ሰኔ 02 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)ተግባራዊ በሆነው አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ውስጥ የሀገር በቀል እውቀት ከጽሑፍ ያለፈ ለትግበራ የተዘጋጀ አካሄድ የለም ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ ጤና መምህር እና በሀገር በቀል እውቀት ዙሪያ ምርምር የሚያደርጉት ፕሮፌሰር መንገሻ አድማሱ ለጣቢያችን ተናግረዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር የተጠና ጥናት ቢኖረውም ወደ ትግበራ አልገባም የሚሉት ባለሙያው፣ ሰነድ ማዘጋጀትና መተግበር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ሌሎች ተቋማትም ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ሀገር በቀል እውቀቶችን አካቶ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲተገበር ለማስቻል የማስፈጸሚያ ሰነድ እየተዘጋጀ መሆኑን በትምህርት ሚኒስቴር የሀገር በቀል እውቀትና የማህበረሰብ ትስስር ዴስክ ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላም አለሙ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
ፍኖተ ካርታው መተግበር ከጀመረ ዓመታትን ያስቆጠረ እንደሆነ የተናገሩት ዳይሬክተሯ፣ ነገር ግን የሀገር በቀል እውቀትን አካቶ ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ለማስቻል የሚቀሩ ስራዎች መኖራቸውን አምነዋል።
ዳይሬክተሯ በሚመሩት የሀገር በቀል እውቀትና የማህበረሰብ ትስስር ዴስክ በኩል የማስፈጸሚያ መመሪያ ሰነድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። ይህ ብቻም ሳይሆን አሁን ላይ በካሪኩለም ወይም በስርዓተ ትምህርት ክፍሉም በኩል እንዲሁ የማስፈጸሚያ መመሪያዎች መቀረጻቸውን ገልጸዋል። ስርዓተ ትምህርቱ ሙሉ በሙሉ የሀገር በቀል እውቀትን እንዲያካትት ለማስቻል ነው በቂ ቅድመ ዝግጅት ያስፈለገው ሲሉም አክለው ተናግረዋል።
አዲስ የትምህርት ፍኖተ ካርታ መቅረጽ ያስፈለገው ሀገር በቀል እውቀቶችን ለማካተት እንደሆነ ካሁን ቀደም የትምህርት ሚኒስትሩ መናገራቸው ይታወሳል።
__
ሀሳብ እና’ሳ’ፍራለን
Related Posts
ኢትዮጵያ በ100 ቢሊዮን ብር ካፒታል የመጀመሪያውን የቤት መግዣ ብድር ማጠናከሪያ ኩባንያ ልታቋቁም ነው
ነሐሴ 28 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እና የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (IFC) በሀገሪቱ የመጀመሪያው የሆነውን የቤት መግዣ ብድር... read more
የሊቨርፑል ደጋፊ ነው ተብሎ የተጠረጠረው ዳኛ 2 ክለቦችን በፕሪሚየር ሊጉ እንዳይዳኝ መታገዱ ተሰምቷል
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአርሰናል ደጋፊዎች የፊታችን ቅዳሜ በሜዳቸው ኤምሬትስ ሊድስ ዩናይትድ በሚያስተናግዱበት የፕሪሚየር ሊጉ 2ኛ ሳምንት ጨዋታን የሚዳኘው ይኸው የሊቨርፑል... read more
ለሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቂ ድጋፍና እገዛ እንደሚያስፈለገው ተገለጸ
ጥር 14 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)በኢትዮጵያ እየተፈጠሩ ያሉ አለመግባበቶችን ለመቅረፍ የኢትዮጵያ ሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰፊ ስራን እየሰራ ቢሆንም ተጨማሪ አጋዥ እንደሚያስፈልገው... read more
በመዲናዋ የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ከ200 ማለፋቸው ተገለጸ
በዝቅተኛ ገቢ የሚተዳደረውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪ ያለበትን የኑሮ ጫና ለማቅለል በመንግስት የተቋቋሙት የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች ከ200 ማለፋቸውን የአዲስ አበባ... read more
ባለፉት 6 ወራት በከተማዋ ከተፈጠረው የሥራ ዕድል ውስጥ 54 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው ተባለ
መጋቢት 25 ቀን 2018(መናኸሪያ ሬዲዮ)የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች፣ ሕፃናትና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ፤ የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎ እንዲሁም ተጠቃሚነት በተመለከተ... read more
ድምፃዊ ዓምደ-ገብርኤል አድማሱ አዲሱን “ወሄነት” የሚል መጠሪያ ያለውን ሶስተኛ አልበሙን የፊታችን እሁድ ለሙዚቃ አፍቃርያን ሊያቀርብ ነው
ሰኔ 19 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ከአሁን በፊት "ሰበበር ኤነዌ" እና "ሟን ያትገፍሬ" በተሰኙት ሁለት የጉራጌኛ አልበሞቹ እንዲሁም በተለየ መልኩ "እያ ኧረሙድን... read more
1ሺህ 500 የሚሆኑ እና ከአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ዜጎች ተሳታፊ የሚሆኑበት 3ኛው የስራ ዕድል ፈጠራ ፎረም ሊካሄድ እንደሆነ ተገለጸ
ሰኔ 27 ቀን 2017(መናኸሪያ ሬዲዮ)ኢትዮጵያ ካላት እምቅ የሰው ሀይል መካከል ወጣት ክፍሉ ይገኝበታል ያለው የኢፌድሪ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ነው።
የሚኒስቴር... read more
ጊዜዉ ያለፈበት መድሃኒት ቀላቅለዉ ሲሸጡ በተገኙ 105 የመድሃኒት መሸጪያ መደብሮች ላይ አስተዳደረዊ እርምጃ ተወሰደ
በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ መድኃኒት መደብሮች የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ቀላቅለው ይዘው የተገኙና አላግባብ ያስቀመጡ 105 ተቋማት ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ... read more
ከስምንት አመታት በላይ የቆየዉ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የህንጻ ግንባታ በቀጣይ ዓመት እንደሚጠናቀቅ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የህንጻ ግንባታን በ4 መቶ ሚሊዮን ብር ለማከናወን በ2009 ዓ.ም የመሰረት ድንጋይ የተጣለ ሲሆን በ2010 ዓ.ም የግንባታ... read more
ኢትዮጵያ ታሪኳን በአግባቡ መሰነድ ያለመቻሏ ምክንያት ምንድነው?
https://youtu.be/IlFirzEtWHk?si=bEJIMRBlYUUxWNYJ
read more
ምላሽ ይስጡ