መስከረም 12 ቀን 2019 ዓ.ም (መናኸሪያ ሬዲዮ) በዓባይ ወንዝ ላይ የሚገነቡ የኃይል ማመንጫ ግድቦች በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ ተጽዕኖ ቢኖራቸውም፣ በትብብር ከተመሩ ለቀጠናው ትልቅ ጥቅም እንደሚሰጡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ኢንጅነር ጌዲዮን አስፋው ገልጸዋል። ውሳኔው የኢትዮጵያን ሀገራዊ የኃይል አቅርቦት ለማስፋፋት፣ የኤሌክትሪክ ተዳራሽነትን ለማረጋገጥ እና ትርፍ ኃይልን ለጎረቤት ሀገራት በመሸጥ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ይናገራሉ። ደቡብ ሱዳን በላይኛው ናይል ተፋሰስ ላይ ግድብ ለመገንባት የምታደርገው እንቅስቃሴ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነትን (CFA) መሠረት ያደረገ መሆኑን የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተደራዳሪ አቶ ፈቅአሕመድ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡ ውሳኔው እስካሁን በግብፅ በኩል የነበረውን የውኃ አጠቃቀም የበላይነትና ጫና በጋራ ለመጋራት እንዲሁም ፍትሐዊ አጠቃቀምን ለማስፈን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ጠቁመዋል። ለኢትዮጵያ በዲፕሎማሲና በልማት ዘርፍ ድጋፍ የሚሰጥ ከመሆኑም በላይ፣ ሌሎች የተፋሰሱ ሀገራትም ወደ ተመሳሳይ የልማት እንቅስቃሴዎች እንዲገቡ መንገድ የሚከፍት በመሆኑ ለቀጠናው ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል። በሌላ በኩል ደቡብ ሱዳን በናይል ወንዝ ላይ ግድብ ለመገንባት የወሰደችው ውሳኔ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስጠብቅና የተፈጥሮ ሀብቷን የመጠቀም ሉዓላዊ መብቷን የሚያረጋግጥ መሆኑን የዲፕሎማሲ ባለሙያው አምባሳደር ጥሩነህ ዜና ገልጸዋል። ውሳኔው ከኢትዮጵያም ሆነ ከሌሎች የዓባይ ተፋሰስ ሀገራት የጋራ ስምምነት ጋር የሚጣጣም መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ፤ ግድቡ መገንባቱ ሀገራት የተፈጥሮ ሀብታቸውን በሉዓላዊነት የመጠቀም መብታቸውን የሚያጠናክር እና የጋራ ተጠቃሚነት መርሕን የሚያጎለብት ነው ብለዋል። የግድቡ መገንባት የደቡብ ሱዳንን ብሔራዊ ጥቅም ከማስጠበቅ ባለፈ፣ ሌሎች የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትንም በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል። ___ ሀሳብ እና‘ሳ‘ፍራለን
Related Posts
በሰሜን ዋዚሪስታን በተፈጸመ የቦምብ ጥቃት 13 የጸጥታ ኃይሎች ሲሞቱ 14 ንፁሃን ቆስለዋል
ሰኔ 21 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ) በፓኪስታን ሰሜናዊ ምዕራብ በሚገኘው ሰሜን ዋዚሪስታን ክልል ውስጥ በተፈጸመ ከባድ የአጥፍቶ ጠፊ የቦምብ ጥቃት 13... read more
ሱዳን የዓባይ ወንዝ የውሃ መጠን እየጨመረ እንደሚሄድ እና የጎርፍ አደጋ ሊያጋጥማት እንደሚችል አስታወቀች
መስከረም 21 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የአባይ ወንዝ ከፍታው ሲጨምር የአገሪቱ መንግስት ለህዝቡ የማስጠንቀቂያ መልዕክት ያስተላልፋል።
በመሆኑም አገሪቱ ትላንት ማክሰኞ በአባይ ወንዝ... read more
ባለፉት 6 ወራት በአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ 15.5 ቢሊየን ብር መሰብሰቡ ተገለጸ
መስከረም 09 ቀን 2019ዓ.ም.(መናኸሪያ ሬዲዮ) በኢትዮጵያ 2.9 ሚሊየን ድጋፍ የሚሹ ተረጂዎች እንዳሉ የኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮምሽን መረጃ አመላክቷል።... read more
የቡና ከረጢቶችን የፈጠራ አቅም ከባንግላዲሽ መማር እንደሚያስፈልግ ተነገረ
ሕዳር 05 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የቡና ከረጢቶችን የፈጠራ አቅም ከባንግላዲሽ መማር እንደሚያስፈልግ በንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ይድነቃቸው ወርቁ... read more
የ7 ዓመት ህፃን የደፈረው ግለሰብ ከማንኛውም ህዝባዊ መብቶች እንዲታገድ ተወሰነበት
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የሰባት ዓመት ህፃን ልጅ አስገድዶ የደፈረው በእስራት መቀጣቱን የቃሉ ወረዳ ፖሊስ አስታውቋል።
ተከሳሹ በእስራት... read more
በአዲስ አበባ ከተማ ለመስቀል ደመራ በዓል የሚዘጉ መንገዶችን ይፋ ተደረጉ
መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ለመስቀል ደመራ በዓል ከዋዜማው ጀምሮ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ... read more
በትውልድ ግንባታ ሂደት ወጣቶች የአርበኞችን ታሪክ እንዲረዱ ማድረግ ይገባል ተባለ
በቀደምት ጊዜ ሃገር በጠላት እጅ እንዳትወድቅ ለመከላከል በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ አርበኞች ከፍተኛ መስዋት የከፈሉበትን ቀን ለመዘከር የአርበኞች ቀን በዛሬው ዕለት... read more
የሰሜን ኮሪያው መሪ እህት ከአሜሪካ ጋር በኑክሌር ትጥቅ ማስፈታት ዙሪያ የሚደረግ ንግግር እንደማይኖር ገለጹ
ሐምሌ 22 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ኃያል እህት ኪም ዮ ጆንግ፣ ከአሜሪካ ጋር በኑክሌር ትጥቅ ማስፈታት... read more
በሀገር አቀፍ ደረጃ የመጀመሪያው የሆነው ብሄራዊ የተማሪዎች ሽልማት ሊካሄድ ነው
ታኅሳስ 02 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በሀገራችን የመጀመሪያው እና ብቸኛ የሆነው ሀገር አቀፍ የተማሪዎች ሽልማት ሊካሄድ መሆኑ ተገልጿል።
ይህን ሽልማት የሚያካሂደው የኢትዮጵያ ብሄራዊ... read more
28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ተጭበርበሩ
28 የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡
የባንኩ ሪፖርት... read more
ምላሽ ይስጡ