በግጭት ወቅት የበለጠ ሊጎለብቱ የሚችል መሆኑን ጠቅሰው፤ በማኅበረሰብ ደረጃ ሴቶች እያደረጉት ያለው የሰላም እንቅስቃሴ፣ የሴቶች ድርጅቶች የሚያከናውኑት የጥበቃና የድጋፍ ሥራ እንዲሁም ለግጭት ተጎጂዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ታውቀውና ተመዝግበው ድጋፍ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል። በተለይም በዚህ ላይ የሚሠሩ የሴቶች ማኅበራት ጥረቶችንም መደገፍ፣ እነዚህን ጥረቶች ማስተባበር እና ግጭትን ከመከላከል ጀምሮ በሰላም ማስፈን ሂደት ሴቶች የሚኖራቸውን ሚና ማሳደግ እንደሚገባ አመላክተዋል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በደቡብ ኮሪያ ጉብኝታቸው ከኪም ጆንግ ኡን ጋር ለመገናኘት ‘እጅግ በጣም ፍላጎት’ እንዳላቸው ገለጹ
ጥቅምት 17 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአሁኑ ወቅት እያካሄዱ ባሉት የእስያ ጉብኝት ወቅት የሰሜን ኮሪያውን መሪ ኪም... read more
የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከላት በአሜሪካውያን ላይ የጤና ቀውስ እየፈጠሩ መሆኑ ተሰማ
ግንቦት 12 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፉ የመጡት የሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) መረጃ ማዕከላት በአቅራቢያቸው በሚኖሩ ነዋሪዎች... read more
መንግስት ጋብቻን የሚያበረታቱና ለቤተሰብ መጽናት አጋዥ የሚሆን ፖሊሲ ሊቀርጽ ይገባል ተባለ
ከጊዜ ወደ ጊዜ ከጋብቻዉ ቁጥር በዘለለ የሚሰማ የፍቺ ቁጥር እየተበራከተ በመምጣቱ መንግስት ለጋብቻ እና ቤተሰብ መጽናት የሚሆኑ ፓሊሲና የተለያዩ ህጎችን... read more
በከተማዋ የምርት አቅርቦት ዕጥረት እንዳይፈጠር ከክልሎችና ሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ
ነሐሴ 20 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኅብረት ሥራ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀምና የ2018 በጀት ዓመት... read more
በበይነ መረብ ይጀመራል ተብሎ የነበረው የምልክት ቋንቋ ትምህርት በግብዓት እና በባለሙያ እጥረት ምክንያት መጀመር አለመቻሉ ተገለጸ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራሰ ገዝ የመንግስት ተቋም ከሆነ በኋላ በመማር ማስተማር ሂደት ውስጥ ተደራሽነቱን ለማስፋት በርካታ ስራዎችን እየሰራ ቢገኝም በበይነ... read more
የስርቆት ወንጀል በፈጸሙ አካላት ላይ የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የቅጣት ውሳኔ አስተላለፈ
ፍ/ቤቱ በአርባምንጭ ከተማ ባለ 2 እና ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን በመስረቅ፣ ተባበሪ በመሆን፣ በመግዛት፣ ወደ ተለያዩ አካባቢዎች ወስደው በመሸጥ፣ በማሻሸጥ... read more
በቀጣይ ሁለት ሳምንታት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ ስራ እንደሚጀመር ተገለጸ
ኅዳር 18 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጪው ሁለት ሳምንት ውስጥ በኦሮሚያ ክልል የአጀንዳ ማሰባሰብ የምክክር መድረክ በይፋ... read more
በጀርመናዊ ወጣት የተደረገው “የቴስላ ጠለፋ” የአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪውን አስደንግጧል
መስከረም 19 ቀን 2018 (መናኸሪያ ሬዲዮ)አንድ የ19 ዓመት ጀርመናዊ ወጣት የሆነው ዴቪድ ኮሎምቦ ከአገሩ ጀርመን ሆኖ ከ13 በሚበልጡ አገራት የሚገኙ... read more
የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በ2017 ዓ.ም ከቅጣት 404 ሚሊዮን ብር ገቢ ማሰባሰቡን አስታወቀ
ነሐሴ 23 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ከድርጅቶች፣ ከግለሰቦች እና ከመንግስት ተቋማት የተጣለባቸውን የቅጣት... read more
ከዛሬ ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኙ በሁሉም ባንኮች አዲስ የባንክ ሒሳብ ለመክፈት የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ (የፋይዳ ቁጥር) ይዞ መቅረብ ግዴታ መሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገልጿል፡፡
ሀሳብ እና'ሳ'ፍራለን
መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1
ሃሳብ፣አስተያየት እና ጥቆማ ለመስጠት የሚከተሉትን የስቱዲዮ ስልኮቻችን ይጠቀሙ
👉011-639-28-52👉011-639-37-63
የቀጥታ ስርጭት 👉 📻 (https://worldradiomap.com/et/play/menaharia) radio 99.1 (https://stream.zeno.fm/yw8poig9iwtuv)
✅ https://t.me/menaharia_fm
✅https://x.com/MenahriaFm99_1
ትክክለኛውን የመናኸሪያ... read more
ምላሽ ይስጡ